www.maledatimes.com - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

By   /   May 25, 2019  /   Comments Off on

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 33 Second

ደገኛው የሰላም አባት ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ዐረፉ • ሥርዐተ ቀብሩ ቅ/ሲኖዶስ በሚወስነው ቀን በመካነ ሰማዕት ቅ/ገላውዴዎስ ይፈጸማል፤ • ለ41 ዓመታት፣ ከኤጲስ ቆጶስነት እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊነት አገልግለዋል፤ • ከማሕሌት እስከ ዐውደ ምሕረት፣ በሙሉ የአገልግሎት ትጋታቸው ይታወቃሉ፤ • በኹለት ቅዱሳን ፓትርያርኮች ምርጫ በዕጩነት ቀርበዋል፤ *** ከየዋሃትና ከደግነት ጋራ በተሟላ የአገልግሎት ሕይወታቸው የታወቁት፣ አንጋፋው የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ዐረፉ፡፡ የ84 ዓመቱ አረጋዊ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ ዛሬ ቅዳሜ፣ ግንቦት 17 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ 11፡30 ላይ፣ ከስኳር እና ከልብ ሕመም ጋራ በተያያዘ የኩላሊት መድከም፣ በሕክምና ሲረዱ በቆዩበት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ዐርፈዋል፡፡ በሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ፣ በ1971 ዓ.ም. ለጅማ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስነት የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፡-

• ከ1971 እስከ 1976 ዓ.ም. የጅማ፣

• ከ1976 እስከ 1978 ዓ.ም. የካፋ፣

• ከ1978 እስከ 1981 ዓ.ም. የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣

• ከ1981 እስከ 2001 ዓ.ም. የደቡብ ጎንደር፣

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ዐረፉ

• ከ2001 እስከ 2011 ዓ.ም.

የሰሜን ጎንደር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመኾን፣ ቤተ ክርስቲያንን ለ41 ዓመታት በትጋት አገልግለዋል፡፡ ጥንቱንም ለሢመተ ጵጵስና ለመመረጥ ያበቃቸው፣ ከማሕሌት ቁመት እስከ ዐውደ ምሕረት ስብከት የዘለቀው ሙሉ አገልግሎታቸው ሲኾን፣ በሕመም ምክንያት እስከተወሰኑበት ጊዜ ድረስ፣ ከተማና ገጠር ሳይመረጡ በትጋት፣ በደግነትና በሰላማዊነት አባታዊ ሓላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡ በፊት ስማቸው መሪጌታ አባ ኅሩይ ይባሉ የነበሩት ብፁዕነታቸው፣ ለሢመት ተጠርተው ሲመረጡ፣ በደብረ ጽጌ ገዳም፣ የድጓ እና የዝማሬ መዋስዕት መምህር ነበሩ፡፡ መጻሕፍተ ሐዲሳትንና ፍትሐ ነገሥትን በደብረ ሊባኖስ ገዳም ተምረዋል፤ የቅኔና የአቋቋም ዐዋቂም ነበሩ፡፡ በአራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እና በስድስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ምርጫ ወቅት፣ በዕጩነት ከቀረቡት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አንዱም ነበሩ፡፡ በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት፣ አፈርዋናት ወረዳ፣ መካነ ሰማዕት ቅዱስ ገላውዴዎስ ደብር፣ በ1927 ዓ.ም. የተወለዱት የአንጋፋው አባት ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ሥርዐተ ቀብር፣ በኑዛዜያቸው መሠረት በዚያው ቤተ ክርስቲያን እንደሚፈጸም ታውቋል፡፡ በመጪው ሰኞ፣ በጎንደር መስቀል ዐደባባይ የስንብት መርሐ ግብር መዘጋጀቱ ተጠቁሟል፤ የሥርዐተ ቀብራቸውን ዕለትና ሰዓት፣ የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤ ስብሰባውን በማካሔድ ላይ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖ እንደሚያስታውቅ ይጠበቃል፡፡ የብፀዕነታቸው በረከት ይድረሰን አሜን፡፡ ከሐራ ተዋሕዶ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on May 25, 2019
  • By:
  • Last Modified: May 25, 2019 @ 3:59 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar