www.maledatimes.com በጅግጅጋ ከተማ “ሁከት እና ብጥብጥ” ሊያስነሱ ነበር ለተባሉት 10 ሚሊየን ብር የከፈለው ማነው? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በጅግጅጋ ከተማ “ሁከት እና ብጥብጥ” ሊያስነሱ ነበር ለተባሉት 10 ሚሊየን ብር የከፈለው ማነው?

By   /   November 15, 2019  /   Comments Off on በጅግጅጋ ከተማ “ሁከት እና ብጥብጥ” ሊያስነሱ ነበር ለተባሉት 10 ሚሊየን ብር የከፈለው ማነው?

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 2 Second

በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ  የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን  “ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ-መሥተዳድር አቶ ሙስጠፋ ዑመር ከሥልጣናቸው ሊለቁ ይገባል የሚል ጥያቄ አቅርበዋል የተባሉ ሁለት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በጅግጅጋ ከተማ ታሰሩ።” የሚል ዜናን አስነበቡ፡፡ ይህን ዜናም ተከትሎ በርካታ ማህበራዊ ሚዲያዎች ጉዳዩን ሲቀባበሉት ሰንብተዋል፡፡ ሸገር ታይምስ የጉዳዩን እውነታ ለማጣራት ሙከራ ያደረገች ሲሆን እውነት አክቲቪስቶች ታስረዋል? ከሆነስ ምክንያቱ ምንድነው? ስትል ለክልሉ አቃቤ ህግና የፍትህ ቢሮ ኃላፊ ለሆኑት አቶ አብዱ ወሊ ጃምአ በስልክ ጥያቄዋን አቅርባለች፡፡

ኃላፊው ሲመልሱም ሁለቱ ግለሰቦች መታሰራቸውን ጠቁመው “አንደኛው አቶ ከድር ጅግሬ አክቲቪስት ሲሆን በጥቅም ምክንያት ያኮረፈ እና በሌሎች ኃይሎች ተታሎ ወጣቶች ከተማ እንዲረብሹ፣ ተቋማትን እንዲያቃጥሉ መልእክት ሲያስተላልፍ እና የጅግጅጋ አየር መንገድ ላይ ሆኖ በማህበራዊ ድረገፅ እና በኦንላየን ቻናሎች ሁከት እና ብጥብጥ እንዲነሳ ሲቀሰቀስ ነበር” ብለዋል፡፡

“በኢትዮጵያ ህገመንግስት በግልጽ አንደተቀመጠው ማንም ዜጋ የመናገር እና የመፃፍ መብቱ የተጠበቀ ነው” ያሉት አቶ አብዲወሊ “ነገር ግን አክቲቪስት ነኝ በሚል ሽፋን ወጣቶችን በገንዘብ ኃይል በመደገፍ ከተማ ለመረበሽ እና ብሄር ከብሄር፣ ጎሳ ከጎሳ እንዲበጣበጥ እና ክልሉ ሰላም እንዳይሆን ሲሰሩ  በመገኘታቸው እንጂ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአክቲቪስትነታቸው ምክንያት የተፈጠረ ተደርጎ የሚወራው ሀሰት እና ከወሬ የዘለለ አይደለም፡፡” በማለት ሀላፊው የግለሰቦቹን መታሰር ምክንያት አስረድተዋል፡፡

ይህን ተንተርሰን የሰዎቹ ግጭት የመቀስቀስ መነሻና አላማቸው ምን እንደነበር ላቀረብንላቸው ጥያቄም ተከታዩን ነበር ያሉት….

“ ግለሰቦቹ በቀድሞው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ይመራ የነበረውን ሄጎ የተሰኘውን ቡድን ቅሪት በማስተባበር በሁከት እና ብጥብጥ የመንግስትን ስራ ከማስተጓጎል ባሻገር በከተማዋ እና በአጎራባች ከተሞች አመፅ እና ሁከት በመፍጠር በቀጣዩ ሳምንት የሚካሄደውን የኢህሶዴፓ ጠቅላላ ጉባኤ እንዳይካሄድ እንዲያደርጉ  አቅጣጫ ተሰጥቶአቸው ሲሰሩ እንደነበር መረጃ አለን” ብለዋል፡፡

የተገኘው መረጃ ከሰዎቹ እንቅስቃሴ ጀርባ የቀድሞ የክልሉ ባለስልጣናት እጅ እንዳለበት የሚጠቁም ነው ባሉት ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡን ጠይቀን የሰጡን ምላሽ የሚከተለው ነበር፡-

“እጃችን ላይ በርከታ መረጃዎች አሉ ከነዚህ ብጥብጦች ጀርባ ያለው እና በቁጥጥር ስር የዋለው ግለሰብ አቶ አህመድ ኑር ሳሂብ የሚባል ሲሆን የቀድሞው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት እና አሁን በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ያለው የአቶ አብዲ ሙሃመድ ኡመር (አብዲ ኢሌ) የቅርብ ሰው ነው፡፡ ግለሰቡ ቀደም ሲል አል-ኢትሃድ የነበረ እና ጎዴ ላይ አውሮፕላን ለማፈንዳት ሞክሮ በቁጥጥር ስር ውሎ አዲስ አበባ ለረዥም ግዜ ታስሮ የነበረ ሰው ነው፡፡ ግለሰቡ በተለያዩ መንገዶች ህዝብ በህዝብ ላይ እንዲነሳ እና በቀደመው ስርአት በክልሉ ገጥሞ እንደነበረው ቀውስ ለመፍጠር ሲንቀሳቀስ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር ውሏል ፡፡”  ሲሉ ለሸገር ታይምስ ገልጸዋል፡፡

በ10 ሚሊየን ብር ከየት እና ለማን?

“ግለሰቡ ከቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ ኢሌ ባለቤት 10 ሚሊየን ብር ለዚሁ አላማ እንደተቀበለ የሚያሳዩ የስልክ የፅሁፍ መልእክቶች እና የድምፅ ልውውጦችን አግኝተናል” ሲሉ የተናገሩት የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግና የፍትህ ቢሮ ኃላፊ በመጨረሻም “ጉዳዩ በህግ እና በህግ አግባብ ብቻ የሚታይ ይሆናል፡፡ በአክቲቪስነት ስም ግን ሀገር መበጥበጥ እና ከህግ ውጭ መሆን ፈፅሞ አይቻልም!” ሲሉ መልሰዋል

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 4 years ago on November 15, 2019
  • By:
  • Last Modified: November 15, 2019 @ 6:03 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar