www.maledatimes.com ተፈጸመ!!!!!!!!! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ተፈጸመ!!!!!!!!!

By   /   September 2, 2012  /   1 Comment

    Print       Email
0 0
Read Time:9 Minute, 35 Second

የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ  ስርአተ ቀብር በዛሬው እለት ብክብር መጠናቀቁን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ሲያመለክት በአዲስ አበባ ከ20ሺ ሰው በላይ በጎዳዎች ላይ የታደሙ ሲሆን  ከፍተኛ የሃዘን ድባብ በከተማዋ ተላብሶአል ብሎአል ።  በቅድስት ስላሴ ካቴድራል የተፈጸመው ይህ ስራተ ቀብር በፖሊስ ማርሽ እና በመከላከያ ሰራዊት የማርሽ ግሩፕ እንዲሁም የወታደራዊ ስርአት በታጀበ የቀብር ሁኔታ መከናወኑን ገልጾአል ። በቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ለመግባት የተፈቀደላቸው በጣም የተወሰኑ በመሆናቸው አጠቃላይ የስርአቱን አፈጻጸም ለመከታተል እና ለመዘገብ አልቻልንም ያለው ይኸው ዘጋቢ በተለይም አዲሱ ጠ/ሚንስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በመንግስት አካላቶች ም/ጠቅላይ ሚንስትር ተብለው መሰየማቸው እና መጠራታቸው በአሁን ሰአት የሚያሳፍርም ከመሆኑም በላይ በባለስልጣናቶቹ ዘንድ ምንም ነገር የስልጣናቸውን ዘመን እንዳለተጀመረ እና እንዳለጸደቀላቸው የሚያሳይ ፍንጭ ነው ሲል አክሏል ። አንድ የመንግስት ሚንስትር በስራው አገልግሎት ካልዋለበት ቀን ጀምሮ የቀድሞው ሚንስትር እየተባለ መጠራት ሲገባው እስካሁን ድረስ ጠ/ሚንስትር በማለት በድን ስጋውን ሲያወድሱት ታይተዋል ሲል ዘግቦአል ። ይህንን አስመልክቶ የማለዳ ታይምስ አስተባባሪ ዘጋቢ በተለያዩ የሶሻል ኔትዎርኮች ውስጥ በመግባት የተከታተላቸን ሪፖርቶች እንዲህ ያቀርብላችኋል 

አንድ ወዳጄ ያቀበለኝ ጨዋታ…  abe  tokichaw
ሴትየዋ በመለስ ሞት ምክንያት ቤተመንግስቱን ጎብኝተው ሲመለሱ ቤተ መንግስቱን ላላዩ ወዳጆቻቸው “አቤት ድንቅ.. አቤት… አቤት” እያሉ እያዳነቁ ያወራሉ፤ በዚህ መሃል አንዱ “ሰማችሁ ሼክ አላሙዲን ሞቱ እኮ!” ብሎ ይናገራል። ታድያ ይሄኔ ሴትየዋ ምን አሉ…? “ጎሽ ደግሞ ሸራተንን ልንጎበኝ ነዋ!” በሳቅ መሞት

“ቅድም ኦቦ እንደተናገረው መለስ እንዲህ አይነት ቢል ቦርድ እንዲሰቀልለት አይወድም” (ወይዘሮ አዜብ) …… ወይ ጉድ እስከዛሬ መውጫ መግቢያቸው ላይ “አባይን የደፈረ ኢትዮጵያን የደፈረ” እያልን ቢል ቦርድ በመስቀል ስናበሳጫቸው ከርመናላ! (እኔ)አሁን አንድ ወዳጄ በፌስ ቡክ መልዕክት ሳጥኔ ውስጥ እንዲህ አለኝ፤
“አቤ እባክህን Abebe Gellawን ካገኘከው አቶ በረከት ስምዖንንም ተቆጣልን ብሎሃል! በልልኝ!” በሳቅ መሞት…የጠቅላይ ሚኒስትራችን ፍታት እየተደረገ ነው… ቄሱ ደጋግመው “ስለ አገልጋይህ ስለ ገብረማሪያም ነብስ እንማልድሃለን” ይላሉ። ገብረ ማሪያም የጠሚው ክርስትና ስም ነው… ያልገባኝ “አገልጋይህ” መባሉ ነው… የትኛውን አገልግሎት ነው የሚሉት…? የዋልድባውን ይሆን…? የቤተክርስቲያናችን ቅኔ መቼም ማለቂያ የለውም…. በሳቅ  መሞት

ተፈፀመ!… ኦሮማይ!

‎”ተመልካቾቻችን እንደምትመለከቱት ሁሉም ሰው ጥቁር ለብሷል ስለዚህ የሚገርም ሀዘን ነው”
የኢቲቪ ጋዜጠኛ የጠሚው አስከሬን ወደ መስቀል አደባባይ ሲሄድ የተናገረው! ጋዜጠኛ አሸብር ጌትነት ጢሙን አሳድጓል። ታድያ ወዳጄ Desta ን እኔ የምልህ ከአሸበር ጋር ጠሚው ዝምድና ነበራቸው እንዴ? ብለው “ዝምድና በኪስ ይገባል እኮ!” ብሎ መለሰልኝ። በሳቅ መሞት

በቅድሚያ ለወይዘሮ አዜብ መስፍንና ለልጆቻቸው እግዚአብሔር መጽናናትን እንዲሰጣቸው ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ።
በዛሬው የቀብር ሥነ-ስርዓት የኢቲቪ እና የአቶ ሀይለማርያም ነገር ግራ እንዳጋባኝ ነው የዋለው። ንግግር ሲያደርጉ የነበሩት የውጪ አገር መሪዎችና ተወካዮች አቶ ሀይለማርያምን፦”acting prime minister “ እያሉ ሲጠሩ ቢውሉም፤ ኢቲቪ ግን፦”ምክትል ጠ/ሚኒስትር እና የው/ገ/ሚኒስትር የሚለውን አልለቅም ብሎ ነው የዋለው። አሁን የመስቀል አደባባዩ ዝግጅት ካለቀ በሁዋላማ ሆን ብሎ እስኪመስል ድረስ በተደጋጋሚ በድሮው ማዕረግ መጥራቱን ቀጥሎበታል። ይህ የሚያሳየው፤የአቶ ሀይለማርያም ሹመት ገና አለመርጋቱን ነው።
ለማንኛውም የሚሆነውን ነገር ነገ እና ከነገ ወዲያ እናየዋለን።
ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም አሉ ! …. ይህ መነኩሴ ወይስ …. ? ጨርቅ ብሎ ባዋረዳት ሰንደቅ ዓላማችን በድኑ ተጠቅሎ፣ የነፍጠኞች መሸሸጊያ ናት እያለ ባንቋሸሻት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መቀበሩ ሲገርመን የበግ ለምድ የለበሱ መነኩሴ የወያኔ ዓርማ ያለበት ሰንደቅ አላማ ከዘራቸው ላይ ሰክተው በመለስ ዜናዊ ሞት ሲያነቡ አየን። መለስ ለመነኮሳት ደግሞ ምን አድርጎ ነበር ሊሉን ይሆን? … እኚህ አባት መለስ የዋልድባን ገዳማት ወደ ሸንኮራ አገዳ ልማት ጣቢያ ለመቀየር ያወጣው እቅድ ተግባራዊ ሳይሆን እግዚአብሔር ስለወሰደው አዝነው ይሆን የሚያነቡት? …. ወይንስ በውስጣቸው ስር የሰደደውን የዘረኝነት ልክፍት ሙሉ ለሙሉ ሳያስወግዱ ቆብ የደፉ አስመሳይ መነኩሴ ናቸው? … እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስቲያናችንን ከእንዲህ አይነት የበግ ለምድ ከለበሱ ተኩላዎች ይጠብቅልን!
http://www.bbc.co.uk/news/world-africa-19454253
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 2, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 2, 2012 @ 6:31 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With: ,

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

One thought on “ተፈጸመ!!!!!!!!!

  1. It’s almost laughable to see the staged ceremony to make one simple tribal guy to larger than life. This again shows they try to make themselves as the Australian journalist said, unconventional style for Ethiopia. Who’s he? how quick did he forget he left the jungle 17 years a go and today he pour the countries resources to a charlatan parade. It’s once again obvious all that staged crying and drama on Addis Abeba street just to stay in power and to show the world how people pour their love. Who are you kidding they know more than you think they do….oh you people make us laugh how funny.

    Keep up your dramatized house of cards it’ll be unveiled soon.

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar