www.maledatimes.com የአራት ደራስያን መታሰቢያ ቴምብሮች ታተሙ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአራት ደራስያን መታሰቢያ ቴምብሮች ታተሙ

By   /   September 9, 2012  /   1 Comment

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 22 Second

በሔኖክ ያሬድ reporter 

በኢትዮጵያ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ ሁነኛ ስፍራ ላላቸው አራት ደራስያን የታተሙ ቴምብሮች ባለፈው ዓርብ ተመረቁ፡፡

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ከኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር (ኢደማ) ጋር በመተባበር የመታሰቢያ ቴምብር ያሳተመላቸው ደራስያን ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ፣ ቀኝጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ፣ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴና አቶ ተመስገን ገብሬ ናቸው፡፡

“የኢትዮጵያ ደራስያን 2ኛ ዕትም” በሚል የታተሙትና ጳጉሜን 2 ቀን 2004 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ የተመረቁት ቴምብሮች የአራቱ ደራስያን ምስሎች ያረፈባቸው ሲሆኑ የ20 ሳንቲም፣ የ80 ሳንቲም፣ የአንድና ሁለት ብር ዋጋ አላቸው፡፡ ዲዛይነሮቹ ሠዓልያኑ አገኘሁ አዳነና እሸቱ ጥሩነህ ናቸው፡፡

ነጋድራስና የድሬዳዋ ጉምሩክ ኃላፊ የነበሩት ደራሲ አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ (1868-1947) ካሳተሟቸው መካከል የመጀመርያው የአማርኛ “ልብ ወለድ ታሪክ” (ጦቢያ) እና “ዳግማዊ አጤ ምኒልክ” ይገኙበታል፡፡ የመጀመርያው የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር “ኢትዮጵያ ሆይ ደስ ይበልሽ በአምላክሽ ኃይል በንጉሥሽ” የሚለውን የደረሱት ቀኝጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ (1887-1939) ስለአገር ፍቅርና ጀግንነት የሚያወሱ በርካታ ድራማዎችና መዝሙሮችን የደረሱ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል “አፋጀሽኝ”፣ “እለቄጥሩ” ወይም “ጎበዝ አየን” ይገኙበታል፡፡

ከድል በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ከ1935 እስከ ሕልፈታቸው ድረስ አገልግለዋል፡፡ የመጀመርያው የአማርኛ አጭር ልብ ወለድ እንደሆነ የሚነገርለትን “የጉለሌው ሰካራም” (1941) የደረሱትና ‹‹ሕይወቴ›› የተሰኘው ግለታሪካቸውን ያዘጋጁት አርበኛው አቶ ተመስገን ገብሬ (1901-1941) ስለየካቲት 12 ጭፍጨፋ “የካቲት 12 እና ሊቀጠበብት እውነቱ” የተሰኘ ድርሰትም ማውጣታቸውና በአምስቱ ዓመት የፋሺስት ወረራ ጊዜም በደረሱት ‹‹በለው በለው አትለውም ወይ የጥቁር አንበሳ አይደለህም ወይ›› በሚለው መዝሙራቸውም ይታወሳሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ (1871-1931) ከሥራዎቻቸው ውስጥ “ወዳጄ ልቤ፣ ጥሩ ምንጭ፣ የኢትዮጵያ ታሪክ ከንግሥተ ሳባ እስከ ታላቁ የዓድዋ ድል፣ መጽሐፈ ቅኔ፣ የአፄ ዮሐንስ ታሪክ በአጭሩ›› ይገኙበታል፡፡

አምሳ ሁለት ዓመታትን ያስቆጠረው ኢደማ የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓሉን ከሁለት ዓመት በፊት ሲያከብር የመጀመርያውን የደራስያን መታሰቢያ ቴምብሮች ለወይዘሮ ስንዱ ገብሩ፣ ለአቶ ሐዲስ ዓለማየሁ፣ ለአቶ ከበደ ሚካኤልና ለአቶ ጸጋዬ ገብረ መድኅን ማሳተሙ ይታወሳል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

One thought on “የአራት ደራስያን መታሰቢያ ቴምብሮች ታተሙ

  1. I know that some of the works of Afework GebreYesus and Hiruy WoldeSelassie are available on the market but I don’t know if the works of Yoftahe Negussie and Temsgen Gebre are.I wonder if some one could give me any information about these.Also,has the remarkable Sindu Gebru written any book?

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar