www.maledatimes.com የሙስሊሞች ጥያቄ አሁንም ቀጥሎአል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሙስሊሞች ጥያቄ አሁንም ቀጥሎአል

By   /   September 21, 2012  /   Comments Off on የሙስሊሞች ጥያቄ አሁንም ቀጥሎአል

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 35 Second

ላለፈው አንድ ወር አካባቢ የጠቅላይ ሚኒስትሩ “ግባተ መሬት” እስኪፈፀም ድረስ እንዲሁም መንግስት ሀዘኑ በረድ እስኪልለት እና ለቀስተኛ እንግዶች እስኪሸኙ በሚል ጋብ ብሎ የነበረው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ጥያቄ በዛሬው ዕለት በርካታ አማኞች በተገኙበት በአንዋር መስጊድ ተከናውኗል።

ሙስሊም ኢትዮጵያውያኖቹ በዛሬው የተቃውሞ ውሏቸው የታሰሩ በርካታ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እና ኡስታዞች እንዲፈቱ እንዲሁም በቀበሌዎች ሊደረግ የታሰበው የመጅሊስ ምርጫ ዕውቅና የማይሰጡት መሆኑን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ገልፀዋል።

ልብ አድርጉልኝ 1

አነዚህን ወንድሞቻችንን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቅሶ ቀለል እኪል ብለው የወሰዱት የስክነት እርምጃ የሚደነቅ ነው። እነዚህን ወንድሞች ነው እንግዲህ መንግስት ባለፈው ግዜ “ሆን ብላችሁ የአፍሪካ ህብረት ስብሰባን ለማወክ አስባችኋል” ብሎ በአስለቃሽ ጭስ እና በአስለቃሽ ዱላ እየዬ ሲያስብላቸው የነበረው። ታድያ ብዙ መራቂ አባቶች አሉን አይደል እንዴ “እንዳስለቀሳችሁን እርሱ ያስለቅሳችሁ” ብለው መንግስታቸውን መረቁ… አፍታም አልቆየ ወድያውኑ የመንግስት ዋና ዋና ሰዎች እየዬ አሉ።

ልብ አደርጉልኝ 2

አሁንም ብዙሃኑን ጥቂት ማለት አደጋው ብዙ ነው። እናም መስማት ይበጃል። አለበለዛ ማለቅስ ይመጣል… “ጥንቱን ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማለቀስ” ይል ነበር አባቴ… እናም የመንግሰት ዋና የስራ ሂደት ባለቤቶች ሆይ እባካችሁ መጥናችሁ ደቁሱ…!

የቃላት መፍቻ

በዚህ ወግ አግባብ “መደቆስ” ተብሎ የተገለፀው ችግሮችን ለመፍታት የሚደረግ የሰለጠነ ዘዴ ነው። እደግመዋለሁ መንግስታችን ሆይ አሁንም ባለችው ጊዜ እባክህ መጥነህ ደቁስ…!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 21, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 21, 2012 @ 11:07 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar