www.maledatimes.com በፓርኮች ላይ የሚከሰት ሰደድ እሳት ለማጥፋት የሚረዱ አውሮፕላኖች እንዲገዙ ጥያቄ ቀረበ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በፓርኮች ላይ የሚከሰት ሰደድ እሳት ለማጥፋት የሚረዱ አውሮፕላኖች እንዲገዙ ጥያቄ ቀረበ

By   /   April 9, 2019  /   Comments Off on በፓርኮች ላይ የሚከሰት ሰደድ እሳት ለማጥፋት የሚረዱ አውሮፕላኖች እንዲገዙ ጥያቄ ቀረበ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 34 Second

  • ባለፉት አራት ወራት በአራት ብሔራዊ ፓርኮች የእሳት አደጋ ተከስቷል

ባለፉት አራት ወራት በአራት ብሔራዊ ፓርኮች ድንገተኛ ሰደድ እሳት በመከሰቱ ከፍተኛ ሽፋን ያለው ደን መውደሙን ተከትሎ የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለድንገተኛ አደጋዎች የሚያገለግሉ አውሮፕላኖች እንዲገዙ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ጥያቄ ማቅረቡ ምንጮች ገለፁ።

እንደኬንያ ባሉ የጎረቤት አገራት እንደዚህ ዓይነት አደጋዎች ሲከሰቱ መከላከል ሥራ ላይ የተሰማሩ 20 አውሮፕላኖች ሲኖሩ፣ ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ መሰል አገልግሎት የሚሰጡ አውሮፕላኖች የሏትም። እስካሁን በአገሪቷ በፓርኮች ውስጥ የተከሰቱ የሰደድ እሳት አደጋዎችን ለማጥፋት የሚሞከረው አፈርና ሌሎች ባሕላዊ መንገዶችን ጥቅም ላይ በማዋል እንደሆነ ይታወሳል።
ይህም በሺዎች የሚቆጠር ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ደን እንዲወድም ሰደድ እሳቱን በአፋጣኝ በቁጥጥር ሥር ለማዋል አዳጋች እንዳደረገው የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጌትነት ይግዛው ገልፀዋል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ አውሮፕላን ግዢ እንዲፈፀም ለጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ጥያቄ ቀርቦ መልስ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ባለፉት 10 ቀናት ብቻ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በተነሳው ሰደድ እሳት 340 ሔክታር መሬት የሸፈነ ደን ጋይቷል። የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው እንደገለፁት፣ በቃጠሎው በፓርኩ እሜት ጎጎ በተባለ ቦታ 311 ሄክታር የተፈጥሮ ደን ሙሉ ለሙሉ ሲወድም ሳንቃ በር በተባለ ቦታ ደግሞ 31 ሄክታሩ በከፊል ጉዳት እንደደረሰበት ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። በአካባቢው መጣል በጀመረው ዝናብ የተፈጠረው ቅዝቃዜ ቃጠሎውን በመቆጣጠር ሒደት የራሱን አስተዋጽኦ እንዳደረገም አክለው ገልጸዋል።
ባለፉት አራት ወራት በባሌ፣ ሰሜን፣ አርሲ ተራሮች እና በሀላይደጌ አሰቦት ብሔራዊ ፓርኮች ሰሞኑን በተከስቱ ድንገተኛ የእሳት አደጋዎች ተከስተዋል። “በሰሜን ፓርክ የነበረው ቃጠሎ ወደ ሌላ አካባቢ እንዳይሰፋፋ የደባርቅ፣ የዳባት፣ የጃናሞራና የጎንደር ከተማ ወጣቶችና ነዋሪዎች እንዲሁም የጎንደርና የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያደረጉት የመከላከል ሥራ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል” ብለዋል።

“የደባርቅ የቱሪስት አስጎብኚ ማኅበራት አባላትና የጸጥታ ኃይሉም አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር” ያሉት ኃላፊው ሆቴሎችና ምግብ ቤቶችም ቃጠሎውን ለማጥፋት ለተሠማራው ኅብረተሰብ ምግብና ውሃ በማቅረብ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ከ5ሺሕ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች ባደረጉት ተሳትፎ ቃጠሎውን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር መቻሉንም አመልክተዋል። እንደ ኃላፊው ገለጻ የቃጠሎውን መንስኤ የሚያጠና ግብር ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል።

በዓለም የተፈጥሮ ቅርስነት የተመዘገበው የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ 412 ስኩየር ኪሎ ሜትር ሥፋት አለው። ፓርኩ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ዋልያ፣ ቀይ ቀበሮና ጭላዳ ዝንጀሮን ጨምሮ የበርካታ የዱር እንስሳትና አእዋፋት መገኛ ሥፍራ መሆኑ ይታወቃል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on April 9, 2019
  • By:
  • Last Modified: April 9, 2019 @ 8:53 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar