www.maledatimes.com 41 አለማቀፍ ድርጅቶች የታሰሩት ጋዜጠኞችና ጦማርያን በአፋጣኝ እንዲፈቱ ጠየቁ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

41 አለማቀፍ ድርጅቶች የታሰሩት ጋዜጠኞችና ጦማርያን በአፋጣኝ እንዲፈቱ ጠየቁ

By   /   August 1, 2014  /   Comments Off on 41 አለማቀፍ ድርጅቶች የታሰሩት ጋዜጠኞችና ጦማርያን በአፋጣኝ እንዲፈቱ ጠየቁ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 43 Second
የጸረ ሽብርተኝነት ህጉ ይሻሻል ብለዋል  ከዚህ በፊት በሽብርተኝነት የተፈረደባቸው  እንዲፈቱ ጠይቀዋል 41 የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የፕሬስ ነጻነት  አቀንቃኞች፣ አለማቀፍና ክልላዊ የሲቪል
ማህበረሰብ ተቋማትና የሙያ ማህበራትመንግስት በቅርቡ የሽብርተኝነት ክስ  የመሰረተባቸውን ጋዜጠኞችና የዞን 9 ጦማርያን  በአፋጣኝ እንዲፈታ ለጠቅላይ ሚኒስትር
ሃይለማርያም ደሳለኝ ከትናንት በስቲያ በላኩት  ደብዳቤ መጠየቃቸውን ብሉምበርግ ኒውስ  ዘገበ፡፡
ሂዩማን ራይትስ ዎች፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ አርቲክል 19 ምስራቅ አፍሪካ፣ ሲቪል ራይትስ  ዲፌንደርስ፣ ወርልድ አሊያንስ ፎር ሲቲዝን  ፓርቲሲፔሽን፣ ፔን አሜሪካና የመሳሰሉት
አለማቀፍ ድርጅቶች በጋራ በጻፉት ደብዳቤ፣ መንግስት ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን  በሽብርተኝነት እየከሰሰ ለእስር መዳረጉን  መቀጠሉ ያሳስበናል፣ እየተወሰደ ያለው እርምጃ  ተገቢነት የሌለው በመሆኑ መገታት ይኖርበታል  ብለዋል፡፡
ሶስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማርያን ሶስት
ወራት ለሚሆን ጊዜ ይህ ነው የሚባል ክስ
ሳይመሰረትባቸው ያለአግባብ በእስር ላይ
መቆየታቸውንና አንዳንዶቹም በምርመራ ወቅት
እንግልት እንደደረሰባቸው መናገራቸውን
የጠቀሰው ደብዳቤው፣ ይህም አግባብ
አለመሆኑን ገልጿል፡፡
ጋዜጠኞቹና ጦማርያኑ በተመሰረተባቸው
የሽብርተኝነት ክስ በረጅም አመታት እስር ብሎም
በሞት ሊቀጡ እንደሚችሉ ስጋታቸውን የገለጹት
ድርጅቶቹ፤ ይህም አለማቀፍ ህጎችን የሚጥስና
በቀጠናው የተረጋጋ ሰላምና ደህንነት ለመፍጠር
የሚደረገውን አለማቀፍ ጥረት ዋጋ የሚያሳጣ
እርምጃ ይሆናል ብለዋል፡፡
መንግስት አግባብነት በሌለው የጸረ ሽብርተኝነት
ህግ በቁጥጥር ውስጥ አውሎ ክስ
የመሰረተባቸውን ጋዜጠኞችና ጦማርያን
በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቅ አስፈላጊውን ሁኔታ
እንዲያመቻቹ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም
ጥያቄ ያቀረቡት እነዚህ ድርጅቶች፤ ከዚህ በፊት
በተመሳሳይ ሁኔታ በጸረ ሽብር ህጉ ተከሰው
የተፈረደባቸው ዜጎች ጉዳይ አግባብ አለመሆኑን
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሳይቀር
እንዳመነበትና እንዳወገዘው አስታውሰዋል፡፡
ከጋዜጠኞቹና ከጦማርያኑ በተጨማሪም፣ ከዚህ
በፊት በሽብርተኝነት ተከሰውና ተፈርዶባቸው
ያለአግባብ በእስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን
በሙሉ መንግስት በአፋጣኝ እንዲፈታና የጸረ
ሽብርተኝነት ህጉንም አለማቀፍ የሰብዓዊ
መብቶች መስፈርቶችን በሚያሟላ መልኩ
እንደገና አሻሽሎ እንዲያጸድቅ ጠይቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ የአለማቀፉ የሲቪልና የፖለቲካ
መብቶች ስምምነትና የአፍሪካን የሰብዓዊና
የህዝብ መብቶች ኮንቬንሽን ፈርማ የተቀበለች
ሃገር እንደመሆኗ፣ መንግስት አለማቀፍ ህጎች
የጣሉበትን ግዴታ በማክበር መሰረታዊ
መብቶቻቸው ተጥሰው ለእስር የተዳረጉ ዜጎችን
በሙሉ ከእስር እንዲለቅ ጠይቀዋል፡፡
ደብዳቤውን የጻፉት ድርጅቶች የሚከተሉት
ናቸው፡፡
1. Amnesty International
2. ARTICLE 19 Eastern Africa
3. Central Africa Human Rights
Defenders Network (REDHAC), Central
Africa
4. CIVICUS: World Alliance for Citizen
Participation
5. Civil Rights Defenders, Sweden
6. Coalition pour le Développement et
la Réhabilitation Sociale (CODR
UBUNTU), Burundi
7. Committee to Protect Journalists
8. Community Empowerment for
Progress Organization (CEPO), South
Sudan
9. Conscience International (CI), The
Gambia
10. East and Horn of Africa Human
Rights Defenders Project
11. Egyptian Democratic Association,
Egypt
12. Electronic Frontier Foundation
13. Ethiopian Human Rights Project
(EHRP)
14. Elma7rosa Network, Egypt 15.
English PEN
16. Freedom Now
17. Front Line Defenders, Dublin 18.
Human Rights Watch
19. International Women’s Media
Foundation (IWMF)
20. Ligue des Droits de la personne
dans la region des Grands Lacs
(LDGL), Great Lakes
21. Ligue Iteka, Burundi
22. Maranatha Hope, Nigeria
23. Media Legal Defence Initiative
24. National Civic Forum, Sudan
25. National Coalition of Human Rights
Defenders, Kenya
26. Niger Delta Women’s movement
for Peace and Development, Nigeria
27. Nigeria Network of NGOs, Nigeria
28. Paradigm Initiative Nigeria, Nigeria
29. PEN American Center 30. PEN
International
31. Réseau africain des journalistes
sur la sécurité humaine et la paix
(Rajosep), Togo
32. Sexual Minorities Uganda (SMUG),
Uganda
33. South Sudan Human Rights
Defenders Network (SSHRDN), South
Sudan
34. South Sudan Law Society, South
Sudan
35. Tanzania Human Rights Defenders
Coalition, Tanzania
36. Twerwaneho Listeners Club (TLC),
Uganda
37. Union de Jeunes pour la Paix et le
Développement, Burundi
38. WAN-IFRA (The World Association
of Newspapers and News Publishers)
39. West African Human Rights
Defenders Network (ROADDH/
WAHRDN), West Africa
40. Zambia Council for Social
Development (ZCSD), Zambia
41. Zimbabwe Human Rights NGO
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on August 1, 2014
  • By:
  • Last Modified: August 1, 2014 @ 3:53 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar