www.maledatimes.com በጉራፈርዳ ወረዳ 6 የጸጥታ ኃይሎች በታጣቂዎች ተገደሉ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

በጉራፈርዳ ወረዳ 6 የጸጥታ ኃይሎች በታጣቂዎች ተገደሉ።

By   /   June 6, 2021  /   Comments Off on በጉራፈርዳ ወረዳ 6 የጸጥታ ኃይሎች በታጣቂዎች ተገደሉ።

    Print       Email
0 0
Read Time:33 Second

በጉራፈርዳ ወረዳ 6 የጸጥታ ኃይሎች በታጣቂዎች ተገደሉ።

6 የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በቤንች ሸኮ ዞን በሚገኘው ጉራፈርዳ ወረዳ ውስጥ ትላንት በታጣቂዎች ተገድለዋል።

የልዩ ኃይል አባላቱ የተገደሉት በወረዳው ስር ባለው ወጀምታ ቀበሌ ነው።

“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ” ቃላቸውን የሰጡት የጉራፈርዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ሻሎም ፥ ጥቃት የተፈጸመባቸው የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት፤ በወጀምታ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሰንበሊጥ በተባለ ቦታ ባለ ካምፕ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

8 የልዩ ኃይል አባላት፤ ትላንት ከጠዋት 2 ሰዓት ገደማ፤ አንድ የካምፑን ሰራተኛ አጅበው ውሃ ለመቅዳት ወደ ወንዝ ሲሄዱ ተኩስ እንደተከፈተባቸው አስረድተዋል።

በጥቃቱ ስድስት የልዩ ኃይል አባላት ሲገደሉ አብሯቸው የነበረው የካምፑ ሰራተኛ ጉዳት ደርሶበት ህክምና ላይ ይገኛል ብለዋል።

ለአጀባ ከተሰማሩት የጸጥታ ኃይሎች ውስጥ 2ቱ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባቸውም ሲሉ ገልፀዋል

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar