www.maledatimes.com የትግራይ ክልል የቤት እጥረት ለመቅረፍ 100 ሄክታር መሬት ለነዋሪዎች አዘጋጀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የትግራይ ክልል የቤት እጥረት ለመቅረፍ 100 ሄክታር መሬት ለነዋሪዎች አዘጋጀ

By   /   April 9, 2019  /   Comments Off on የትግራይ ክልል የቤት እጥረት ለመቅረፍ 100 ሄክታር መሬት ለነዋሪዎች አዘጋጀ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 24 Second

በትግራይ ክልል የቤት እጥረት ለመቅረፍ ለግለሰቦችና ማኅበራት 100 ሄክታር መሬት መዘጋጀቱን መስተዳደሩ አስታወቀ። በክልሉ ለ500 ማኅበራት የሚሆነ መሬት የተዘጋጀ ሲሆን ለአንድ ሰው 70 ካሬ ለመስጠት ምዝገባ መጀመሩን ክልሉ ይፋ አድርጓል።

የቤት እጥረትን ለመቅረፍ በማኅበር ለተደራጁ ነዋሪዎች መሬት መስጠት የተጀመረው በ2009 የተጀመረ ሲሆን የአሁኑ ምዝገባ ከባለፉት ዓመታት ለየት የሚያደርገው በክልሎ ከአንድ በላይ ይዞታ ያላቸው ሰዎችን አለማካተቱ ነው። ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር ማንኛውም የክልሉ ነዋሪ በተለያዩ ከተሞች መሬት ማግኘት ይፈቀድለት የነበረ ሲሆን በአዲሱ ምዝገባ እንዲቀር ተደርጓል።

ለዚህም እንደ ምክንያት የተገለፀው በበፊቱ አሰራር መሬት ለሁሉም ማዳረስ አለመቻሉ ነው። የተዘጋጀው መሬትና አዲሱ ምዝገባው የመንግሥት ሠራተኞችና ለመንግሥት ግብር የሚከፍሉ መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ማኅበረሰቦችን ያማከለ ሲሆን ከዚህ ቀደም ከነበረው አሰራር በተቃራኒ በቀን ሠራተኝነት የሚተዳደሩ በኢኮኖሚ ዝቅተኛ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ያካተተ እንዲሆን መደረጉን ክልሉ አስታውቋል።

አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው በክልሉ የሚኖሩ ተመዝጋቢዎች እንደገለፁት መሬት የማቅረቡ ሒደት ባለፉት ዓመታት በብዛት አቅም ላላቸው ግለሰቦችን ትኩረት ያደረገ ነበር። በአሁን ግን ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ግለሰቦች ማሳተፉን አድንቀዋል። ይሁን እንጂ፤ በተመዝጋቢዎች መብዛት ምክንያት የበዛውን ከፍተኛ መጨናነቅ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል ብለዋል።

በተጨማሪም መካከለኛ ገቢ ባላቸው የልማት ፕሮግራም ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ የመንግሥት ሠራተኞች፣ በሥማቸው የተመዘገበ ቤት የሌላቸው፣ በክልሉ ኹለት ዓመት መኖራቸውን የሚገልፅ የነዋሪነት መታወቂያ ያላቸው ማንኛውም ግለሰቦች፣ በክልሉ ኗሪ የሆኑ የመከላከያ አባላት፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት፣ ድሬዳዋ ፖሊሰ አባላትና የፌዴራል ፖሊስ አባላት ከተመዘጋቢዎች መካከል እንደሆኑ ተገልጿል፡፡ በተለይም በተለያዩ ክልሎች ተፈናቅለው ለመጡ ቅድሚያ እንደሚሠጥ ክልሉ አስታውቋል።

ምንጮች እንደገለፁት ምዝገባው በሚካሔድበት ሁሉም የትግራይ ከተሞች የተመዝጋቢዎች ቁጥር መጨናነቅ የተፈጠረ በመሆኑ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ሰልፍ ለመያዝ ተገደዋል። ይህንን መጨናነቅ ለማስቀረት የሰው ኃይል መጨመሩን ክልሉ ገልጿል።

ምዝገባው ባለፈው ወር የካቲት ከተጀመረ አንስቶ በቀን በአማካይ በመቀሌ ብቻ 20 ማኅበራት እየተመዘገቡ ሲሆን እስከ ረቡዕ፣ መጋቢት 18 ድረስ 290 ማኅበራት በከተማው ብቻ እንደተመዘገቡ ለማወቅ ተችሏል። አሁን ላይ ምዝገባ ብቻ የሚካሔድ ሲሆን መሬት የመስጠቱ ሒደት እስከ ዓመት ሊቆይ እንደሚችል ተነግሯል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on April 9, 2019
  • By:
  • Last Modified: April 9, 2019 @ 8:43 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar