www.maledatimes.com ኦነግ በወለጋ ዞን በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት ፈፀመ። ቢቢሲ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኦነግ በወለጋ ዞን በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት ፈፀመ። ቢቢሲ

By   /   June 20, 2019  /   Comments Off on ኦነግ በወለጋ ዞን በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ጥቃት ፈፀመ። ቢቢሲ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 12 Second

በቄለም ወለጋ ዞን በጋዎ ቄቤ ወረዳ ሽመላ ቀበሌ ውስጥ በመከላከያ ሠራዊት አምስት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የቄለም ወለጋ ዞን የጸጥታና ህዝብ ደህንነት ኃላፊ አቶ ሃብታሙ ታምሩ በበኩላቸው አምስት ሰዎች በመከላከያ ኃይል መገደላቸውን አረጋግጠዋል።

ነገር ግን እሳቸው እንደሚሉት የተገደሉት ሰዎች ንጹሃን ሳይሆኑ የታጠቁ ሃይሎች ናቸው ብለዋል።

“የመከላከያ ሰራዊት እርምጃ የወሰደው በንጹሃን ዜጎች ላይ ሳይሆን በታጠቁ እና በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ሽፍቶች ላይ ነው” ብለዋል::

የሽመላ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ዮሃንስ ወጋ ለቢቢሲ እንደገለፁት “ማክሰኞ ጠዋት የመከላከያ ሰራዊት ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ ህዝቡ ላይ ተኩስ ከፍቶ ነበር” ብለዋል።

በዚህ መካከል አምስት አባወራዎችና ወጣቶች መገደላቸውን አቶ ዮሃንስ ይናገራሉ።

ከተገደሉት ሰዎች መካከል አንዱ የአካባቢው ወጣቶች (ቄሮ) ሃላፊ ነው ብለዋል።

የደህንነታቸው ሁኔታ ስጋት ውስጥ መግባቱን የሚናገሩት አቶ ዮሃንስ ለስደት እንደተዳረጉ ገልፀው “የአካባቢው ነዋሪ አስከሬን እንቅበር ብለው ቢጠይቁም ተከልክለዋል። የአካባቢው ማህበረሰብ ትልቅ ችግር ውስጥ ነው ያለው” ብለዋል።

ሌላኛው የሽመላ ቀበሌ ነዋሪ አቶ መሃመድ የቀበሌው ነዋሪዎች ኦነግን እየደገፋችሁ ነው በማለት ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የተገደሉት ሰዎችን የኦነግ ወታደራዊ ልብስ በማልበስ የኦነግ ወታደሮችን ገድለናል ማለታቸውንም አቶ መሃመድ ገልጸዋል።

አቶ ሃብታሙ በበኩላቸው በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን የተገደሉትም ሆነ የታሰሩት ንጹሃን ዜጎች እንደሆኑ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተ ቢስ ነው ይላሉ።

ከቀድሞው የኦነግ ሰራዊት አባላት መካከል ጫካ የቀሩት ሽፍታ መሆናቸውን አቶ ሃብታሙ ይናገራሉ።

“ከኦነግ ሰራዊት የተነጠሉ ናቸው። ሌላ ስምም የላቸውም። ስማቸውም ከሽፍታ የተለየ ሊሆን አይችልም” ብለዋል አቶ ሃብታሙ።

ኦነግ በቅርቡ በሰጠው መግለጫ በኃይል የታጠቀ ምንም አይነት ወታደር የለኝም ማለቱ የሚታወስ ሲሆን የታጠቀው ሰራዊትም በእኔ የሚመራ አይደለምም ማለቱ የሚታወስ ነው።

በምዕራብ ኦሮሚያ ከሚንቀሳቀሰው የመንግሥት ወታደር ጋር በሚያጋጥሙ ግጭት ምክንያት የግለሰቦች ህይወት እንደሚቀጠፍ የሚወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on June 20, 2019
  • By:
  • Last Modified: June 20, 2019 @ 5:10 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar