www.maledatimes.com ኢትዮጵያዊነት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሠረቱ ነው! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢትዮጵያዊነት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሠረቱ ነው!

By   /   May 12, 2014  /   Comments Off on ኢትዮጵያዊነት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሠረቱ ነው!

    Print       Email
0 0
Read Time:12 Minute, 4 Second

አሲምባ ርዕሰ አንቀጽ
Editor’s Note ቁጥር 4/2006

May 12, 2014 አሲምባ ርዕሰ አንቀጽ ቁጥር 4/2004 ግንቦት 3 ቀን 2006 ዓ.ም.

1

ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ኩታ ገጠም ያሉ ብዙ ከተሞችን በዋና ከተማው ሥር ለመጠቅለል የወያኔ አገዛዝ
በሥራ ላይ ለማዋል አቀረብኩ የሚለውን “የተቀናጀ የልማት ማስተር ፕላን”ን በመቃወም ድምጻቸውን
ለማሰማት በአምቦ፣ በጅማ መቱና በመሳሰሉት ከተሞች ሠላማዊ ሠልፍ የወጡ ወገኖቻችን ላይ የገዢው
ሥርዓት (ወያኔ) ያደረሰውን ፋሺሽታዊ የግድያና የአፈና እርምጃ የአሲምባ ድረ-ገጽ ዝግጅ ክፍል አጥብቀን
እያወገዝን በኢትዮጵያዊነት የምናም ሁሉ በያለንበት ካለምንም ማወላወል በአንድ ድምፅ እጥብቀን ልናወግዘው
የሚገባ መሆኑን እናሳስባለን። ስለሆነም በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ፍጅት ስንቃወም በሀገራችን እንዲሠፍን
የምንታገልለት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መሠረቱ ኢትዮጵያዊነት ብቻ መሆኑ መዘንጋት የለበትም።
የወያኔዎች ሥርዓት መሠረቱ የሆነው የጎሣና የክልል ፖከቲካ፣ በስብሶና ከስሮ በራሳቸው መካከል
በአውራጃና በመንደር ሳይቀር ተከፋፍለው ተፋጠው ባሉበት በአሁኑ ወቅት፤ ሥርዓቱን ከጻዕረ-ሞት ለማዳንና
በየዕለቱ እየጎለበተ የመጣውን የሕዝቡን የአመጽ ስሜት ለማቀዝቀዝ፣ ወያኔና መሰሎቹ አይቧጥጡት ገደል፣
አይገለብጡጥት ድንጋይ፣ አለመኖሩን የሰሞኑን የተማሪዎች እንቅስቃሴ የኦሮሞዎች ብቻ ችግርና ጥያቄአቸውም
የጎጠኝነት መርዝ የተቀላቀለበት እንደሆነ ለማስመሰል ወያኔና መሰሎቹ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ መሆኑን
እየታዘብን ነው። የተለያዩ የውጥረት ፈንጂዎችን በኢትዮጵያውያን መካከል በመቅበር ትርምሳችን ሲወጣ
ወያኔዎችና መሰሎቻቸው ክስረትና ውድቀታቸውን ለመጠገን የማይሸርቡት ጉድ አለመኖሩን መገንዘብ የሁሉም
ሀገር ወዳድ ግዴታ ነው። ከሁሉም በላይ በሀገር ቤት ያሉት ወያኔና የፈለፈላቸው የጎሣ ፖለቲከኞችና
ድርጅቶቻቸውም ሆኑ ተሰደውም ለጎሣችን ተጠሪዎች ነን የሚሉን ሁሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች
መሆናቸውን አለመዘንጋት ተገቢ ነው። በየአቅጣጫው እየተፋፋመ ያለው ሕዝባዊ እንቅስቃሴ መሠረቱ ወያኔ
ከ23 ዓመታት በፊት በጠመንጃ ኃይልና በምዕራባውያን ዕርዳታ በሕዝቡ ላይ የጫነው የክልል ጭቆና ሥርዓት
ብቻ ነው። የጥያቄው መሠረት የዴሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብት መነፈግ፣ የፍትሕና የመልካም አስተዳፈር ብቻ
ነው። የሁላችንም ኃይልና ትኩረት መሆን ያለበት ደግሞ የዴሞክራሲ፣ የሰብአዊ መብት፣ የፍትሕና የመልካም
አስተዳደር ባላንጣ የሆነውን የወያኔን ሥርዓት ከነሰንኮፉ መነጋግሎ መጣልና በምትኩ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ
ሥርዓት በመላው ኢትዮጵያ እንዲሰፍን ማድረግ ብቻ መሆን አለበት።
ወያኔና መሰሎቹ የሰሞኑን በአምቦና በመሳሰሉት የተነሳውን የተማሪዎች አመጽ አስመልክቶ
እንደሚነዙብን መፍረስ ያለበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ቅርስ፣ የዓለም አቀፍ የጸረ ቅኝ አገዛዝ ምልክት የሆነው የአፄ
ሚኒሊክ ኃውልት ሳይሆን የወያኔው የጎሠኞች ሥርዓት ብቻ ነው። ጥሪው መሆን ያለበት የወያኔንና መሰሎቹን
የጭቆና ቀንበር አሽነቀንጥሮ መጣል ብቻ ነው። ጎሣንና ኃይማኖትን መሠረት ያደረገ ፖለቲካ ዴሞክራሲያዊና
ፍትሃዊ ሥርዓትን ማምጣት አለመቻሉን እነሆ በመላው ዓለም በተለይ በቅርባችን አፍሪካ ከአጎራባች ሀገሮች
ከኤርትራ ብንጀምር፤ የሻቢያ ሥርዓት ዴሞክራሲያዊ መብትን ለኤርትራውያን ሲያጎናጽፍ አላየንም። ችግራችን
ኢትዮጵያዊነትና አማራው ነው ብሎ ቀስቅሶ ከባርነት ነፃ ወጣን ያለው ሻዕቢያ የኢርትራን ሕዝብ እሥረኛውና
ባርያ ማድረጉን ኤርትራውያንን ጠይቆ መረዳት ነው። ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ሕዝባዊ ፍትሃዊና የሰባአዊ
መብት ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አማራ ይሁን ኦሮሞ ወይም ወይጦ መብቱ የሚረጋገጥበት ነው። የጎሣ
ፖለቲከኞችና ተባባሪዎቻቸው በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የመጡ መዓቶች ናቸውና ዛሬ ቅራኔው በኢትዮጵያ
ሕዝብና በጎሠኛ ፖለቲከኞች መሪ የወያኔ ኤሊቶች መካከል ነው። ዴሞክራሲያዊት ሕዝባዊ ኢትዮጵያ
የምትመጣው በወያኔና በኮለኮላቸው የጎሣ ፖለቲከኞች መቃብር ላይ ብቻ ነው። አሲምባ ርዕሰ አንቀጽ
Editor’s Note ቁጥር 4/2006

May 12, 2014 አሲምባ ርዕሰ አንቀጽ ቁጥር 4/2004 ግንቦት 3 ቀን 2006 ዓ.ም.

2

ከዚህ በፊት አሲምባዎች ደጋግመን እንዳሳሰብነው ሀገር ወዳዶች በኢትዮጵያዊነት አጀንዳ
እንሰባሰብ! እንደራጅ! በኢትዮጵያዊነት አጀንዳም እንሰባሰብ ስንል ኢትዮጵያዊነትን የተላበሱ መስለው
ጩኸታችንን የሚያሰሙ ግን በውስጣቸው በወያኔዎችና ፀረ- ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች የሚዘወሩ
ድርጅቶችን ለይተን እንመርምር። እንደ ኦነግ ያሉ በፀረ-ኢትዮጵያዊነት የሚንቀሳቀሱትና እውነተኛ
ኢትዮጵያዊ ድርጅቶችን ለይተን እንወቅ! ፀረ-ኢትዮጵያዊ የሆኑ ክፍሎችን መድረክ የሚሰጡ ሚዲያዎችን
ተጠያቂ እናድርግ። ኢትዮጵያዊ አጀንዳ ያላቸው ድርጅቶችን እንርዳ! ማንም ወደደም ጠላ
ኢትዮጵያዊነትን እንደሚጋባ ቁምጥና በሽታ የምንሸሸው ሳይሆን እቅፍ የምናደርገው፣ ያውም ባደባባይ
ያበጠው ይፈንዳ ብለን አንገታችንን ቀና ፣ ደረታችንን ነፋ አድርገን የምንሄድበት ሁናቴን የምንፈጥርበት
መሆን አለበት። ለዘመኑ የጎሠኝነት ወረርሽኝ በሽታም ማርከሻው ኢትዮጵያዊነት ብቻ መሆኑን አውቀን
ኢትዮጵያዊነት በሁሉም መስክ እንዲንፀባረቅ ማድረግ፤ መጠየቅም የእያንዳንዳችን ፈንታ መሆን አለበት።
በዚህም ዓይነት ስነ-ልቦና የምንገነባው ኢትዮጵያዊነት እንደ አባቶቻችን ከብረት የጠነከረ ዕምነትንና
መተማመንን በመካከለችን ኮትኩተን የምንገነባበት ሊሆን ይገባዋል። በሀገራችን ኢትዮጵያ ሁሉም
ተከባብሮ የሚኖርበት ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ዋና መሠረቱ ኢትዮጵያዊነት ብቻ ነው።

ኢትዮጵያዊነት ያለጥርጥር በትግላችን ያቸንፋል!
የሚፈርሰው የወያኔዎችና ግብረ-አበሮቻቸው ሥርዓት ብቻ!

የኢሲምባ ድረ-ገጽ ዝግጅት ክፍል
(ግንቦት 3 ቀን 2006 ዓ.ም.)

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on May 12, 2014
  • By:
  • Last Modified: May 12, 2014 @ 10:41 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar