www.maledatimes.com በአፋር ክልል ገዋኔ አካባቢ በዛሬው ዕለት ታጣቂዎች በትግራይ ዋልታ ፖሊስ እግር ኳስ ቡድን ላይ ተኩስ ከፍተው አንድ ተጫዋች ሲገድሉ ሌሎች አምስት አቆሰሉ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በአፋር ክልል ገዋኔ አካባቢ በዛሬው ዕለት ታጣቂዎች በትግራይ ዋልታ ፖሊስ እግር ኳስ ቡድን ላይ ተኩስ ከፍተው አንድ ተጫዋች ሲገድሉ ሌሎች አምስት አቆሰሉ።

By   /   April 26, 2019  /   Comments Off on በአፋር ክልል ገዋኔ አካባቢ በዛሬው ዕለት ታጣቂዎች በትግራይ ዋልታ ፖሊስ እግር ኳስ ቡድን ላይ ተኩስ ከፍተው አንድ ተጫዋች ሲገድሉ ሌሎች አምስት አቆሰሉ።

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 3 Second

በአፋር ክልል ገዋኔ አካባቢ በዛሬው ዕለት ታጣቂዎች በትግራይ ዋልታ ፖሊስ እግር ኳስ ቡድን ላይ ተኩስ ከፍተው አንድ ተጫዋች ሲገድሉ ሌሎች አምስት አቆሰሉ።

እግር ኳስ ተጫዋቾቹ ትናንት ከደብረ ብርሃን ከነማ ጋር የነበራቸውን ጨዋታ አጠናቀው ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባ በመነሳት በአፋር በኩል ወደ መቐለ እየተጓዙ ነበር። የትግራይ ክልል ፀጥታ እና አስተዳደር ጽህፈት ቤት የኮምኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሀፍታይ መለስ ጥቃቱ በዛሬው ዕለት ጠዋት 3 ሰዓት ተኩል ገደማ ላይ መፈፀሙን ለዶቼቬሌ የገለጹ መሆኑን ራዲዮ ጣቢያው ገልጧል። በጥቃቱ ከቆሰሉ ስድስት ሰዎች መካከል የአንዱ ሕይወት ማለፉንም ገልጸዋል።

አቶ ሀፍታይ መለስ «የትግራይ ፖሊስ እግር ኳስ ቡድን ከጨዋታ እየተመለሰ መንገድ ላይ ማንነታቸው እስካሁን ድረስ ማንነታቸው በግልፅ ማን እንደሆኑ ያላወቅናቸው ታጣቂዎች ጥቃት አድርሰዋል። በደረሰው ጥቃት ወደ ስድስት የቡድኑ አባላት ቆስለዋል። ከቆሰሉት ሁለቱ ከበድ ያለ ጉዳት ደርሶባቸው ነበር። አንደኛው ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል። በጣም የሚያሳዝን እና እጅግ የሚያስቆጭ አደጋ ነው» ሲሉ ተናግረዋል። 

Image may contain: 8 people, people standing, outdoor and nature
(ፎቶ፦ ትግራይ ዋልታ ፖሊስ እግር ኳስ ቡድን) http://www.maledatimes.com

የትግራይ ክልል የጸጥታ እና አስተዳደር ጽህፈት ቤት ጥቃቱን “በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለው አረመኒያዊ ድርጊት ነው” ሲል አውግዞታል። የጥቃቱ ፈፃሚዎች ማንነት እንደማይታወቅ የገለጸው ጽህፈት ቤቱ “ማንም ሽፍታ እየተነሳ በአውላላ ሜዳ ላይ ዜጎችን ለአደጋ እንዲያጋልጥ እያደረገው ያለው የፌዴራል እና የክልል መንግስታት የዜጎችን በነፃ የመንቀሳቀስ መብት ላይ ብቁ ስራ መስራት በሚችሉበት ቁመና ላይ አለመገኘታቸው ነው” ሲል ወቅሷል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቀደም ብሎ ባወጣው አጭር መግለጫ ጥቃቱ መፈፀሙን አረጋግጧል። 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on April 26, 2019
  • By:
  • Last Modified: April 26, 2019 @ 12:26 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar