www.maledatimes.com ወቅታዊ ሪፖርት በኖርዎይ ከኤደን መስፍን(ኖርዌይ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ወቅታዊ ሪፖርት በኖርዎይ ከኤደን መስፍን(ኖርዌይ)

By   /   April 17, 2014  /   Comments Off on ወቅታዊ ሪፖርት በኖርዎይ ከኤደን መስፍን(ኖርዌይ)

    Print       Email
0 0
Read Time:9 Minute, 15 Second

 የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር በኖርዎይ የሚገኙ ኢትዮጵያን ስደቶኞች የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው የሚኖሩበት ሃገር እንደሚሰለሉ እና የወያኔ ሰላዮች በኖርዎያ እንደሚገኙ የኖርዎይ ደህንነት ፖሊስ ለሃገሩ ትልቅ መረጃ መስጠታቸውን በተመሳሳይ ሂውማን ራይትስ ዎች በቅርቡ ያወጣውን መረጃ መሰረት በማድረግ የኖርዎይ መንግስታት ለወያኔ ሰላዮች የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያቆም እና አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ለመጠየቅ እና ኖርዎይ በኢትዮጵያውያን ላይ ያላትን አሳይለም ፖሊሲ እንድታስተካክል በሚል የጠራውን ሰልፍ እጅግ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። ይህ ሰልፍ የኢትዮጵያን በኖርዎይ ምን ይህል የሃገራቸው ሁኔታ እንዳሳሰባቸው እና እየታገሉ እንደሆነ የሚያሳይ ሰልፍ ነበረ። ከኖርዎይ ጂኦግራፊያዊ ይዘት አንጻር ለመሰባሰብ አስቸጋሪ ቢሆንም ኢትዮጵያውያን ግን ይህንን ችግር ከምንም ሳይቆጥሩት ድምጻቸውን እንዳሰሙ ይገኛሉ በርቱ የሚያሰኝ ነው። በሌላውም ሃገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንደ ኖርዎይ አንድ ሆነው ድምጹ የታፈነውን ህዝባችንን ድምጽ ሊሆኑለት ይገባል።

 

በኖርዎይ ዋና ከተማ ኦስሎ ከተለያዩ ቦታ በተሰባሰቡ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በየጊዜው የሚደረገውን የተቃውሞ ሰልፍ ማስተናገዱን ተያይዘዋለች። በኖርዎይ የሚገኙ ጠንካራ ተቃዋሚ ድርጅቶች በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት, የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር ትልቁን ሚና ይጫወታሉ። እነዚህ የተለያዩ ድርጅቶች ለሚያዘጋጁት ሰልፎች መሳካት ደግሞ በኖርዎይ ነዋሪ የሆኑ እና በተለያዩ ካንፕ ውስጥ የሚገኙ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ተጠቃሽ ናቸው። ዓርብ አፕሪል 11 2014 ያየንው ይህንንው ነው። በዚህ ዕለት የኢትዮጵያውያ  ሰደተኞች ማህበር የጠራውን ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ነበር። ሠልፉ የሚጀምረው ከቀኑ 12 ሰአት ይሁን እንጂ በሀገሩ ወቅታዊ ሁኔታ የሚንገበገበው ሀገር ወዳድ ኢትዮጲያዊ ከተባለው ሰአት በፊት ጥሪ በተደረገበት ቦታ ተሰባስቦ የፕሮግራሙን መጀመር ሲጠባበቅ ነበር። የተባለው ሠአት ሲጀምር የዝግጅቱ አስተባባሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁና የዝግጅቱን አላማ በማስተዋወቅ ዝግጅቱ ጀምሯል። ልክ ንግግሩ እንዳለቀ በፕሮግራሙ መሰረት ያለውን ችግር ወደ ሚያስረዳበት ፖርላማ ጉዞውን አድርጎዋል። ህዝቡም ፖርላማ እስከሚደርስ ድረስ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰማ ነበር። በሰልፉ ላይ የተሳተፈው ህዝብም መፈክሩን የሚያሰማው እጅግ ከልቡ ተቆጥቶና በከፍተኛ ጩኸት ነበር።  በዚህ ወቅትም በጎዳና ላይ የነበሩ ኖርዊጅያኖች በመገረም መንገዳቸውን ትተው ቆመው ሲያስተውሉ ነበር። አንዳንዶችም ካሜራቸውንና ሞባይላቸውን ወደ ሰልፈኛው ቀስረው ለረጅም ሰአት ሲቀርጹ ነበር። በዚህ ሁኔታ ወደ ፓርላማው ከተደረሰ በኌላ የተለያዩ ግለሰቦች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ስለ ወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ እና ስለሰልፉ አላማ ንግግሮች አድርገዋል። ሠልፉን በተመለከተም መልዕክታቸውን ከፓርላማ ለተላኩት ግለሰብ ሠጥተዋል።

አፕሪል 12/2014 በኖርዌ ኦስሎ ከተማ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት አዘጋጅነት የአትዮጵያን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ እንደዚሁም የዲያስፖራው የትግል ተሳትፎን የዳሰሰ ታላቅ ስብሰባ ተካሂዷል። በዚህ ሕዝባዊ ስብሰባ ላይ በርካታ አትዮጵያውያን ተገኝተዋል።

 

ለ6 ሠዓታት ያህል የተካሄደው ይህ ስብሰባ የጀመረው በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የሆኑት አቶ አቢ አማረ ጋባዥነት በሀገራችን ባለው በዘረኛው አረመኒያዊ ስርአት በጭካኔ በግፍ ለተገደሉ እና በተለያዩ እስር ቤቶች በፓለቲካ አስተሳሰባቸው ምክንያት ያለጥፍታቸው ያሚሰቃዩትን ውድ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችንን በማሰብ በዚሁ ዘረኛ ቡድን ሰለባ ለሆኑ እና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያዊያን የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማድረግ ነበር። በመቀጠል አቶ ዩሀንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ሊቀመንበር የመግቢያ ንግግር አድርገዋል።

በዚህ ስብሰባ ላይ የእለቱ ተጋባዥ እንግዳ የሆኑት የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት የዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር አባል አቶ ብዙነህ ጽጌ የተገኙ ሲሆን በሃገራችን ስላለው ጠቅላላ የፖለቲካ ሁኔታ እና የግንቦት 7ን አስተዋጽኦ ከህዝቡ የሚጠበቀውንም አጠቃሎ እጅግ ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል። በዝግጅቱ ላይ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት አባሎች  ‘’ላንቺ ነው ሃገሬ’’  የሚለውን መዝሙር አቅርበዋል።

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር!!!

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on April 17, 2014
  • By:
  • Last Modified: April 17, 2014 @ 8:28 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar