www.maledatimes.com የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሰራተኞች ቅሬታ እና የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ መልስ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሰራተኞች ቅሬታ እና የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ መልስ

By   /   April 16, 2020  /   Comments Off on የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሰራተኞች ቅሬታ እና የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ መልስ

    Print       Email
1 0
Read Time:1 Minute, 18 Second

    የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሰራተኞች ቅሬታ እና የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ መልስ

ሰሞኑን በጣም በብዛት ሲደርሱኝ ከነበሩ መልእክቶች አንዱ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ሰራተኞች ቅሬታ ይገኝበታል። ቅሬታዎቹ የመጡት መስሪያ ቤቱ የመዋቅር ስራውን አጠናቆ ያለፈው አርብ ውጤቱን ይፋ ካደረገ በሁዋላ ነበር።

ቅሬታዎቹን ሰብሰብ ሳደርጋቸው ይህንን ይመስላሉ:
– መስሪያ ቤቱ ካሉት 3 ሺህ ገደማ ሰራተኞች ውስጥ 1,080ዎቹ ምደባ አልተሰጠንም፣ በተለይ በብዛት በሲኒየርና ከዛ በላይ ባሉ መደቦች ሲሰሩ የነበሩ አልተመደብንም
– አዲስ የመጡት ሃላፊዎች ነባሮች እንዲቀጥሉ አይፈለጉም፣ ምደባው በውድድር ነው ቢባልም ሀላፊዎች ለማይፈልጉት ዝቅተኛ ነጥብ በመስጠት ለሚፈልጉት ደግሞ ከፍተኛ በመስጠት አንዱን መድቦ ሌላውን አንሳፈዋል
– አሁን በዚህ የኮሮና ቫይረስ አለምን በሚያስጨንቅበት ወቅት ይፋ መደረጉ አግባብ አይደለም
– የእኛ የሰራተኛ የወደፊት እጣ ፈንታ ምንድን ነው የሚለው አሳስቦናል የሚሉ ይገኙበታል።

በጉዳዩ ላይ ማምሻውን የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ የሆኑትን ኢ/ር ሰናይት ዳምጠውን አናግሬ ነበር። መልሳቸው ይህንን ይመስላል:

“ከዚህ በፊት በተሰራ የቢፒአር ስራ ተቋማት ሁሉ እንደ አዲስ ተደራጅተዋል። የኛ ተቋም ወደ ድልድሉ ወይም ምደባው ያልገባው ተቋሙ በጣም ግዙፍ ስለሆነ እና ሌሎችም የሚሰሩ ስራዎች ስለነበሩ በሽግግር ላይ ስለቆየ ነው። አሁን ላይ ላለፉት ወራት የተደረገው ውድድር ሂደቱ ተጠናቆ ነው ይፋ የተደረገው። ይህ ማለት አዳዲስ መደቦች አሉ፣ የታጠፉም አሉ። እዛ ላይ ካሉት 3,000 በላይ ሰራተኞች እንዲወዳደሩ ነው የተደረገው። ስለዚህ አሁን ዋናው ጉዳይ በተወዳደረበት ቦታ ማን ውጤት አገኘ ነው እንጂ ሁሉም በተቋማችን ውስጥ መስራት ይቀጥላሉ። በሚመጥናቸው ቦታ ይመደባሉ፣ ግን በፈለጉበት የስራ ቦታ እንዳይመደቡ በሌሎች ሰራተኞች ተበልጠዋል ማለት ነው። ከዚህ በሁዋላ ቅሬታ ያለው እንዲያቀርብ ይደረጋል። እዚህ እኛ ጋር 1,080 ሰው የሚፈልገውን ቦታው አላገኘም፣ ግን ደግሞ ራሳቸውን የሚጠብቅ ከ1,200 በላይ ክፍት መደብ አለ። እውነታው ይሄ ነው እንጂ ሰራተኛ የሚያሰናብት ተቋም በዚህ ወቅት የለም፣ ደሞዛቸው እና ጥቅማ-ጥቅማቸውም እንደተጠበቀ ይሆናል።”

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 4 years ago on April 16, 2020
  • By:
  • Last Modified: April 16, 2020 @ 7:15 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar