www.maledatimes.com ሰኔ 15 ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በተካሄደ የድጋፍ ሰልፍ ቦምብ በመወርወር ወንጀል የተከሰሱ አምስት ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

ሰኔ 15 ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በተካሄደ የድጋፍ ሰልፍ ቦምብ በመወርወር ወንጀል የተከሰሱ አምስት ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ።

By   /   August 28, 2020  /   Comments Off on ሰኔ 15 ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በተካሄደ የድጋፍ ሰልፍ ቦምብ በመወርወር ወንጀል የተከሰሱ አምስት ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ።

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 24 Second
ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በተካሄደ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ቦምብ በመወርወር የሽብር ወንጀል የተከሰሱ አምስት ተከሳሾች የጥፋተኝነት ፍርድ ተፈረደባቸው።
ተከሳሾቹ ጌቱ ቶሎሳ፣ ብርሃኑ ጃፋር፣ ጥላሁን ጌታቸው፣ ደሳለኝ ተስፋዬ እና ባህሩ ቶላ ናቸው። የጥፋተኝነት ፍርዱን የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የወንጀል ችሎት ነው ያስተላለፈው።
የዐቃቤ ህግ ክስ እንደሚያመላክተው ተከሳሾቹ ወንጀሉን የፈጸሙት ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አባባ መስቀል አደባባይ ከረፋዱ አራት ሰአት ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በተደረገው የድጋፍ ሰልፍ ላይ በ40 ሜትር ርቀት አካባቢ ቦንብ በመወርወር ነው።
ተከሳሾቹ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1ሀ እንዲሁም አንቀጽ 38 እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ፤ በሃገሪቱ ያለውን ለውጥ ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ የሚመራ መንግስት መኖር የለበትም በሚል የራሳቸውን አላማ ለማራመድ በማሰብ መንቀሳቀሳቸውን ዐቃቤ ህግ በክሱ አመላክቷል።
በዚህም ከ1ኛ እስከ 4ኛ ያሉ ተከሳሾች ከሱሉሉታ ከተማ መነሻቸውን በማድረግ በስልክ በመደዋወልና በአካል በመገናኘት በድጋፍ ሰልፉ ላይ እንዴት ቦምብ መወርወር እንዳለባቸው ሲዘጋጁ ቆይተዋልም ነው ያለው ዐቃቤ ህግ፡፡
በዚህ መልኩ በ1ኛ ተከሳሽ ቤት ቡራዩ በማደር 2ኛ ተከሳሽ በሚያሽከረክረው ተሽከርካሪ 2ኛ ተከሳሽ ያዘጋጀውን ኤፍ1 ቦምብ በመያዝ ከ3 እስከ 5ኛ ያሉ ተከሳሾች ጋር ከፒያሳ ወደ ቴድሮስ አደባባይ በመምጣትና የድጋፍ ቲሸርት ልብስ ገዝተው በመልበስ ተመሳስለው መግባታቸው ተጠቅሷል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ንግግር ካደረጉ በኋላ ተከሳሾቹ በ40 ሜትር ርቀት ላይ ቦምብ የወረወሩ ሲሆን በዚህም የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ163 በላይ ሰዎች ላይ ደግሞ ከከባድ እስከ ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸውም ዐቃቤ ህግ አስረድቷል፡፡
የዐቃቤ ህግን የሰነድና የሰው ምስክር እንዲሁም የተከሳሾችን መከላከያ የመረመረው ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹን በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ብሏቸዋል ሲል ፋብኮ ዘግቧል።
በተከሳሾቹ ላይ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠትም ለጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
እስከ ጥቅምት 17 ድረስ ግን የቅጣት ማቅለያዎችን ማቅረብ እንደሚቻል ትዕዛዝ ሰጥቷል።
አብመድ
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar