www.maledatimes.com እናንተ ወያኔዎች እንደ ቀትር እባብ መቅበዝበዛችሁን ትታችሁ እንደ ሰው አስቡ! ከፍቅሬ ዘለቀው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

እናንተ ወያኔዎች እንደ ቀትር እባብ መቅበዝበዛችሁን ትታችሁ እንደ ሰው አስቡ! ከፍቅሬ ዘለቀው

By   /   September 9, 2012  /   1 Comment

    Print       Email
0 0
Read Time:11 Minute, 39 Second

የአንባገነኖች ቁንጮና የዘረኞች መሀንድስ መለሰ ዜናዊ ሞት ነሐሴ 14፣ 2004 ዓ ም ይፋ ከተደረገ ጀምሮ የመንግሰቱ አቀንቃኞች፣ ደጋፊዎች፣ ሆድ አደሮች፣ ካድሬዎችና ሹማምንቶች ድንጋጤ ከመጠን ያለፈ ሆኖ እንደታየ ለመታዘብ በቅተናል። እውን ይህ ሁሉ ድንጋጤና መርበትበት እነሱ እንደሚሉት አገሩን የሚወድ፣ አርቆ አሳቢ፣ የልማት መሀንድስ፣ የአፍሪካ አባት፣ ኢየሱስ፣ ወዘተ… የሆነውን ንጉሳቸውን በማጣታቸው ነውን?
መልሱ ግን አይደለም ነው። በሕዝብ አገልጋይነት ስም፣ በጌታቸው አጋፋሪነት የሕዝብን ንብረትና ሀብት በመዝረፍ ያገኙት የነበረው ጥቅም ሲቀር እየታያቸው እንጂ።በጣም የሚያሳዝነው ግን እነሱ ያዘኑትን ያህል፣ ይህን የተራበና በፍትህ እጦት የተሰቃየን የኢትዮጵያ ሕዝብ ከእነሱ ተርታ በግዳጅና በጥቅም አሰልፈው እንዲያለቅስ ማድረጋቸው ሳያንስ አላዘናችሁም፣ የእዝን መዋጮ አላዋጣችሁም፣ የመለስን ካኒታራ አልገዛችሁምና የመሳሰሉትን ምክንያቶች በመፍጠር ማሰቃየታቸው፣ መደብደባቸውና ወደ ዘብጥያ ማጋዛቸው ነው። ከዚህም አልፎ በአቶ መለስ ሞት የተደሰቱትን በስሜታዊነት መግደላቸው፣ በተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች መዘገባቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።
የሀገሪቱ ርዕሰ-ብሔር ቢሞት አንድ የሀዘን ቀን ይታወጃል የሚለውንና ራሳቸው ያረቀቁትን ህገ-መንግሰት በመሻር ድፍን ሰማንያ ስምንት ሚሊዮን ሕዝብን ከሁለት ሳምንታት በላይ ከሥራ አግቶ፣ የቀድሞ መሪያቸውን ተክለ ሰውነት ለመገንባት ሲታክቱ መሰንበታቸው ለሀገርና ለህዝብ ደንታቢስነታቸውን ከማጉላቱም በላይ አቶ መለስ ከሌለ ሕዝቡን በብቃት መምራት የማይችሉ መሆናቸውን ምስክርነት መስጠታቸው እንደሆነ በሕዝባችን ዘንድ መነጋገሪያ ርዕስ ሆኖ የቆየ ቢሆንም እስካሁንም ትረካው ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መስኮት አለመጥፋቱ የሕዝብን የትኩረት አቅጣጫ ከውስጥ የስልጣን ሽኩቻና ችግሮቻቸው ለመቀየር መሆኑ እየታመነበት መጥቷል።
ከዚህም ባሸገር የመማር ማስተማር ሂደቱን በማስትጓጎል መምህራንን በመሰብሰብ ከሁለት ሳምንታት ያላነሰ ስልጠና ሊሰጥ ሽር ጉድ እያሉ እንደሆነ ኢሳት በጳጉሜን

3፣ ዜናው  ጠቁሞናል። የዚህ ሁለት ሳምንት የሥራ እገታ ውጤትና ለዚሁ ዓላማ የወጣው አለስፈላጊና የተሞለቀቁ ወጪዎች እንዲሁም ሌሎች ምክንያቶች ሳቢያ በአሁኑ ሰዓት ሕዝቡ በኑሮ ውድነት እየተጠበሰ ይገኛል።
በአቶ መለስ ሀያ አንድ ዓመታት የግፍ አገዛዝ፣ የሕዝባችን የደም እንባ፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ሲያገኙ ጥሬ ቆርጥመው፣ ሲያጡ ቅጠል በልተው ለሀገራችንና ለሕዝባችን እንዲሁም ለዓለም ደህንነት የሚፀልዩ የዋልድባ አባቶችና እናቶች መነኮሳት እሮሮ፣ የሙስሊም ወገኖቻችን ጥልቅ ሐዘን፣ ፅዋ ሞልቶ ተርፎ በመፍሰሱ ከእግዚያብሔር ፊት ደርሶ በደልን የማይረሳ ሀያል አምላክ ጊዜውን ጠብቆ ሁለት የአመፃ ከያኒያንን ከዚህ የባሰ በደል ሳያመጡ በሚል ዓይነት በሞት ቀጣ እንጂ ብዙሀኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወይም በሌላ አነጋገር ተቃዋሚዎቻቸው ተጠያቂ አይሆኑም።ታዲያ ይህ ሆኖ ሳለ በአቶ መለስ ረጅም የግፍ አገዛዝ ዘመናት የተገረፉትን፣ የተሰቃዩትን፣የታሰሩትን፣ የተሳደዱትን፣ የተገደሉትንና የተፈጁትን ኢትዮጵያንን ለማስታወስና በአንባገነኑ ሞት የተሰማውን ደስታና በዚህም ሳቢያ ሀገራችን መልካም ነገር እንዲገጥማት ከወትሮው በበለጠ በቁርጠኝነት የነፃነታችን ባለቤት ለመሆን ቃል ለመግባት ተሞ በወጣው የዋሽንግተን ሰልፈኛ ኢትዮጵያዊያን ላይ ከፍትህና ከሀገር ጥቅም ይልቅ የግልና የዘረኝነት
በሽታ የተጠናወታቸው በአሜሪካ የሚኖሩ የወያኔ ቅጥረኞች የሚያወርዱት የስድብ ውርጅብኝ በስነ ምግባርና በሐይማኖት ታንፆ በኢትዮጵያ ምድር ካደገ ጨዋ ህብረተሰብ የተገኙ ሳይሆን አሳዳጊ አጥተው ከጎዳና ላይ ተሰብስበው በስድብ ኮሌጅ ውስጥ ተመርቀው የወጡ ይመስሉ ነበር ሲሳደቡ። እጅግ አስነዋሪዎች ናቸው።
እኔ በምኖርበት አገር ኖርዎይም በዚሁ ዕለት ማለትም አምባገነኑ መለስ ዜናዊ ይጠላት በነበረው መሬት ለአንዴና ለመጨረሻ ከነ ዘረኝነት ኮተቱ አፈር በሚለብስበትና ሌሎች ፍትህ ፈላጊ የዋሽንግቶንና ደቡብ አፍሪካ ሰልፈኞች ወንድሞቻችን በተሰለፉበት ነሐሴ 27፣ ቀን 2004 ዓ ም በተመሳሳይ ዓላማ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት እና በኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ ኖርዎይ ቅርንጫፍ አስተባባሪነት ከኦስሎና አካባቢው ሰልፍ የወጣውን ኢትዮጵያዊ በተለመደው ዓይነት ተግባር ለመመረጅ ጥቂት የወያኔ አሸቃባጮች ውርውር ሲሉ ተስተውለዋል። ቀኑን ጥሩ ለብሰው የታዩትን
ኢትዮጵያዊያንንም ከጌታቸው ሞት ስሜት ጋር በማያያዝ ሲሳደቡና ሲተናኮሉ ታይተዋል።
በሀገሬ የፖለቲካና የደሞክራያዊ መብቴ ተጣሰ ብለው በሚኖሩበት አገር የፖለቲካ ጥገኝነት አግንተው ሳለ አሳደደን ላሉት መንግስት ድጋፍና የመረጃ ሥራ መስራት ዓለም አቀፍ የስደተኞች ህግን የመፃረር ወንጀል መሆኑን ዘንግተው አደባባይ ላይ በመውጣት አፀያፊ ሥራ መስራትና እንደቀትር እባብ ወዲያና ወዲህ ሲቅበዘበዙ መታየት አያዋጣምና እረጋ ብላችሁ ለሀገር ደህንነትና እድገት፣ ለሕዝብ ሰላም፣ ፍቅር፣ ፍትህና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ቅድሚያ በመስጠት እንደ ባለ አእምሮ ሰው ቆም ብላችሁ እንዲታስቡ እየመከርን ይህ ካልሆነ የግፉ ቀማሽ ከሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ መዳፍ ውስጥ ገብታችሁ
ለሰራችሁት መንጀል ተጠያቂ ከመሆን የማታመልጡ መሆኑን ልንነግራችሁ እንወዳለን። እግዚያብሔርም የማስተዋል ጥበብ ይሰጣችሁ ዘንድ እንለምናለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
እግዚያብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ!!!
ጳጉሜን 4፣ 2004 (September 9, 2012)
ለአስተያየት ፀሐፊውን በዚህ እሜል ያገኙታል፡ belete_z@yahoo.co.uk

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 9, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 9, 2012 @ 11:03 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

One thought on “እናንተ ወያኔዎች እንደ ቀትር እባብ መቅበዝበዛችሁን ትታችሁ እንደ ሰው አስቡ! ከፍቅሬ ዘለቀው

  1. የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ፡፡

    ከአሰግድ ታመነ [ ኖርዌይ ]

    የቀድሞው የወያኔ መሪና አንባገነኑ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሞተው ተቀብረዋል አፈሩን ድንጋይ ያድርግላቸውና እንዳይነሱ ምን ይታወቃል ተጭበርብሬ ነው ልመለስ ብለው እንዳይመለሱ ፈራው፡፡ እንደሚታወቀው የወያኔውን መሪ በስልጣን ዘመኑ ማለትም ለሁለት አስርተ አመታት በወጣና በገባ ቁጥር ከቤተ-መንግስት እስከ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ድረስ ለመግለፅ በሚያሰቸግር ሁኔታ ስፍራው በአጋዚ እየታጠረ፣ መንገድ ተዘግቶ ነዋሪው እየተዋከበ፣ ከመንገድ ግራና ቀኝ ያሉ ህንፃዎች ማማ ሳይቀር በአልሞ ተዃሽ ተከቦ፣ ህዝብ ጀርባውን ሰጥቶ እንዲቆም ተደርጎ፣ በከፍተኛ ጥበቃ ጥይት በማይበሳው መኪና በከፍተኛ ፍጥነት ሲደርስና ሲመለስ ነበር የምናቀው፡፡ ጊዜ ብዙ ያሳያልና አሁን በጠባብ ሳጥን ውስጥ ሆኖ በግልፅ በአደባባይ ቢሄድም፡፡

    መለስ እራሱን ብቻ አይደለም የገደለው ህወሀትንም ጨምሮ እንጂ በዙርያው የነበሩትን የህዝብ ድጋፍ ያገኛሉ ብሎ ያሰባቸውን ሰዎች ለማጥራትና ብቸኛው መሪ ሆኖ ያለተቀናቃኝ የስልጣን ዘመኑን ለማሳለፍ ባለው ፍላጎት እንደ አየሎም አይ ነቱን ሲገድል ሌሎቹን በጡረታና ከህዝብ ጋር በማያገናኝ ስራ እንዲጠመዱ ሲያደርግ ነበር ። በዚህም ስራው አሁን ላይ ወያኔ ኢሀደግ ብቁ የሚሆን አመራር አጥተውና በስልጣን ይገባናል ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለ መሪ ከሁለት ወራት ለበለጠ ጊዜ ለመቆየት የተገደደችው። እናም ለዝያ ነው መለስ ለኢትዮጵያ ብሎ ሳይሆን ለግል ጥቅሙ ሲል TPLFን የገደለው። ነገ ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም ግን መለስ የራሱን ድርጅት ለስልጣኑ ተቀናቃኝ ያላቸውን ሰዎች በማስወገድ ባዶ አስቀርቶ ሲያጠፋ አሁን ያሉት አይል የሌላቸውና ሀገር አይደለም ቤተሰብ መምራት የማይችሉ ጥረቅምቃሞ ብቻ በመሆናቸው የነገዋን ሀገራችንን ሳያት በጣም ያሳሰበኝ።

    በርግጥ የህወሃት ነባር የአመራር አባላት በዚህ ቀውጢ ወቅት ይከፋፈላሉ ማለት ግን ቲኒሽ የሚያስቸግር ይመስለኛል። ከተከፋፈሉ ቤተመንግስት ውስጥ ማን እንደሚገባ ያውቃሉ። የምኒልክን ቤተመንግስት አንድ ጊዜ ከለቀቁ፣ ዳግም እንደማይመለሱባትም እንደዚሁም እልውናቸው እንደሚያከትም ይረዳሉ። ስለዚህ ወያኔ ህወሃት የስልጣን የበላይነታቸውን ማስጠበቅ የመጀመሪያ እቅዳቸው ስለሆነ ባብዛኛውም ከፍተኛ አመራር ላይ ያሉት እንደ መከላከያ ፌደራል ፖሊስ የደህንነት ቦታዎችን የተቆጣጠሩት ወያኔ ህወሃት በቀላሉ የጠቅላይ ሚንስትሩን ቦታ ለም/ ጠ /ሚ አቶ አይለማርያም ደሳለኝ አሳልፎ የሚሰጡ አይሆንም። በዚህም ምክንያት ነው እስካሁን ጠ/ሚ መሾም ያቃታቸው። እንድያውም ከመቼውም በላቀ አንድ ሆነው ይታገላሉ እንጂ ህወሃት ወያኔ ተከፋፍሎ ትርምስ ውስጥ እንደሚገባ መጠበቅ የዋህነት ይመስለኛል ።

    ም/ጠ/ሚ አቶ አይለማርያም ደሳለኝ የደህዴን ፕሬስዳንት ሆኖ ከ2002-2005 የሰራ ሲሆን በአቅም ማነስ ከፍተኛ ተቃውሞ በሲዳማ ህዝብ ሲደርሰበት አቶ መለስ ከቦታው አስነስተው
    በ2005 የጠ/ሚንስትሩ አማካሪ ተብሎ በSocial Affairs and Civic Organizations and Partnerships ለሁለት ዐመት አስቀምጠውት ነበር ። ታዲያ ይህ ሰው ከፍተኛ የስራ ለምድ የሌለው ከመሆኑም ባሻገር ሌሎቹ የቀድሞው የወያኔ አመራር አባላት ሊታዘዙትና ሊያከብሩት አይችሉም እናም እንዴት ብሎ አገር ሊመራ ይችላል በዝያ ላይ የመጀመርያው የፕሮቴስታንት መሪ በዚህም ላይ ጥያቄ ቢኖረኝም። ያለመሪ መጪውን አዲስ አመት የምተቀበለው አገራችን ባለስልጣኖችዋ ከህዝብ መሪ ይልቅ የፓርቲ መሪ ሰላሳሰባቸው የህወህትና የኢሀዴግ መሪ ለመምረጥ ቀጠሮ ይዘዋል። እንደምናውቀው የጋናው ፕሬዝዳንት ከመቀበራቸው በፊት ነበር ም/ጠ/ሚ የሳቸውን ቦታ ተክትው እንዲሰሩ ቃለመሃላ የፈፅሙት የሀገር ጉዳይ የሚያንገበግባቸው በፍትህና በዲሞክራስያዊ አሰራር የሚያምኑ ቅድሚያ በመስጠት እንደተንቀሳቀሱት ጋናዎች ትምህርት እንክዋን ሊሆኑን ሲገባ የኛዎቹ ለፓርቲያቸው በመጨነቀ እንደ ቀድሞው ሱማሊያ ያለመሪ አስቀርተውናል ።

    በሀገራችን በኢትዮጵያ ከፓለቲካ ጨዋታ ባለፈ የግል ጥቅምና ዘረኝነት የሌለበት አርቆ አሳቢና ቅን መሪ በማጣት ለዘመናት በረሀብ በድህነት ስሟ ከሀለም የመጀመሪያውን ቦታ እንደያዘች አለች። የመለስ አንባገነናዊው አገዛዝ በሱ ሞት ብቻ ተወስኖ ሳይቀር የሁሉም ፓርቲዎች መቻቻልና መግባባት ታክሎበት መሰረታዊ ለውጥ ካላመጣ በስተቀር ወያኔዎች እንደሚሉት የመለስን ፖሊሲ ተከትለን እናስፈፅማለን የሚባል ከሆነና የህዝቡ ነፃንት እንደተረገጠ ዲሞክራሳዊ መብቱ እንደተጣሰ በአንድ ዘር የበላይነት የሚመራና በዚያው የሚቀጥል ከሆነ መለስን ሞተ ለማለት ይከብዳል ስሙን ቀይሮ መጣ ከማለት ውጪ። እስከዝያው ግን ሁላችንም ባለንበት ቦታ እያደረግን እንዳለነው ትግላችንን በተናጠል ሳይሆን በአንድነት በመለያይት ሳይሆን በመግባባት ልዩነታችንን አስወግደን ለምንወዳት ሀገራችን የተሻለ ጊዜ እንፍጠርላት ዘንድ …. አሜን ።

    ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ፤፤፤

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar