www.maledatimes.com ከጅዳ የሽሜሲ ጊዜያዊ ማቆያ የሚደርሰኝ ሮሮ ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከጅዳ የሽሜሲ ጊዜያዊ ማቆያ የሚደርሰኝ ሮሮ !

By   /   December 26, 2013  /   Comments Off on ከጅዳ የሽሜሲ ጊዜያዊ ማቆያ የሚደርሰኝ ሮሮ !

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 54 Second
             “የሳውዲ መንግስት ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ሳውዲን ለቀው አንዲዎጡ ያስተላለፈውን እና የኢትዮጵያ ኢንባሲና ቆንስለወ መስሪያ ቤቶች ዜጎች ሀጉን አክብረው ወደ ሃገራቸው እንዲወጡ
ያስተላለፉትን ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎች በመረዳት ወደ ሃገር ለመግባት ወደ ሽሜሲ መጠለያ በመሄድ እጃችን የሰጠን ዜጎች እየተንገላታን ነው! ” በማለት ሮሮና ቅሬታቸውን ያቀረቡ ወገኖች መጠለያ እንደገቡ በኢትዮጵያ መንግስት የመጓጓዣ ሰነድ የተሰጣቸው ቢሆንም የሳውዲ ፖስፖር ሃላፊዎች የቀረበላቸውን ሰነድ በማጣራት የመውጫ ሰነድ ለመስጠት አንግልት አያደረሱባቸው መሆኑን ገልጸውልኛል። ጉዳያቸውን ለማስፈጸም በአውቶቡስ ላይ እና በመጠለያው ግቢ ውስጥ ተበትነው በመጠባበቅ ላይ እንደሆኑ የገለጹልኝ እኒህ ወገኖች የአቅመ ደላማ ሴቶችና ህጻናትን እንግልት ከግምት ውስጥ በማስገባት የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ከሚመለከታቸው የሳውዲ መንግስት ሃላፊዎች ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን ትብብር ያደርጉላቸው ዘንድ ጠይቀዋል።

እኒሁ ሮሯችን ለሚመለከታቸው እንዳሰማ የተማጸኑኝ ወገኖች ወደ ጅዳ ቆንሰል ሃላፊዎች ስልክ ደውለው ስልክ ስለማያነሱ ወደ እኔ መደወላቸውን የገለጹልኝ ሲሆን ወደ ሃገር ግቡ ተብለን ወደ ሃገር እንግባ ባልን እንግልት ሊደርስብን አይገባም ሲሉ ” አሁን በደል እያደረሰብን ያለው ሳውዲ ኢሚግሬሽን መፍትሄ እንዲሰጠን ዲፕሎማቶች የተቻላቸውን ያድርጉልን! ” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ። በሌላ በኩል ወደ መጠለያው ገብተው አስፈላጊውን ሰነድ ያሟሉ አንዳንድ ነዋሪዎች መካከል ሻንጣችን ጠፋብን የሚሉና ከአንድ ሻንጣ በላይ እንዳይዙ የተከለከሉ ነዋሪዎችም ተመሳሳይ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

ጉዳዪን ለማሳወቅና ዝርዝር ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊ ወደ አቶ ዘነበ ከበደ እና ወደ ምክትላቸው አቶ ሸሪፍ ስልክ በመደወል ያደረግኩት ሙከራ ዛሬም አልተሳካም!

ሰላም

ነቢዩ ሲራክ

ከጅዳ የሽሜሲ ጊዜያዊ ማቆያ የሚደርሰኝ ሮሮ  !

   "የሳውዲ መንግስት ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ሳውዲን ለቀው አንዲዎጡ ያስተላለፈውን እና የኢትዮጵያ ኢንባሲና ቆንስለወ መስሪያ ቤቶች ዜጎች ሀጉን አክብረው ወደ ሃገራቸው እንዲወጡ 
ያስተላለፉትን ተደጋጋሚ ማሳሰቢያዎች በመረዳት ወደ ሃገር ለመግባት ወደ ሽሜሲ መጠለያ በመሄድ እጃችን የሰጠን ዜጎች እየተንገላታን ነው! " በማለት ሮሮና ቅሬታቸውን ያቀረቡ ወገኖች መጠለያ እንደገቡ በኢትዮጵያ መንግስት የመጓጓዣ ሰነድ የተሰጣቸው ቢሆንም የሳውዲ ፖስፖር ሃላፊዎች የቀረበላቸውን ሰነድ በማጣራት የመውጫ ሰነድ ለመስጠት አንግልት አያደረሱባቸው መሆኑን ገልጸውልኛል።  ጉዳያቸውን ለማስፈጸም  በአውቶቡስ ላይ እና በመጠለያው ግቢ ውስጥ ተበትነው በመጠባበቅ ላይ እንደሆኑ የገለጹልኝ እኒህ ወገኖች የአቅመ ደላማ ሴቶችና ህጻናትን እንግልት ከግምት ውስጥ በማስገባት የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ከሚመለከታቸው የሳውዲ መንግስት ሃላፊዎች ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን ትብብር ያደርጉላቸው ዘንድ ጠይቀዋል። 

   እኒሁ ሮሯችን ለሚመለከታቸው እንዳሰማ የተማጸኑኝ ወገኖች ወደ ጅዳ ቆንሰል ሃላፊዎች ስልክ ደውለው ስልክ ስለማያነሱ ወደ እኔ መደወላቸውን የገለጹልኝ ሲሆን ወደ ሃገር ግቡ ተብለን ወደ ሃገር እንግባ ባልን እንግልት ሊደርስብን አይገባም ሲሉ " አሁን በደል እያደረሰብን ያለው ሳውዲ ኢሚግሬሽን መፍትሄ እንዲሰጠን ዲፕሎማቶች የተቻላቸውን ያድርጉልን! " ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።  በሌላ በኩል ወደ መጠለያው ገብተው አስፈላጊውን ሰነድ ያሟሉ አንዳንድ ነዋሪዎች መካከል ሻንጣችን ጠፋብን የሚሉና ከአንድ ሻንጣ በላይ እንዳይዙ የተከለከሉ ነዋሪዎችም ተመሳሳይ ቅሬታቸውን ገልጸዋል። 

    ጉዳዪን ለማሳወቅና ዝርዝር  ማብራሪያ ለማግኘት ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊ ወደ አቶ ዘነበ ከበደ እና ወደ ምክትላቸው አቶ ሸሪፍ ስልክ በመደወል ያደረግኩት ሙከራ ዛሬም አልተሳካም!  

ሰላም 

ነቢዩ ሲራክ
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on December 26, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 26, 2013 @ 4:46 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar