www.maledatimes.com ኢዜማ በአዲስ አበባ ባለቤትነት ጥያቄ ላይ “የማመቻች አቋም” እንደሌለው አስታወቀ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

ኢዜማ በአዲስ አበባ ባለቤትነት ጥያቄ ላይ “የማመቻች አቋም” እንደሌለው አስታወቀ!

By   /   June 6, 2021  /   Comments Off on ኢዜማ በአዲስ አበባ ባለቤትነት ጥያቄ ላይ “የማመቻች አቋም” እንደሌለው አስታወቀ!

    Print       Email
0 0
Read Time:50 Second

ኢዜማ በአዲስ አበባ ባለቤትነት ጥያቄ ላይ “የማመቻመች አቋም” እንደሌለው አስታወቀ!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ የባለቤትነት ጥያቄ ላይ “ምንም አይነት ብዥታ” እንደሌለው እና በጉዳዩ ላይም “የማመቻመች አቋም” እንደማይከተል አስታወቀ። ፓርቲው ይህን አቋሙን የገለጸው፤ ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 28 በአዲስ አበባው ዋቢ ሸበሌ ሆቴል በነበረው ህዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ ነው።

የፓርቲውን መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ ሌሎች የፓርቲው ዕጩዎች በተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የአዲስ አበባ ከተማን፣ ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ፓርቲው የሚያራምዳቸውን አቋሞች እና አስተሳሰቦች የተመለከቱ ጥያቄዎች ከታዳሚዎች ተነስተዋል። ሶስት መቶ የሚጠጉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በተገኙበት በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የከተማይቱ የባለቤትነት እና የልዩ ጥቅምን የተመለከቱ ጉዳዮች እና ራስን በራስ ማስተዳደርን የተመለከቱ ጥያቄዎች ለፓርቲው ዕጩዎች ቀርበዋል።

ሌሎች ክልሎች በአዲስ አበባ ላይ ያላቸውን ልዩ ጥቅም በተመለከተ ለቀረበው ጥያቄ፤ የኢዜማ መሪ በሰጡት ምላሽ “ለአንድ ብሄር የሚሰጥ ልዩ ጥቅም አይኖርም” ሲሉ የፓርቲያቸውን አቋም አስታውቀዋል። ከአዲስ አበባ መስፋፋት ጋር በተያያዘ ለተነሳው ጥያቄ ደግሞ “አዲስ አበባ መስፋት እስካለባት መስፋት ትችላለች” ብለዋል። ነገር ግን ይህ የከተማዋ መስፋፋት በዙሪያዋ ያሉ ነዋሪዎችን በሚጠቅም እና በማይጎዳ መልኩ መሆን እንዳለበትም አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar