www.maledatimes.com በስታዲየም ዙሪያ ያሉ መጠጥ ቤቶችና የቢራ ማስታወቂያ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚታሸጉ ተገለፀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በስታዲየም ዙሪያ ያሉ መጠጥ ቤቶችና የቢራ ማስታወቂያ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚታሸጉ ተገለፀ

By   /   April 27, 2019  /   Comments Off on በስታዲየም ዙሪያ ያሉ መጠጥ ቤቶችና የቢራ ማስታወቂያ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚታሸጉ ተገለፀ

    Print       Email
0 0
Read Time:45 Second

ይልቅ ወሬ ልንገርህ –

የአልኮል መጠናቸው ከሁለት ከመቶ በላይ የሆኑ መጠጦችን የሚያስተዋውቁ የቢራ ማስታወቂያዎች በስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ላይ እንዳይሸጡና እንዳይተዋወቁ የሚከለክለውና በቅርቡ የጸደቀውን አዋጅ ተከትሎ በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ ያሉ መጠጥ ቤቶች እንደሚታሸጉ አልያም ወደ ሌላ የንግድ ዘርፍ እንዲቀይሩ እንደሚደረግ ተገለፀ፡፡
በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ስር የሚገኘው ስፖርት ኮሚሽን አዋጁን ተከትሎ በስታዲየም አካባቢ ያለውን የመጠጥ ማስታወቂያና መጠጥ ቤቶች ላይ ለምን እርምጃ እንዳልተሰደ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የተጠየቁት የኮሚሽኑ የስራ ሀላፊዎች አዋጁ ከወጣ አጭር ጊዜ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን በስታዲየም ዙሪያ ያሉ መጠጥ ቤቶችን ያከራየው እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በመሆኑ አዋጁ ከአንድ ወር በኋላ ተግባራዊ መሆን ሲጀምር በህግ አግባብ ውሉን እንዲያስፈፅም እየተነጋገርን ነው ብለዋል፡፡
በህጉ መሠረት የአልኮል መጠጥ ንግዳቸውንና የቢራ ማስታወቂዎቻቸውን ከስታዲየም ዙሪያ ውጭ ለማድረግ ፍቃደኛ ያልሆኑ ተከራዮችን ውል በማቋረጥ የማሸግ እርምጃ እንደሚወሰድ ከሀላፊው ገለፀ ለመረዳት ተችሏል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሄኒከን ኢትዮጵያ ጋር ለብሔራዊ ቡድኑ ድጋፍ ለማድረግ የ56 ሚሊዮን ብር የስፖንሰር ሽፕ ስምምነት ለመጪዎቹ አምስት ዓመታ ለማድረግ በቅርቡ መስማማቱ ይታወሳል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on April 27, 2019
  • By:
  • Last Modified: April 27, 2019 @ 8:48 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar