www.maledatimes.com በአዲስ አበባ የቅርብ ጊዜ የጅምላ ግድያ የተፈጸመባቸው ግለሰቦች አስከሬን በሶስተኛ ሻለቃ (ጃን ሜዳ ግቢ ውስጥ)ተገኘ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በአዲስ አበባ የቅርብ ጊዜ የጅምላ ግድያ የተፈጸመባቸው ግለሰቦች አስከሬን በሶስተኛ ሻለቃ (ጃን ሜዳ ግቢ ውስጥ)ተገኘ!

By   /   December 30, 2013  /   Comments Off on በአዲስ አበባ የቅርብ ጊዜ የጅምላ ግድያ የተፈጸመባቸው ግለሰቦች አስከሬን በሶስተኛ ሻለቃ (ጃን ሜዳ ግቢ ውስጥ)ተገኘ!

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 19 Second

ነገሩ የተከሰተው አርብ እና ቅዳሜ እለት ነው ከስድት ኪሎወደ ፈረንሳይ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው

 የጃንሜዳ ጦር ካምፕ(በቀድሞ ስሙ ሦስተኛ ሻለቃ) ግቢውስጥ በትንሹ ወደ 6 የሚጠጉ አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተገኝተዋል!

 አስከሬኖቹ ሊገኙየቻሉት ለመንገድ ስራ የጦር ካምፑ ግቢ አጥር ወደ ውስጥ ፈርሶ መቆፈር ነበረበት፡፡ በዚህ ሂደት ላይ ነውእንግዲህ በስካቫተር ሲቆፈር በመጀመሪያ ሁለት አስከሬኖች በብርድልብስ እንደተጠቀለሉ ተንከባለሉ፡፡ በዚህየተደናገጡት ሰራተኞችለጊዜው ስራቸን ያቋረጡ ሲሆን በበነጋው ቅዳሜ እለት ረፋዱ ላይ በሌላ አቅጣጫቁፋሮ ሲያደርጉ

 በዛም በኩል እዲሁ በብርድ ልብስ የተጠቀለሉ አራት አስከሬኖች በተመሳሳይ ሁኔታ ከአፈሩዉስጥ ተገኙ፡፡ በዚህ መሃል ከጦር ካምፑ አካባቢ የተወሰኑ መኮንኖችና ከፍተኛ ማዕረግ(ጄነራሎች)በትከሻቸው ላይ ያለባቸው ሰዎች ወደ ቦታው

 በመምጣት ስራው እንዲቆም ትእዛዝ ያስተላለፉ ሲሆንበአካባቢው የነበረውንም ሰው ከቦታው አባረው በትነዋል፡፡ በስፋራው ተገኝተው ሁኔታውን ሲከታተሉ እናበስራው ላይም ተሳታፊ የነበሩ ለሰማያዊ ፓርቲ ቅርብ የነበሩ ሰዎች ፎቶ ለማንሳት 

ጥረት ቢያደርጉምበወታደሮቹ ተመናጭቀዉ ክልከላ ደርሶባቸዋል፡፡እንደምንጮቻችን እና የምስል ማስረጃዎች ከሆነአስከሬኖቹ የተጠቀለሉበት ብርድልብስ አንዳችም ሳይቀደድና ሳይበሰብስ 

ከነአዲስነቱ መገኘቱ ጅምላግድያው በቅርቡ የተፈፀመ ሊሆን እንደሚችል ከፍተኛ ጥርጣሬን አሳድሯል! በጉዳዩ ላይ ማጣራት ለማድረግImage

ሙከራ ያደረጉት ሰማያዊ ፓርቲ አባሎችንም ፊት እንደተነሳቸውና ለማናገርም ፈቃደኛ የሆነ ሰውአለማግኘታቸዉንም እንዳዉም

ቦታውን ባስቸኳይ እንዲለቁ ከሀይለ ቃል ጋር መታዘዛቸውንም ጨምረውተናግረዋል፡፡ ከወታደሮቹ መሀከል የሆነ አንድ ስምና ሀላፊነቱ ለጊዜው ያልታወቀ ምናልባትም የግቢው አዛዥሊሆን የሚችል ሰው ይህ ግቢ ሶስት

ስርዓቶችን ያገለገለ በመሆኑ የማናቸው እንደሆነ ለማወቅ ባይቻልም ሰዎችበመሆናቸው ክቡር ናቸውና አፈር አልብሷቸው ብሎ ትእዛዝ ሲሰጥ የሰሙ የአይን ምስክሮች ለምንጫችንስለሁኔታው አስረድተዋል! በሁኔታው በአካባቢው የነበሩ ሰዎች በእጅጉ ያዘኑና የተደናገጡ  ሲሆንየሚመለከታቸው አካላትና መንግስት ይህne ጉዳይ አጣርተው ለህዝብ ይፋ እንዲሆን አስተያየት ሲሰጡምተደምጠዋል!  በአሁኑ ሰዓት በስፍራው ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ አይታይም፡፡ አካባቢውም በቆርቆሮ ተከልሏል፡፡

Image

 

ተጨማሪ ብርድልብሱ ደብረ ብርሃን ሲሆን ዲዛይኑ በኢህአዲግ ዘመን በቅርብ የተጀመረው ነው!

ሁኔ አቢሲኒያዊ
ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on December 30, 2013
  • By:
  • Last Modified: December 30, 2013 @ 4:06 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar