www.maledatimes.com የኢትዮጵያውን ቀን ተከብሮ ፣በደማቅ ክብረ በአል እንደነበረው ተጠቁሞአል ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያውን ቀን ተከብሮ ፣በደማቅ ክብረ በአል እንደነበረው ተጠቁሞአል ።

By   /   September 8, 2012  /   Comments Off on የኢትዮጵያውን ቀን ተከብሮ ፣በደማቅ ክብረ በአል እንደነበረው ተጠቁሞአል ።

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 33 Second

በየአመቱ የሚከናወነውን  እና ልዩ የበአል ድምቀት ሰጥቶት የነበረው የኢትዮጵያኖች ቀን በታላቅ ክብረ በአል ተከብሮ ውሎአል ።በትላንትናው እለት የተካሄደውን የኢትዮጵያኖችን ቀን አስመልክቶ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያኖች እና ኢትዮጵያን ወዳጆች እንዲሁም ከኢትዮጵያ በማደጎ የሚያድጉ እና ያደጉ ኢትዮ አመሪካኖች ከአሳዳጊዎቻቸው ጋር በመሆን  በዴይሊ ሴንተር በመገኘት በአሉን አክብረዋል ። በክብረ በአሉ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በመዲናዋ ሲውለበለብ የህዝብ መዝሙሯንም በአንድነት ከሃገሪቱ የህዝብ መዝሙር ጋር ተዘምሯል። የኢትዮጵያን አዲስ አመት አስመልክቶ በቺካጎ ማህበረሰብ የተሰየመውን እና በየአመቱ በመዲናዋ መሃል ቦታ ላይ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ቀንን በደማቅ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን በተለይም ከተለያዩ የመንግስት ተቋማት እና የአፍሪካ ኮሚኒቲዎች በስፍራው በመገኘት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።በትላንትናው እለት የድምጻዊ ካሳሁን ታዬ (ሶራ) በመታጀብ የበአሉን ድምቀት አሰደሳች በማድረግ ወጣት ተወዛዋዦች ባህሎቻቸውን እና የእለቱን የብሄር ብሄረሰቦች ውዝዋዜ ያደረጉ ሲሆን በዛሬው እለትም ቀጣዩን የባህል ጨዋታ በክሮሺያ ሴንተር በሰፊው እንደሚያደርጉ ከማህበሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ። በተለይም በኢትዮጵያ ኮሙኒቲ አሶሴሽን ኦፍ ቺካጎ ዳይሬክተር የአዲሱን አመት አስመልክቶ ባስተላለፉት መልእክት ህዝቦች ልዩነታቸውን አቻችለው ፣ለተጠናከረ ሰላም አንድ ላይ የሚጓዙበት መንገድ መፍጠር መቻል አለባቸው ፣ማንኛውም ሰው የፖለቲካ ልዩነቱን ወድኋላ በመተው ፣ከኮሙኒቲው ጋር በመሆን ወገኖቹን እና ሃገሩን በጥንካሬ መርዳት ይገባዋል ሲሉ ይህ ዘመን የእኛ ነው ሰርተንም የምንለወጥበት ፣ሰርተን እድገታችንን የምናሳይበት ፣ዛሬ ላይ ቆመን ነገን የምናስብበት ስለሆነ በአንድነት ፣በሰላም እና በፍቅር ወደ 2005 እንደንሸጋገር እጅ ለእጅ እንጓዝ የጋራ ድላችንም ይሁን ዘመኑን አሁንም የሰላም እና የደስታ ዘመን ይሁንላችሁ ሲሉ በግላቸው እና ኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማህበር ስም  አስተላልፈዋል።

Ethiopian Day, Official Celebration in Chicago 2012 (Chicago Reggae Channel)

34 views 

   

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 8, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 20, 2012 @ 10:59 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar