www.maledatimes.com በአኖሌ የተቆረጠው የማን እጅ ነው? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በአኖሌ የተቆረጠው የማን እጅ ነው?

By   /   March 5, 2014  /   Comments Off on በአኖሌ የተቆረጠው የማን እጅ ነው?

    Print       Email
0 0
Read Time:13 Minute, 57 Second

እንዲህ ነው በ1860ዎቹ ንጉስ ሚኒሊክ ገና አፄ ሳይባሉ አፄ ቴዎድሮስ ሸዋን ባስገበሩበት ወቅት የተወሰኑ የጎንደሬ ሰራዊት አባላት በሸዋ እንዲቀሩ ተደርጎ ነበር፡፡ እነዚህ የጎንደርና የወሎ ፈረሰኞች ከንጉሥ ሣህለሥላሴ ዘምን ጀምሮ በአርሲና በጨርጨር ሰፍረው ነበር፡፡ አፄ ምኒሊክ ብዙውን ጊዜ በአርሲና በሐረርጌ  በማቅናት ዘመቻው በኦሮሞ ላይ ጭፍጨፋ እንደፈፀሙ ተደርጎ ተወርቷል ብዙ ተብሏል፡፡

መራሩ ሀቅ ግን ይህ ነው፡፡

ኦኖሌ፡-ሀርከ-ሙራ

በአኖሌ የተቆረጠው የማን እጅ ነው? በሂጦሳ አኖሌ የአንድ ኩሩ ኢትዮጵያዊ አርበኛ እጅ ተቆርጧል፡፡ ይህ ሰው ልጅ አበበ ኮላሴ ብሩ ይባላል፡፡ታሪክ ፀሃፊዎቹ ተክለፃዲቅ መኩሪያና ብላቴን ጌታ ኀሩይ ወልደሥላሴ በታሪክ መዛግብቶቻቸው የልጅ አበበን ስም በመጥቀስ የአባታቸውን ስም ለመጥቀስ ያልፈለጉበት ዐብይ ምክንያት ቤተሰቡ በሐረርጌና በሸዋ በነበረው ከፍተኛ ተሰሚነት ነው፡፡ ኃይለሥላሴን ለማንገስ በቅድሚያ የጎንደሬውን ጦር ማሳመን ያስፈልጋል ያሉት የፊታውራሪ ተክለሃዋሪያት ኦቶ ባዮ ግራፊ ለልጅ አበበ አባት ሰም አለመጠቀስ ዋነኛው ምክንያት ነው፡፡ 

በዐፄ ምኒሊክ አጎት በመርዕድ አዝማች ኃይሌ በተጠነሰሰው መፈንቅለ መንግስት ጎንደሬው ደጃዝማች መሸሻ ወርቄን ጨምሮ ከመቅደላው እስር ቤት አፄ ምኒልክን  እንዲያመልጡ የረዱ የምኒሊክ ዘመን ታላላቅ ሰዎች ምኒሊክን በመርዕድ አዝማች ኃይሌ ለመተካት የወጠኑት ውጥን ከሸፈ፡፡ ልጅ አበበ ኮላሴ የተመረጠው ለአፄ ምኒልክ ከነበረው ቅርበት የተነሣ ምኒልክን ከደርብ ላይ ገፍትሮ በመጣል  ለመግደል ስምምነት አድርጎ ነው፡፡ ልጅ አበበ ኮላሴ  የስሜኑ ራስ ውቤ እና የእቴጌ ጣይቱ የስጋ ዘመድ የነበረው  በመሆኑ ከልጅ አበበ ኮላሴ የተሻለ ሰው አልተገኘም፡፡  ልጅ አበበ ኮላሴ ወደ ሸዋ የመጣው ምኒሊክ ገና የሸዋ ንጉስ በነበሩበት በ1860  ዎቹ አጋማሽ   ነው፡፡ ከመቅደላው ጦርነት በኋላ አባታቸው ሰራዊታቸውን ይዘው ወደ ምኒልክ ካመሩት የጦር አዝማቾች ውስጥ የሚገኙት በፊታውራሪ ኮላሴ ብሩ የሚመራው ሲሆን በዚህ ሰራዊት ውስጥ ፊታውራሪ ዋዠቁ እንዲሁም የአቶ አዲሱ ለገሰ አያት ቀኛአዝማች ቀረኩራት ነበሩበት፡፤  ይህ ጦር የጎንደሬ ጦር በመባል የሚታወቅና በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች አገርን በማቅናት ረገድ ተወርዋሪ ኃይል የነበረ የሰራዊት ክፍል ነው፡፡

ይህ ታላቅ ሰራዊት በመጀመሪያ በእንጦጦ ቀጥሎም አሁን ግቢ በሚባለው ስፍራ ከከተመ በኋላ ምኒልክ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በአደረጉት እንቅስቃሴ ከፍተኛና ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡በእነዚህ የተለያዩ ዘመቻዎች አንቱ የተባለ ክንውን ከፈፀሙ በኋላ ስማቸውን የታሪክ መዝገብ ሳያየው ካለፈ ቤተሰቦች ውስጥ ቤተ-ኮላሴ ወይም ወረ-ኮላሴ የሚባሉት ቤተሰቦች ዋንኞቹ ናቸው፡፡

በሶዶ ፣በቤተ ጉራጌ ፣በአርሲና ባሌ ፣እንዲሁም በሐረርጌ ወደ ማዕከላዊ መንግሰት መምጣት የዚህ ቤተሰብ ሚና ቀላል አልነበረም፡፡ ምስጋና ለፈታውራሪ ተክለሐዋሪያት ኦቶ ባዮግራፊ ወደ አድዋ የዘመተው አብዛኛው ራስ መኮንን በበላይነት የሚመራው ሰራዊት በወንድማማቾቹ በፊታውራ ኮላሴ እና በፊታውራሪ አለሙ የጎንደሬ ሰራዊት መሆኑ በአፅንኦት የተጠቀሰ ቢሆንም ይህንን ታሪክ ፈልፍሎ በማውጣት ረገድ የታሪክ ምሁራኖቹ ከተወሰነ ስፍራ ላይ በመወሰናቸው ዛሬ ኦነግና አህዴድ ለሚያነፋሱት አዳዲስ የፈጠራ ወሬዎች ህዝቡ ሰለባ ሆኗል፡፡በአድዋ ጦርነት የሐረርጌን ሰራዊት አድዋ ድረስ ይዘው በመሄድ የተዋጉት ፊታውራሪ ኮላሴ ብሩና ቤተሰባቸው ወደ አድዋ የዘመቱት ልጃቸው ልጅ አበበ ኮላሴ በምኒሊክ አጎት በተጠነሰሰው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እጅና እግር ካጡ  ከአስራ አምስት ዓመት በኋላ ነው፡፡ የልጅ አበበ እጅና እግር መቆረጥ የፈታውራሪ ኮላሴ ብሩ ና ልጆቻው እንዲሁም ከጎንደርና ላሰታ ተሰባስቦ የተከተላቸውን ሰራዊት በአገሩ ላይ እንዲደራደር አላደረገውም፡፡ በአድዋ ጦርነት  በራስ መኮንን መሪነት ታላላቅ ጀብዱዎችን ፈፅመው አገራቸውን ኢትዮጵያን አኩርተዋል፡፡ በአፄ ምኒልክ ይህንን መሰል ቅጣት ለመቀጣት የመጀመሪያው ቤተሰብ አማራ-ሲሆን ይህም የተፈፀመው በልጅ አበበ ኮላሴ ላይ ነው፡፡ ቅጣቱን በአሁን ዘመን መነፅር አይቶ ምኒልክ ትክክል ሰርተዋል አልሰሩም ለማለት በወቅቱ የነበረውን የዕውቀት የንቃተ ህሊና ደረጃና የፍትህ ስርዓት አንፃር መገምገሙ ተገቢ ነው፡፡ በተመሳሳይ ዘመን በአውሮፓ ጊሎቲን የአንገት መቁረጫ ማሽን ተዘጋጅቶ  አንገት የሚቆረጥበት ዘመን ጋር ብናስተያየው በእኛም ሀገር ይፈፀም የነበረው ተመሳሳይ ድርጊት መሆኑን ማሰተዋል ይገባል፡፡ ልጅ አበበ የተቀጣበት ስፍራ የአሁኗ አኖሌ ነበረች፡  በስፍራው የነበሩ ሰዎች ልጅ አበበ ኮላሴን  በኦሮሚኛ ሃርከ ሙራ -እጀ ቆራጣ ለማለት የሰጡት ስም ዛሬ ከበሮ እየተደለቀበት ያለ በተለይም ድህረ ኢህአዴግ ሀርመ ሙራ የምትል ቅጥያ የኦነግና የኦህዴድ ካድሬዎች በማከላቸው  ጡት ጭምር ተቆርጧል አስብሎ በሀሰት የፖለቲካ ትርፍ ፕሮፓጋናዳና ሃውልት በመስራት ቢዝነስ በሚያጧጡፉ ግለሰቦች ሀሰት እውነት ተደርጎ መዘገቡ አሳፋሪ ነው፡፡ እውነት ነው የልጅ አበበ ኮላሴ ቀኝ እጅና ግራ እግር የተቆረጠው በንጉሳዊ ትእዛዝ ነው ፈፃሚዎቹም ከአሁኗ እንጦጦ ወደ አርሲ ሄደው የሰፈሩት ወረ-ሂጦመሌ በሚባል የሚታወቁት የኦሮሞ ጎሳዎች ነው፡፡ የተገላቢጦሽ እንዲሉ በፈሰሰው የነፍጠኛው የልጅ አበበ ኮላሴ ደም ዛሬ ከፍተኛ የፖለቲካ ትርፍ ለማትረፍ የሚንቀሳቀሱ ዋሾዎችን ማየት አሳፋሪ  ከመሆኑም በላይ መንግስት ጉዳዩን በዝምታ መመልከቱ አሳሳቢም ጭምር ነው፡፡

የፊታውራሪ ኮላሴ ቤተሰቦች በሁለተኛው የኢትዮ ኢጣሊያ ወረራ ወቅትም ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገዋል፡፡

ፊታውራሪ ጓንጉል ኮላሴና ወንድማቸው ኃይለማሪያም ኮላሴ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ታንክ የማረኩ መሆናቸውን ጳውሎስ ኞኞ አልተወራላቸውም እንጂ በማለት በኢትዮጵያና በኢጣሊያ ጦርነት ወቅት ስለፈፀሙት ተጋድሎ በመጽሐፉ ዘግቧል፡

ሻምበል መብራቴ ኮላሴ የጥቁር አንበሳ ሰራዊት አባል  ማይጨው በጀግንነት ወድቀዋል ተክለፃዲቅ መኩሪያ ዘግበውታል

የይፍቱ ስራ ኮላሴ ልጅ ፊታውራሪ ነገደ ዘገየ በጎንደርና በሐረር ከኢጣሊያ ጋር በመዋጋት ከፍተኛ ተጋድሎ ፈጽመዋል፡፡ ልጅ አበበ ኮላሴ በፈጸሙት ስህትት ተቀጥተዋል፡፡ እጅና እግራቸው ከተቆረጠበት አርሲ አኖሌ በተቆረጠ እጃቸው አንበሳ ገድለው ለአፄ ምኒልክ የአንበሳ ጎፈር ልከዋል፡፡ ምኒልክም የእጄን በእጄ በማለት መፀፀታቸው አሁን ድረስ የሚወራ ታሪክ ነው፡፡ እናም በአማራው ላይ ለተፈፀመው ድርጊት በኦሮሞ ላይ እንረተፈፀመ ተደርጎ በፈጠራ ድርሳን የሚወራው ወሬ መቆም አለበት፡፡ 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on March 5, 2014
  • By:
  • Last Modified: March 5, 2014 @ 10:55 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar