www.maledatimes.com የማንዴላን ስርአተ ቀብር ለማከናወን አስከሬኑ በፕሪቶሪያ ስትሪት ላይ ለህዝብ እይታ ለስንብት ይቀርባል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የማንዴላን ስርአተ ቀብር ለማከናወን አስከሬኑ በፕሪቶሪያ ስትሪት ላይ ለህዝብ እይታ ለስንብት ይቀርባል

By   /   December 7, 2013  /   Comments Off on የማንዴላን ስርአተ ቀብር ለማከናወን አስከሬኑ በፕሪቶሪያ ስትሪት ላይ ለህዝብ እይታ ለስንብት ይቀርባል

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 19 Second

በማንዴላ ስርአተ ቀብር ላይ የመጀመሪያው የጥቁር አፍሪካ አሜሪካዊው ፕረዚዳንት ኦባማ እንዲሁም ዲልማ ሮዜፍ በስራተ ቀብሩ ፕሮግራም ላይ ስንብታቸውን ለማድረግ ለጉዞአቸው ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል ፣በዚህ ሳምንት መግቢያ ላይ ወደ ደቡብ አፍሪካ እንደሚበሩ ተገልጾአል ።

እንደ ደቡብ አፍሪካ መንግስት ገለጻ ከሆነ አስከሬኑ በደቡብ አፍሪካ ዋነኛ አደባባይ ላይ የሚዞር ሲሆን ከዚያም አልፎ በፕሪቶሪያ ጎዳና ላይ ለተወሰነ ሰአት ለህዝብ እይታ ይቀርባል ሲሉ የመንግስት ቃል አልቀባይ የሆኑት ኒዮ ሞሞዱ ተናግረዋል ።Minilik Salsawi

የማንዴላ አስከሬን ለተወሰነ ሰአት የሚቆየው በስቴት ዩኒየን ህንጻ ላይ በሚገኘው ሰፊ ጎዳና ላይ ሲሆን ይህም ሮብ ሃሙስ እና አርብ ቀናቶች ብቻ ልህዝብ እንደሚቀርብ አክለው ገልጸዋል ።ይህም ሲሆን በ95 አመታቸ የአረፉበትን የኔልሰን ማንዴላን የሙት ቀናት አስሩን ቀናቶች የመታሰቢያ ቀን ተደርገው እንደሚታሰቡም አያይዘው የገለጹ ሲሆን በመቀጠልም 90.000 ሰዎችን እና ከዚያም በላይ ይይዝል ትብሎ የሚታሰበው የስዌቶ ስታዲየም የቀጣዩን የመጨረሻውን የመሰናበቻ ፕሮግራም ያከናውናሉ ሲሉ የመንግስ ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።ይህም ስታዲየም በ2010 የመጨረሻውን የአለም አቀፍ እግር ኳስ የተከናወነበት ሜዳ ሲሆን ማንዴላም ከህዝብ ጋር ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የታዩበት (የተሳተፉበት )ሜዳ ነው ።

በዚህ አጋጣሚ የተለያዩ የአለም መንግስታቶች የሃዘን መግለጫቸውን እየላኩ ሲሆን የኡናይትድ ኔሽን ፕረዚዳንት ባንኪ ሙን እና የደቡብ ኮሪያው ፕረዚዳንት ዛሬጠዋት መል እክታቸውን አስተላልፈዋልእንደ ማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል መሰረት ከሆነ፣በዲሴምበር 15 ቀን 2013 አመተ ምህረት አስከሬናቸው ለግብ አተ መሬት ያርፋል ይህም የሚሆነው በቁኑ ከተማ ምስራቃዊ ኬፕታውን አቅጣጫ በምትገኘው የኔልሰን ማንዴላ ትውልድ መንደር እና እድሜ እስኪያውቁ ድረስ ባደጉባት በሂሊ ገጠራማው ክፍል እንደሆነ ይጠቁማል ።

የመጀመሪያው የአሜሪካው ጥቁር ፕረዚዳንት እና የቀድሞው የአሜሪካ ፕረዚዳን ጆርጅ ደብሊው ቡሽ ከባለቤታቸው ጋር ላውራ ቡሽ ወደ ደቡብ አፍሪካ አብረው በአየር ፎርስ በተሰኘው ፕሌን በመጭው ሳምንት ለቀብሩ እንደሚበሩ ዋይት ሃውስ አስታውቆአል በሌላም በኩል የቀድሞው የአሜሪካው ፕረዚዳንት እና በወቅቱ ኔልሰን ማንዴላ ስልጣን ሲይዙ በፕረዚዳንትነት ስልጣን ላይ የነበሩት ቢን ክሊንተን ጉዞ ለማድረግ ወስኛለሁ በቦታውም ላይ እገኛለሁ ሲሉ መደመጣቸውን የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄይ ካርኒ ገልጾአል ።ስለ ባራክ ኦባማ አጠቃላይ መግለጫ ሰሞኑን ይሰጣል ።በሌላም በኩል የብራዚል ብቸኛ ሴት ፕረዚዳንት ዲልማ ሮዜፍ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ደቡብ አፊካ እንደምታመራ ከቢሮዋ የወጣው መረጃ ያመለክታል ።

የመታሰቢያ ፕሮግራሙ ከነገ ጀምሮ ይጀመራል ደቡብ አፍሪካዎችም ተጋብዘዋል ቤተ ክህነቶች ፣የእስልምና መስጂዶች መጅሊሶች እንዲሁም ሌሎችም ህዝቦች በቦታው ላይ ተገኝተው ጸሎቶቻቸውን እንዲያደርጉ ጥሪው ከደቡብ አፍሪካ መንግስት ለህዝብ በመገናኛ ብዙሃን መተላለፉን የማለዳ ታይምስ መረጃ ማእከል ይጠቁማል ።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on December 7, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 7, 2013 @ 11:35 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar