www.maledatimes.com በጅዳ ቆንስል በር ውላ የምታድረው እህት ክራሞት …(ነቢዩ ሲራክ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በጅዳ ቆንስል በር ውላ የምታድረው እህት ክራሞት …(ነቢዩ ሲራክ)

By   /   December 11, 2013  /   Comments Off on በጅዳ ቆንስል በር ውላ የምታድረው እህት ክራሞት …(ነቢዩ ሲራክ)

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 27 Second

      ይህችን እህት በጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት በር ተቀምጣ ካየኋት ሳምንት አልፏል። አልፎ አልፎ ላነጋግራት ብሞክርም መልስ አትሰጥም። መጀመሪያ የየኋት ቀን አካባቢ ከስራ ለተፈናቀሉ እህቶች አነሰም በዛ መጠለያ እያለ ፣ ለምን በር ላይ ትሆናለች? ብየ የጠየቅኳቸው የቆንስሉ ጸጥታ አስከባሪ ” አንተየ የዚህች እህት ጉዳይ አስቸጋሪ ነው ። ከመጠለያው ብዙ ቆይታለች ፣ አሁን በር  ላይ የሆነችው ሃገር ቤት ለመሄድ ወረቀቷ አልቆ እያለ ” ሃገር ቤት አልሄድም!” በማለቷ እነረደሆነ ተነግሮኛል ። ” በመጠለያው የነበሩት ሰነዳቸው ባሳር በመከራ አልቆ ሲሸኙ ወደ ሃገር ቤት አልሸኝም ብላ ረብሻ ከማንሳት አልፎ ከተዘጋጀው መኪና ወርዳ ይህን የምታየው ሚኒባስ መስታውት ሰብራዋለች!  ከዚያን ቀን ወዲህ አትበላም አትጠጣም ፣ እኛንም የገረመን ይሄ ነው!  ሚን ታደርጋለህ! ” ነበር ያሉኝ … 

       ይህ ከተነገረኝም “ወዲህ ሃገር ቤት አልገባም!” ያለችው እህት ለቀናት  በቆንስሉ በር አልጠፋችም። ከተቀመጠችበት ወንበር ጀርባ ባለው ግድግዳ ” ህጋዊ ሰነድ የሌላችሁ እና የወጣውን የሳውዲ ህግ መስፈርት የማታሟሉ ወደ ሃገር ግቡ !” የሚለው የቆንስል ማስታወቂያ ይታያል ። ከአጠገቧ በፕላስቲክ ኪስ የታጨቀ ጓዟን አስቀምጣ ፣  በሆዷ ቁርአን ታቅፋ አንገቷን ከመድፋት ባለፈ በአካባቢው አዛን ስትሰማ የዘወትር ጸሎቷን (ሰላቷን) ወንበሯን ፈቀቅ አድርጋ እንደምትሰግድ አንድ ዘወትር እንቅስቃሴዋን የሚከታተል ወዳጀ አጫውቶኛል… እንዲህ ሆና ኮርመት ብላ ውላ ታድራለች! ቀን ጸሃይ ሲወቃት ፣ ማታ ወበቁ ይፈራረቅባታል ! ካየኋት ቀን ጀምሮ ወደ መጠለያው እንድትገባ ብዙ ሁነን ብንማጸናትም አልተሳካልንም …

       ከሃገሯ በጤና የመጣችው እህት ችግር ውጋቷን እንድንጋራ ስንጠይቃት አትመልስም  !  ወደ ሃገር ቤት እንድትገባ በጅዳ ቆንስል ልትሸኝ ቢሞከርም አልተሳካም። የ”ሃገር ቤት ግቢ!” ” አልገባም!” አለ መግባባት  ፍርሻ ከመምጣቱ በፊት አንዳንዴ ኦሮምኛና ብዙ ጊዜ ግን የተሰባበረ  አረብኛ እየቀላቀለች መናገር ይቀናት እንደነበር አንድ ” በመጠለያው እያለች አውቃታለሁ!” ያሉ ወንድም አጫውተውኛል። ያን ሰሞን ወደ መጠለያው እንድትገባ ተለምና ብትገባም በመጠለያው ውስጥ ካሉ ግፉአን ጋር ግብ ግብ ፈጥራ መውጣቷን ሰምቻለሁ  !

     ይዚህች ግፉዕ እህት ሰላም የነሳና አዕሮዋን ያወከ የውስጥ ህመም ሚስጥር አይታወቅም! ትሰማለች ፣ ለመናገር አልፈቀደችም!  ባሳለፍናቸው የበር ላይ ውሎዋ ትንፍሽ ብላ ስትናገር ቢያን እኔ እስከ ዛሬ አልሰማኋትም ! ውስጧ እንጅ ውጭ አካሏ የተጎዳ አይመስልም! ከሁሉም የሚገርመው ይህች እህት ጤናዋ ታውኮ እንኳ ሃገር ቤት ከወገኖቿ ጋር መቀናቀል ሞት መስሏታል  ! ሌላው አስገራሚ ሂደት  የዚህችን መልከ መልካም እጣ ፈንታ የምንመለከትም ህጋዊ ሰነድ የሌለን ብዙዎች የሳውዲን መንግስት የምህረት ቀቢጸ-ተስፋ ሰንቀን ጤናችን ተጠብቆ እያለ” በሰላም ሃገር ቤት ግቡ !” የሚለውን የመንግስትና የወገን ምክር መቀበል አቅቶናል !  እንዴት ነው ነገሩ …?

አንድየ ይታረቀን ከማለት ባሻገር ምን ይባላል 🙂 ብቻ እሱ ያቅልለው እንጅ የሚሰማ የሚታየው ይከብዳል ! … ያማል … ያማል  !

ነቢዩ ሲራክ 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on December 11, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 11, 2013 @ 6:41 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar