www.maledatimes.com አይደለም ደም እንባ ሳይፈስ አለፈ፡፡ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አይደለም ደም እንባ ሳይፈስ አለፈ፡፡

By   /   August 25, 2014  /   Comments Off on አይደለም ደም እንባ ሳይፈስ አለፈ፡፡

    Print       Email
0 0
Read Time:52 Second

እግዚአብሄር ይመስገን አይደለም ደም  እንባ ሳይፈስ አለፈ፡፡
በፍርሃት ያሳለፍናት አርብ
ፀሐይ በየነ
ሶስትና አራት አመታትን ያስቆጠረው የአረብ ሀገሩ ቀውስ ይኸው ዛሬም እንዳለ አለ፡፡ከቱኒዝያ ተነስቶ ሊቢያን፣ግብፅን፣ሶሪያን ብሎም በየመን የተነሳው የፖለቲካ ቀውስ የብዙ ሺህ ንፁሃን ዜጎቸን ህይወት የቀጠፈ፣ ያቆሰለ በብዙዎች መጥፎ የህሊና ጠባሳ የጣለ፣የአለም ፍፃሜ ቀርበ ተብሎ ህዝብ በህብረት ወደ ፈጣሪ እግዚኦታን ያሰማበት ወቅት ሆነ፡፡
አንዴ ጋብ አንዴ ደግሞ ናር የሚለው ይህ አረቡ ሀገሩ ጦርነት እሳቱ ጨርሶ የሚጠፋው መች እንደሆነ አሳሳቢ ሆኗል፡፡ታድያ በዚሁ እኔ ባለሁበት የአረብ ሀገሯ የመንም የእሳቱን መጥፍያ በመጠበቅ በሰቀቀን አለን፡፡ በየመን የማይፈልጉት ወርዶ የሚፈልጉት ስልጣን ላይ ቢወጣም አልዋጥ ብሎ ከጎሮሮአቸው ተሰንቅሮ ይተነናቃቸዋል፡፡
አልዋጥ ብሎ ከጎሮሮ ተሰንቅሮ ያለውን ባለስልጣን ፍላጎታቸው ምን እንደሆነ ለማሳማት በሚወጡ ሰልፈኞች፣ ሰልፈኞቹ በሚያሰማቸው ድምፅና በከሴት በተቀዱ የተቃውሞ መዝሙሮች መንገዶቿ ዘውትር ደምቀው ይውላሉ፡፡
በእነዚህ ቀናት እኛም መንገድ ላይ ሰልፈኞቹ ከገጠሙን ስለማንቀላቀል መዝሙሩ ከጆሮ እሰኪር ይኮመኮምን በአይን የተወሰነ መንገድ እንሸኛለን ሰልፉ ምንም ችግር ስለሌለበት፡፡ የትላትናው አርብ ግን ትንሽ አስፈሪ ነበረች፡፡ ተቃውሞ አሰሚዎቹ የሚፈልጉትን ነገሮች በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ካላስተከለ ከፍተኛ የደም መፋሰስ እንደሚኖር ስለታገሩ በፍርሃት አኮራምታ አውላናለች፡፡
ግን እግዚአብሔር ይመስገን አይደለም ደም እንባ ሳይፈስ አለፈ፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on August 25, 2014
  • By:
  • Last Modified: August 25, 2014 @ 8:57 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar