www.maledatimes.com የዶ/ር አብይ አህመድ እና የኦቦ ለማ መገርሳ ነገር…. በጋዜጠኛ ታምሩ ገዳ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የዶ/ር አብይ አህመድ እና የኦቦ ለማ መገርሳ ነገር…. በጋዜጠኛ ታምሩ ገዳ

By   /   November 30, 2019  /   Comments Off on የዶ/ር አብይ አህመድ እና የኦቦ ለማ መገርሳ ነገር…. በጋዜጠኛ ታምሩ ገዳ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 36 Second

ኢትዮጵያ አሁን ለተያያዘችው “የለውጥ/የነውጥ ሂደት” ውስጥ አሻራቸውን ከጣሉ የኢሕአዲግ ቁልፍ ፓለቲከኞች መካከል አንዱ ለመሆናቸው ብዙዎች ይመሰክሩላቸዋል፣ የአርባ ዘጠኝ አመቱ የመከላከያ ሚ/ር ሹሙ ለማ መገርሳን።

ታዋቂው ዘ-ኢኮነሚስት መጽሔትን ጨምሮ በበርካታ መገናኛ ብዙሀናት ዘንድ ” ከዘመኑ ተወዳጅ ፓለቲከኞች መካከል አንዱ” ሲሉ ያወደሷቸው የቀድሞው የጨፌ ኦሮሚያ ክልል ገዥ ፓርቲ ፕ/ትነት ስልጣናቸውን ለጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ በመልቀቅ የፓርቲው የምክትልነት ስልጣኑን የያዙት ለማ መገርሳ የትግል አጋራቸው የሆኑት ዶ/ር አብይ አህመድ ለኢትዮጵያ እና ለህዝቦቿ መጻኢ እድሎች ይጠቅማል ብለው የቀመሩት እንደሆነ የሚነገርለት “የመደመር” ፍልስፍናን ሆነ በስም እንጂ በተግባር ማዶ ለማዶ የነበሩት የኢሕአዲግ አውራ ድርጅቶችን ሆነ አጋር ፓርቲዎችን አንድ እንደሚያደርግ የተነገርለት “የብልጽግና ፓርቲን” እንደማይደግፉ በአደባባይ መናገራቸው ብዙዎችን አስደንግጧል፣እያነገገረም ይገኛል።

ከአሜሪካ ራዲዬ የኦሮምኛ ክፍለ ግዜ ጋር ቃለምልልስ ያደረጉት ኦቦ ለማ አስተያየትን የጠቀሰው ብሉምበርግ የዜና አውታር” የዶ/ር አብይ ቅርብ ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ለማ መገርሳ የብልጽግና ፓርቲው ምስረታ ሆነ የመደመር ፍልስፍናው በጥድፊያ የተካሄዱ በመሆናቸው ከጅማሬው ሆነ አሁንም አልስማማበትም ማለታቸው ለጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ መጻኢ የፓለቲካ ጉዞ ብርቱ ፈተና ነው”ብሎታል።

የብልጽግና ፓርቲው ምስረታን በተመለከተ በወዳጆች መገናኛ መረብ ገጻቸው ላይ አስተያየት የሰጡት ዶ/ር አብይ ” አዲሱ የብልጽግና ፓርቲ በምሁራኖች የተጠና እና በሁሉም አመራር ደረጃ ለሚገኙትም ለውይይት የቀረበ ፣ሁሉንም የህግ አግባቦችን የተከተለ ፣አገሪቱን እና ህዝቦቿን ወደ ብልጽግና ምእራፍ የሚያሸጋግር ታላቅ ግብአት ነው” በማለት በፓርቲው መመስረት ያላቸውን ጽኑ እምነት እና የተሰማቸው ደስታንም ገልጸዋል።

የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ህጋዊ ሰውነቱን በማክሰም የብልጽግና ፓርቲን እንደሚቀላቀል በጠቅላላ ጉባኤው ከተስማማ ከሁለት ቀናት በሁዋላ “የመደመሩንም ፍልስፍናን ሆነ የብልጽግናውን ሂደትን አልቀበልም ” የሚል መንፈስ የተላበሰ አስተያየት የሰጡት የመከላከያ ሚ/ር ቁንጮው ለማ መገርሳ ይህ አይነቱ ለጽንፈኞች ፣ ውህደቱን ከጅማሮ ሲቃወሙ ለነበሩ ቡድኖች የልብ ልብ የሚሰጥ እና የአገሪቱ ደህንነትንም ሊፈታተን የሚችል አስተያየት መስጠታቸው ብዙዎች”ያልተጠበቀ ፣ ያልተገራ አስተያየት ፣የትግል አጋሬ ለሚሏቸው አብይ አህመድ አስተዳደርም የክህደት ያህል ይቆጠራል” ሲሉ ኮንነውታል።

አንዳንድ መረጃዎች በበኩላቸው አቶ ለማ መገርሳ ለአሜሪካ ራዲዮ የኦሮሚኛው ክፍለ ጊዜ ሰጥተውታል የተባለው ሙለ ቃለምልልስ ይፋ እንዲሆን ከድርጅታቸው ከኦፒዲ መጠየቁን ሲገልጹ ተስተውለዋል።

እንደ ብሉምበርግ ትንታኔ ከሆነ የአቶ ለማ መገርሳ አስተያየት በመጪው አመት በወረሃ ግንቦት በአገሩቱ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው አገራዊ ምርጫ ለሚሳተፈው እና ከህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ፓርቲ(ህወሀት)ከጅማሬው ተቃውሞ ለግፕጠመው ለብልጽግና ፓርቲ ስኬታማነት ብርቱ ፈታና ሊሆን ይችላል ሲል ስጋተን ገልጿል።

አንድ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎችን በቅርበት የሚከታተሉ፣በአገሪቱ ለተጀመረው “የለውጥ ሂደትም” ልዩ ፍቅር እና እክብሮት እንዳላቸው የሚናገሩ ቅን ኢትዮጵያዊ ለዚህ ጸሀፊ በሰጡት አስተያየት “የዶ/ር አብይ አህመድ እና የኦቦ ለማ መገርሳን ቅርብርቦሽ እና መደጋገፍን ስመለከትው እስከ ቀራኒዮ የሚደርስ የአላማ ጽናት ይኖራቸዋል፣በመልካም እና ታማኝ ጓደኛነትም ይጠቀሳሉ የሚል ፍጹም እምነት እንጂ ፣ እንደዚህ በአደባባይ የማይወጣ ልዩነታቸውን ያረዱናል የሚል ግምት በጭራሽ አልነበረኘም፣የእኛ አገር ፓለቲካ ምን ማለት እንደሆነ አሁን አሁን ገባኝ …ወዘተ ” በማለት ከኦቦ ለማ አፍ ወጣ በተባለው አስተያየት የተሰማቸውን ብሽቀት እና ተስፋ መቁረጣቸውን ገልጸዋል።

ከአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲ በፓለቲካ ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪ እና በአለማቀፍ ግንኙነት በማስትሬት ዲግሪ ትምህርትም የተመረቁት ፣ በለውጡ ማግስት “ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው” በሚለው የሁሉን ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊ ልብ በደስታ ጮቤ ያስረገጠው አባባላቸው የሚታወቁት ኦቦ ለማ ከጥቂት ወራት በፊት “በሰላም ቤተሰቦች” በ አ/አበባው የሚሊዬነም አዳራሽ ተዘጋጅቶ በነበረው እና ለዶ/ር አብይ የተበረከተውን የኢትዮጵያ ካርታን የያዘ ሚዳሊያን ከአንገታቸው አውልቀው በምትኩ በአቶ ለማ መገርሳ አንገት ላይ ያጠለቁላቸው ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ ” ሽልማቱ የሚገባው ለእኔ ሳይሆን በብዙ መከራዎች ፣ ችግሮች ውስጥ ላልተለየኝ ፣ አስተባባሪ በመሆን ከጎኔ ለቆመው፣ ጓደኛዬ እና ወንድሜ ለለማ መገርሳ ይሁንልኝ “ማለታቸው በወቅቱ በብዙዎች ዘንድ ትልቅ አግራሞትን ፈጥሮ እንደነበረ አይዘነጋም።
(በታምሩ ገዳ)

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 4 years ago on November 30, 2019
  • By:
  • Last Modified: November 30, 2019 @ 10:59 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar