www.maledatimes.com የሳውዲ ስታር ምርት በአርባ በመቶ አሽቆለቆለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሳውዲ ስታር ምርት በአርባ በመቶ አሽቆለቆለ

By   /   August 23, 2019  /   Comments Off on የሳውዲ ስታር ምርት በአርባ በመቶ አሽቆለቆለ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 48 Second

ንብረትነቱ የሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲን የሆነው ሳውዲ ስታር የሰፋፊ የእርሻ ፕሮጀክት የ2011 ምርት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር በ40 በመቶ ቅናሽ ያሳየ መሆኑን አዲስ ማለዳ ሰማች፡፡

ኩባንያው የሚያመርተው አብዛኛው ምርት መቀነሱ የተረጋገጠ ቢሆንም በተለይ የበቆሎና ጥጥ ምርቱ በከፍተኛ መጠን አሽቆልቁሏል፡፡ የድርጅቱ ስራ አስከያጅ በድሉ አበራ ለጋዜጣዋ እንደገለጹት ከሆነ ለምርት መቀነሱ ዋና ምክንያት የግብዓት ግዢ በመዘግየቱ የመስኖ ስራውን በተያዘው ዕቅድ መሰረት ማከናወን ባለመቻሉ ነው፡፡

በተጨማሪም የኤሌክተሪክ ኀይል እጥረት እና የእርሻ ማሳው በሚገኝበት የጋምቤላ ክልል በነበረው የሰላምና ፀጥታ ችግር ምክንያት ሰራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ ተሟልተው መገኘት ባለመቻላቸው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም የድርጅቱ የጥጥ ምርት በተለያዩ ተባዮች ምክንያት ውጤት እያስገኘ ባለመሆኑን በመጥቀስ አዲስ ዝርያ በ2012 ወደ ምርት ለማስገባት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል።

ቢዋዋሉም ካራቶሪ ንብረቶቹን ሙሉ በሙሉ ባለማስረከቡ ምክንያት ሳውዲ ስታር የከፈለው ክፍያ 22 ሚሊየን ብር ብቻ መሆኑ ክርክር አስነስቷል፡፡ በሂደት ላይ ያለው ክርክርም ለነሐሴ 28 ለውሳኔ እንደተቀጠረ የተናገሩት የሳውዲ ስታር ስራ አስኪያጅ፤ የፍርድ ሂደቱ ተጠናቆ በቀጣይ አመት እቃዎቹን ሙሉ ለሙሉ በመረከብ በተሻለ አቅም ወደ ስራ በመግባት የምርት መጠኑ ከፍ እንደሚል ያላቸውን ተስፋ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል፡፡ በ2002 በጋምቤላ ክልል በአቦቦ ወረዳ አስር ሺህ ሄክታር መሬት በግብርና ለማልማት መሬት የወሰደው ሳውዲ ስታር ከወሰደው ሰፊ መሬት ውስጥ ማልማት የቻለው 1411 ሄክታሩን ብቻ እንደሆነ የክልሉ የግብርና እና የተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ኡጁሉ ሉላ ለአዲስ ማለዳ ገልፀዋል፡፡

አክለውም ኩባንያው የተሻለ የማምረት ፍላጎት እና አቅም እንዳለው ገልፀው፣ ነገር ግን በተያዘው አመት ዝቅተኛ ምርት ማምረቱን አስረድተዋ፡፡ ‹‹ለምርቱ መቀነስ የተለያዩ ምክንያቶች እንዳሉ ብናውቅም በአመቱ መጨረሻ ቦታው ድረስ ሄደን የምንገማገም ይሆናል›› ብለዋል፡፡ ምክትል የቢሮ ኀላፊው ሳውዲ ስታር የሩዝ እርሻ በአንድ ሺህ ሁለት መቶ ሄክታር፣ በቆሎ በአንድ መቶ አስር ሄክታር፣ ጥጥ በአንድ መቶ ሄክታር፣ ማንጎ በአንድ ነጥብ አምስት ሄክታር ላይ እንደለማ መረጃ እንዳላቸው ተናግረው፤ ዶሮ እና የተለያዩ እንስሳትን ጨምሮ ለማርባት መሬት መውስዱንና እስካሁን ወደ ስራ የተገባባቸው ፕሮጄክቶች የተወሰኑት ብቻ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡

እርሻው በቋሚነት ለ68 ወንድ እንዲሁም ለ32 ሴቶች የስራ እድል እንደፈጠረ የተናገሩት ኡጁሉ ለ521 ወንዶች እና ለ302 ሴቶች ግዜያዊ የስራ እድል እንደፈጠረም ተናግረዋል፡፡ ሳውዲ ስታር ከሰፋፊ የእርሻ ስራው በተጨማሪ የሩዝ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በጋምቤላና ቢሾፍቱ ያስገነባ ሲሆን ፋብሪካው በቀን 400 ቶን ሩዝ የማድረቅና 350 ቶን የመፈልፈል አቅም ያለው መሆኑን የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አስረድተዋል፡፡

ከሚያመርተው የሩዝ ገለባ ተረፈ ምርት ኃይል እያመነጨ የራሱን የኀይል ፍጆታ እንደሚሸፍንም ተናግረዋል፡፡ ኩባንያው ሩዝ በማፅዳት፣ ማሳመር፣ ደረጃ በመስጠትና በቀለም ለይቶ በማሸግ ለገበያ ዝግጁ የማድረግ ስራ ይሰራል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on August 23, 2019
  • By:
  • Last Modified: August 23, 2019 @ 1:39 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar