www.maledatimes.com የሃገር ውስጥን ሰላም መዝራት ሳይቻል ስለ ጎረቤቶች ማሰብ ህልም እና ቅዥት መደባለቅ ነው !! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሃገር ውስጥን ሰላም መዝራት ሳይቻል ስለ ጎረቤቶች ማሰብ ህልም እና ቅዥት መደባለቅ ነው !!

By   /   March 7, 2019  /   Comments Off on የሃገር ውስጥን ሰላም መዝራት ሳይቻል ስለ ጎረቤቶች ማሰብ ህልም እና ቅዥት መደባለቅ ነው !!

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 27 Second

ዛሬ ይህንን ሃሳብ የምጽፈው በሃገራችን በተፈጠረው የመሬት ይገባኛል ጥያቄ እና የእኔ ዘር ነው የነገሰው በሚል የተፈጠረው እንቢተኝነት እና ሰርአት አልበኝነት ቅጥ ያጣ በመሆኑ መንግስት እየሰበከ ያለውን ፍቅር መንገዱን ስቶ ወደ አንድ አቅጣጫ ብቻ ሲያደላ ፣ ሌላው ሲያጠፋ እንደ እንጀራ ልጅ አፈሙዝ ሲዞርበት ነገር ግን ፣ የተጨቆኑ ዘሮች በሚል አነስተኛ እና ጥቃቅን አስተሳሰብ ዘሮቻቸው ባንክ ሲዘርፉ፣ ሰው ዘቅዝቀው ሲገድሉ፣ በዱላ አዛውንቶችን ሲደበድቡ እና ሲገድሉ ፣ከቦታ ቦታ ሲያፈናቅሉ የምናየው ፣በዚሁ ሃገራችን በምንላት ምስኪን ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ። የሃገር ውስጥን ሰላም መዝራት ሳይቻል ስለ ጎረቤቶች ማሰብ እልም እና ቅዥት መደባለቅ ነው ። በመጀመሪያ የሃገር ውስጥ ሰላም ይቀድማል ፣ የህዝብ ደህንነት፣ የሃገር ደህንነት የህዝብ ደህንነት ነው ፣ ደህንነት ካለ ርሀብን እና እና ችጋርን ማሸነፍ ይቻላል ፤ ነገር ግን የእራሳችንን ችግር ሳንቀርፍ ለሰዎች መሮጥ ግን አግባብም አይደለም ተገቢም አይደለም ። ስለዚህ ዶክተር አብይ ለታይታ በተለያዩ ሃገራቶች የሚያደርጋቸውን የጎረቤት ሃገር የሰላም ማረጋገጫ ስምምነት ጉዞ ከማሰቡ በፊት የሃገሩን ደህንነት ቢያረጋገጥ ይበልጥ ችግሩን በቀላሉ መፍታት በተቻለ ነበር ፣ ታዲያ በተፍረከረረከ ምንግስት መካከል ፣ ችግር የገባው እና መንገድ የጠፋው ህዝብ አምጽ ከፈጠረ የዚህ መንግስት አወዳደቂ የከፋ ሊሆን ይችላል፣ ይህ ማለት ህዝብ ደህና ሲሆን እና ህዝብ ሲወደው አንድን መንግስት ይንከባከበዋል ፣ ህዝብ ከጠላው ግን መድረሻውን እና መጨረሻውን ህዝቡ ያውቀዋል ፡ ይህ ባለበት ሁኔታ ግን በሃገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጠረ ያለው የፖለቲካ ልዩነት እና የህዝቦች አስተሳሰብ ፣ በዘር መከፋፈል ፣ በእውቀት አለመብሰል፣ በተለይም የወጣቶች አለመብሰል እና በጡንቻ ማሰብ ለዚህ መንግስት የፈጠሩት ችግር መንስኤዎች ናቸው ።
አንድ ሃገር ሃገር የምትሆነው በህዝቦቿ ጠንካራ አኗኗር እና በህገ መንግስታዊ ሂደት በሚደረገው የጠበቀ ደህንነታዊ አሰራር ነው ፣በተልፈሰፈሰ መንግስት እና አመራር የሚደረገው ሂደት የሚመጣው አስተዳደር ግን ገቢራዊው ሁኔታ የውድቀትን መገድ መምረጥ ነው ። ይህ ደግሞ ለሃገራዊ ደህንነት ስጋት ይፈጥራል። 
ጓዶች የመጣንበትን የምናውቅ ሰዎች ነን ወይንስ የምንሄድበትን መንገድ የምንመለከት? እንዲያስ ከሆነ የመጣንበትን ካስተዋልን ብዙ አመታትን ተጉዘን ሁላችንም ዘላኖች ነበርን ማንም ሰው አንድ ቦታ ላይ አልተቀመጠም የምንሄድበትን የምናስብ ከሆነ ሁላችንም ወደ አንድ አቅጣጫ እንጂ ለእኔ ወደሚለው መንገድ ከተጓዝን ቀጭኑ መንገድ እልቂት ነው የሚፈጥረው እና መጠንቀቁ ይበጃል ። ጥንቃቄው ለአንዱ ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም ነው ፣ በዘመናችን የእርስ በእርስ ጦርነት የተላለቀንበት ዘመን ሲሆን ዛሬ ግን እርስ በእርሳችን የምንተባበርበት ላይ ነን …ይህንን ልንተባበርበት የሚገባውን እድል ግን የሚሰብሩ ዜጎች አልታጡም ፣ እነዚህ ዜጎች በአንድ ዜጋ ወይንም ብሄር ላይ ያነጣጠረ ጥላቻ እና የጥላቻ መንፈስ ፣ለማካሄያድ ምግባራቸውን መተግበር ጀምረዋል ፣ ይህ የሆነው ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት በተሰጣቸው የጥላቻ መንፈስ ተመርተው ሲሆን ከጀርባው ደግሞ በቤተሰቦቻቸው ፣ በአፈ ታሪክ በተነገራቸው የጥላቻ መንፈስ ታውረው ነው ። ለዚህ መረጃ አቅርቡ ቢባሉም ምንም አይነት በእጃቸው ላይ የቀረበ አሳማኝ መረጃ እንደሌላቸው ያውቁታል። ከብዙሃኑ ኢትዮጵያኖች ጥቂቶቹ ከተለያዩ ሃገራት በዘላንነት መጥተው ሃገሪቱ ላይ የሰፈሩ እና ኢትዮጵያዊነትን የተላበሱ ዜጎች እንደሆኑ ማንም ያውቃል ያም ሆነ ይህ ሲወርድ ሲዋረድ በአንድነት የኖረን ህዝብ እና ኢትዮጵያዊነቱን ተቀብሎ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ሁሉ ሃገሩ እንደሆነች ያምናል ። ስለዚህ ኢትዮጵያን ለማዳን ሲባል ወታደራዊ ስርአት እንዲመራት የሚገባ መንግስት ሊኖር አይገባም ማለት አይደለም ፣ ወታደር የሃገርን ድነበር እና የሃገርን ደህንነት ማስከበር ነው እና በአብይ አስተዳደር ስር ያለው የመከላከያ ሰራዊት በህዝብ ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት ዝም ብሎ ካየ ለሃገር እና ለህዝብ ነው የቆመው ማለቱ ግን ተገቢ አይመስለኝም ። በሃገሪቱ ውስጥ ተከባብሮ የሚኖረው ማንኛውም ዜጋ ፣ ዘር ጾታ ቀለም ዜግነት እና ሃይማኖት ሳይለየው ተቻችሎ እና ተከባብሮ በፈለገው ቦታ የመኖር መብቱ የተጠበቀ ሆኖ መኖር እንዲችል ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ማስከበር ይገባዋል።
ለመላው ህዝባችን ሰላም ለጸረ ሃይሎች …ለጥፋት ሃይሎች ደግሞ የፍትህን ትርጉም ቅጣት ሊሰጣቸው ይገባል

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on March 7, 2019
  • By:
  • Last Modified: March 7, 2019 @ 6:00 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar