www.maledatimes.com ከድባጤ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የአስቸኳይ ዕርዳታ ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን ገለጹ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

ከድባጤ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የአስቸኳይ ዕርዳታ ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን ገለጹ!

By   /   November 21, 2020  /   Comments Off on ከድባጤ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የአስቸኳይ ዕርዳታ ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን ገለጹ!

    Print       Email
0 0
Read Time:31 Second

በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች በምግብ፣ በአልባሳት እና በመጠለያ እጦት እየተቸገሩ መሆኑን ለአብመድ ተናግረዋል። በጉዳዩ ላይ የተጠየቀው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለተፈናቃዮች አስቸኳይ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ታረቀኝ ተሲሳ ከኅዳር 5 ጀምሮ ከተለያዩ ቀበሌዎች ተፈናቅለው በድባጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚገኙ 1 ሺህ 200 ተፈናቃዮች 180 ኩንታል እህል እና 20 ኩንታል የህፃናት አልሚ ምግብ እንዲሁም ሦስት ቦንዳ ልብስ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ በዘላቂነት ለማቋቋም ቀጣናው በኮማንድ ፖስት እየተመራ እንደሆነ ኮሚሽነር ታረቀኝ አንስተዋል፡፡ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ይደረጋል፤ መልሶ የማቋቋም ሥራም ይስራል ብለዋል። በአካባቢው ተጨማሪ ጥቃት እንዳይፈጸም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar