www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ፡፡ ከአሰግድ ታመነ [ ኖርዌይ ] - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ፡፡ ከአሰግድ ታመነ [ ኖርዌይ ]

By   /   September 10, 2012  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ፡፡ ከአሰግድ ታመነ [ ኖርዌይ ]

    Print       Email
0 0
Read Time:10 Minute, 1 Second

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከድጡ ወደ ማጡ፡፡
ከአሰግድ ታመነ [ ኖርዌይ ]

የቀድሞው የወያኔ መሪና አንባገነኑ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሞተው ተቀብረዋል አፈሩን ድንጋይ ያድርግላቸውና እንዳይነሱ ምን ይታወቃል ተጭበርብሬ ነው ልመለስ ብለው እንዳይመለሱ ፈራው፡፡ እንደሚታወቀው የወያኔውን መሪ በስልጣን ዘመኑ ማለትም ለሁለት አስርተ አመታት በወጣና በገባ ቁጥር ከቤተ-መንግስት እስከ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ድረስ ለመግለፅ በሚያሰቸግር ሁኔታ ስፍራው በአጋዚ እየታጠረ፣ መንገድ ተዘግቶ ነዋሪው እየተዋከበ፣ ከመንገድ ግራና ቀኝ ያሉ ህንፃዎች ማማ ሳይቀር በአልሞ ተዃሽ ተከቦ፣ ህዝብ ጀርባውን ሰጥቶ እንዲቆም ተደርጎ፣ በከፍተኛ ጥበቃ ጥይት በማይበሳው መኪና በከፍተኛ ፍጥነት ሲደርስና ሲመለስ ነበር የምናቀው፡፡ ጊዜ ብዙ ያሳያልና አሁን በጠባብ ሳጥን ውስጥ ሆኖ በግልፅ በአደባባይ ቢሄድም፡፡

መለስ እራሱን ብቻ አይደለም የገደለው ህወሀትንም ጨምሮ እንጂ በዙርያው የነበሩትን የህዝብ ድጋፍ ያገኛሉ ብሎ ያሰባቸውን ሰዎች ለማጥራትና ብቸኛው መሪ ሆኖ ያለተቀናቃኝ የስልጣን ዘመኑን ለማሳለፍ ባለው ፍላጎት እንደ አየሎም አይ ነቱን ሲገድል ሌሎቹን በጡረታና ከህዝብ ጋር በማያገናኝ ስራ እንዲጠመዱ ሲያደርግ ነበር ። በዚህም ስራው አሁን ላይ ወያኔ ኢሀደግ ብቁ የሚሆን አመራር አጥተውና በስልጣን ይገባናል ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለ መሪ ከሁለት ወራት ለበለጠ ጊዜ ለመቆየት የተገደደችው። እናም ለዝያ ነው መለስ ለኢትዮጵያ ብሎ ሳይሆን ለግል ጥቅሙ ሲል TPLFን የገደለው። ነገ ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም ግን መለስ የራሱን ድርጅት ለስልጣኑ ተቀናቃኝ ያላቸውን ሰዎች በማስወገድ ባዶ አስቀርቶ ሲያጠፋ አሁን ያሉት አይል የሌላቸውና ሀገር አይደለም ቤተሰብ መምራት የማይችሉ ጥረቅምቃሞ ብቻ በመሆናቸው የነገዋን ሀገራችንን ሳያት በጣም ያሳሰበኝ።

በርግጥ የህወሃት ነባር የአመራር አባላት በዚህ ቀውጢ ወቅት ይከፋፈላሉ ማለት ግን ቲኒሽ የሚያስቸግር ይመስለኛል። ከተከፋፈሉ ቤተመንግስት ውስጥ ማን እንደሚገባ ያውቃሉ። የምኒልክን ቤተመንግስት አንድ ጊዜ ከለቀቁ፣ ዳግም እንደማይመለሱባትም እንደዚሁም እልውናቸው እንደሚያከትም ይረዳሉ። ስለዚህ ወያኔ ህወሃት የስልጣን የበላይነታቸውን ማስጠበቅ የመጀመሪያ እቅዳቸው ስለሆነ ባብዛኛውም ከፍተኛ አመራር ላይ ያሉት እንደ መከላከያ ፌደራል ፖሊስ የደህንነት ቦታዎችን የተቆጣጠሩት ወያኔ ህወሃት በቀላሉ የጠቅላይ ሚንስትሩን ቦታ ለም/ ጠ /ሚ አቶ አይለማርያም ደሳለኝ አሳልፎ የሚሰጡ አይሆንም። በዚህም ምክንያት ነው እስካሁን ጠ/ሚ መሾም ያቃታቸው። እንድያውም ከመቼውም በላቀ አንድ ሆነው ይታገላሉ እንጂ ህወሃት ወያኔ ተከፋፍሎ ትርምስ ውስጥ እንደሚገባ መጠበቅ የዋህነት ይመስለኛል ።

ም/ጠ/ሚ አቶ አይለማርያም ደሳለኝ የደህዴን ፕሬስዳንት ሆኖ ከ2002-2005 የሰራ ሲሆን በአቅም ማነስ ከፍተኛ ተቃውሞ በሲዳማ ህዝብ ሲደርሰበት አቶ መለስ ከቦታው አስነስተው
በ2005 የጠ/ሚንስትሩ አማካሪ ተብሎ በSocial Affairs and Civic Organizations and Partnerships ለሁለት ዐመት አስቀምጠውት ነበር ። ታዲያ ይህ ሰው ከፍተኛ የስራ ለምድ የሌለው ከመሆኑም ባሻገር ሌሎቹ የቀድሞው የወያኔ አመራር አባላት ሊታዘዙትና ሊያከብሩት አይችሉም እናም እንዴት ብሎ አገር ሊመራ ይችላል በዝያ ላይ የመጀመርያው የፕሮቴስታንት መሪ በዚህም ላይ ጥያቄ ቢኖረኝም። ያለመሪ መጪውን አዲስ አመት የምተቀበለው አገራችን ባለስልጣኖችዋ ከህዝብ መሪ ይልቅ የፓርቲ መሪ ሰላሳሰባቸው የህወህትና የኢሀዴግ መሪ ለመምረጥ ቀጠሮ ይዘዋል። እንደምናውቀው የጋናው ፕሬዝዳንት ከመቀበራቸው በፊት ነበር ም/ጠ/ሚ የሳቸውን ቦታ ተክትው እንዲሰሩ ቃለመሃላ የፈፅሙት የሀገር ጉዳይ የሚያንገበግባቸው በፍትህና በዲሞክራስያዊ አሰራር የሚያምኑ ቅድሚያ በመስጠት እንደተንቀሳቀሱት ጋናዎች ትምህርት እንክዋን ሊሆኑን ሲገባ የኛዎቹ ለፓርቲያቸው በመጨነቀ እንደ ቀድሞው ሱማሊያ ያለመሪ አስቀርተውናል ።

በሀገራችን በኢትዮጵያ ከፓለቲካ ጨዋታ ባለፈ የግል ጥቅምና ዘረኝነት የሌለበት አርቆ አሳቢና ቅን መሪ በማጣት ለዘመናት በረሀብ በድህነት ስሟ ከሀለም የመጀመሪያውን ቦታ እንደያዘች አለች። የመለስ አንባገነናዊው አገዛዝ በሱ ሞት ብቻ ተወስኖ ሳይቀር የሁሉም ፓርቲዎች መቻቻልና መግባባት ታክሎበት መሰረታዊ ለውጥ ካላመጣ በስተቀር ወያኔዎች እንደሚሉት የመለስን ፖሊሲ ተከትለን እናስፈፅማለን የሚባል ከሆነና የህዝቡ ነፃንት እንደተረገጠ ዲሞክራሳዊ መብቱ እንደተጣሰ በአንድ ዘር የበላይነት የሚመራና በዚያው የሚቀጥል ከሆነ መለስን ሞተ ለማለት ይከብዳል ስሙን ቀይሮ መጣ ከማለት ውጪ። እስከዝያው ግን ሁላችንም ባለንበት ቦታ እያደረግን እንዳለነው ትግላችንን በተናጠል ሳይሆን በአንድነት በመለያይት ሳይሆን በመግባባት ልዩነታችንን አስወግደን ለምንወዳት ሀገራችን የተሻለ ጊዜ እንፍጠርላት ዘንድ …. አሜን ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ፤፤፤

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 10, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 10, 2012 @ 12:55 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar