www.maledatimes.com አንድ ወር ከ15 ቀን ያለ አስታማሚ ኮማ ውስጥ… - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አንድ ወር ከ15 ቀን ያለ አስታማሚ ኮማ ውስጥ…

By   /   February 9, 2014  /   Comments Off on አንድ ወር ከ15 ቀን ያለ አስታማሚ ኮማ ውስጥ…

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 30 Second
አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ
በግሩም ተ/ሀይማኖት
ሰሞኑን ልጄ ሙሴን አሞብኝ ሀኪም ቤት እየተመላለስኩ ነው፡፡ የአራት አመቱ ልጄ ሙሴ ወንደሰን ይባላል፡፡ የስምንት ወር ልጅ እያለ ነው አባቱ ወንደሰን እዚሁ አል-ቶውራ የተባለው ሆስፒታል ውስጥ እያስታመምኩት እጄ ላይ ያረፈው፡፡ አዲስ አበባ ያለው ልጄ እንዳል ግሩም የአባት ፍቅር አጥቶ ማደጉን ሳስበው ሰቀጠጠኝ፡፡ በስደት እኔን በሞት እናቱን ያጣው ልጄ በርቀት ምክንያት የአባትነት ፍቅሬን ልሰጠው እንደማልችል ሳስበው ሙሴም እንዳለም በአባት ፍቅር ማጣት መጎዳት እንደሌለባቸው ወሰንኩ፡፡ ከዚያም በኋላ ሙሴ የአባት ፍቅር እንዳያጣ አባት ልሆነው ለራሴ ቃል ገባሁ፡፡ በቃሌ መሰረት እያሳደኩትም ነው፡፡
ልጄ ሙሴ ህመሙ መለስ ቀለስ እያለበት ቢሆንም በመጨረሻው ሰዓት ደከመብኝ እና ሆስፒታል እንዲተኛ ተደረገ፡፡ ማጅራት ገትር ነው ብለውኝ ተኛ፡፡ ከሞት ተርፎ ህክምናውን እየተከታተለ ስለሆነ እግዚአብሄር ይመስገን፡፡ ግን ልጄን እዛው እያስታመምኩ ሳለሁ ከሀ እስከ ፐ ከጎኔ ሆነው የሚያግዙኝ ጽዳት የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ልጆች አንዲት ኢትዮጵያዊት አስታማሚ የላትም ታማ ኮማ ውስጥ ናት አሉኝ፡፡ ሄድኩና አየኋት፡፡ አትናገርም፣ አትሰማም በጉሮሮ በኩል ኦክስጂን ተሰጥቷት ሳያት እንባ እንባ አለኝ፡፡ ብሎኝስ መቼ ቆመ፡፡ እንባዬን ጠብ ሳደርገው እንዳታየኝና ሆደ እንዳይብሳት ዞር አልኩኝ፡፡ ለካ አይኖቿ ፈጠዋል እንጂ አያዩም፡፡
ፈሳሽ ምግብ የምትወስደው በትቦ ላስቲክ በአፍንጫዋ በኩል ነው፡፡ እጆችዋ አብጠዋል፡፡ አንድ ልጅ እንዳላት ነግረውኛል፡፡ አንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን ስትቆይ መድሀኒት እየገዛ ሊያቀርብላት የሚችል ባለመኖሩ ለጊዜው በማቆያ ለማቆየት እንጂ ለማዳን አልተቻለም፡፡ በሽታዋንም ሆነ ያለባትን ችግር ከማንም መስማት አልቻልኩም፡፡ የህክምና ባለሞያዎችን ለማናገር ብሞክርም ለአንድ ቀንም ቢሆን መድሃኒቱን ግዛላት አሉኝ፡፡ 13400 የየመን ሪያል ተባልኩኝ፡፡ ይህ ማለት 65 ዶላር አካባቢ ማለት ነው፡፡ በየቀኑ የሚያስፈልጋት መድሀኒት፡፡ አቅሜ የፈቀደውን ያህል አደረኩላት፡፡ ግን ትላንት ያደረኩት ለዛሬ አልሆነላትም፡፡ዛሬ ማን ገዝቶላት ይሆን? ታዲያ በምን መንገድ ቀጣይ ነገር ላድርግ የሚለውን ሳስብ ወገኔን ማስቸገር ግድ አለኝ፡፡ አቅም ኖሮኝ ባደርግ ደስ ባለኝ.. ግን አልቻልኩም፡፡ ወገን የምላት እህቴ በጣር ውስጥ ሆና ምንም ማድረግ አለመቻል እንዴት ያማል?…እባካችሁ ለወገን ደራሽ ወገን ነውና ሁላችንም አድርገን ይህቺ እህታችን እናድናት.. እጃችሁን ለመዘርጋት የፈቀዳችሁ
በስልክ ቁጥሬ 00967713545566 ወይም 00967735126401 ብትደውሉልኝ እቀበላለሁ፡፡ አስተናግዳለሁ፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 11 years ago on February 9, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 9, 2014 @ 3:46 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar