www.maledatimes.com አቶ አስራት በ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ለ3 ቀናት እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ወደ ቅሊንጦ ወህኒ ቤት ተወሰዱ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አቶ አስራት በ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ለ3 ቀናት እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ወደ ቅሊንጦ ወህኒ ቤት ተወሰዱ

By   /   February 10, 2014  /   Comments Off on አቶ አስራት በ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ለ3 ቀናት እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ወደ ቅሊንጦ ወህኒ ቤት ተወሰዱ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 26 Second

ዳንኤል ተፈራ ማዓከላዊ ወንጀል ምርመራ በመቅረብ ቃሉን እንዲሰጥ በፌደራል ፖሊስ ታዘዘ፡፡

አቶ አስራት ጣሴ በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ለ3 ቀናት እንዲቆዩ ከተደረገ በኋላ ምክን ያቱ ለጊዜው ግልፅ ባልሆነ ውሳኔ ወደ ቂሊንጦ ከፍተኛ ጥበቃ ወህኒቤት እንዲዛወሩ መደረጉን የፍኖተ ነፃነት የፖሊስ ምንጮች አሳውቀዋል፡፡

የፖሊስ ምንጮቹ እንዳሉት ኦአስራት በፖሊስ ጣቢያው በቆዩባቸው ጊዜያት በእስረኛው ተገቢው አክብሮትና መልካም አቀባበል ማግኘታቸው አሳሪዎቻቸውን አላስደሰተም፡፡

አንድነት ፓርቲን ከምስረታው ጀምሮ በከፍተኛ አመራርነት ሲያገለግሉ የቆዩትና በአሁኑ ወቅትም በፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤትና ስራ አስፈፃሚ የፓርቲዎችን ውህደት እንዲመሩና የአማካሪ ምክርቤት እንዲያቋቁሙ ኃላፊነት የተሰጣቸው መሆኑ ይታወቃል፡፡ አንድነት “የሚሊዮኖች ድምፅ ለፍትህ” በሚል መሪቃል የመንግስት የተለያጡ ሀላፊዎችን ለመክሰስ እንቅስቃሴ ማድረጉን ተከትሎ መንግስትም የአንድነት ፓርቲ አመራሮችን ምክንያት እየፈለገ መክሰስና ማሰር መጀመሩ ገዢው ፓርቲ አለመረጋጋት ውስጥ እንደገባ የሚያመላክት ነው፡፡

ዳንኤል ተፈራ ቃል እንዲሰጥ በፌደራል ፖሊስ ታዘዘ
የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የሆነው ወጣቱ ፖለቲከኛና ደራሲ ዳንኤል ተፈራ ማዓከላዊ ወንጀል ምርመራ በመቅረብ ቃሉን እንዲሰጥ በፌደራል ፖሊስ ታዘዘ፡፡ ፍኖተ ነፃነት ምንጮችን ዋቢ በማድረግ አቶ ዳንኤል ተፈራን ጨምሮ በአራት የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ላይ ክስ ለመመስረት ጥረት እየተደረገ መሆኑን መዘገቧይታወሳል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on February 10, 2014
  • By:
  • Last Modified: February 10, 2014 @ 9:24 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar