www.maledatimes.com የጉራማይሌ አሳታሚ የህትመት ስራዎች ሲታወስ (ሚሊዮን ሹርቤ ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የጉራማይሌ አሳታሚ የህትመት ስራዎች ሲታወስ (ሚሊዮን ሹርቤ )

By   /   October 16, 2014  /   Comments Off on የጉራማይሌ አሳታሚ የህትመት ስራዎች ሲታወስ (ሚሊዮን ሹርቤ )

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 25 Second

በጉራማይሌ አሳታሚ ድርጅት እየታተሙ የሚያቀቧቸው የኪነጥበባዊም ሆነ ማህበረሰባዊ እንዲሆም የፖለቲካም ይሁን የፋሽን ስራዎችን በትልቁ ጉልህ ቦታ ላይ ስራዎቻቸው እንዲቀመጡ ረድቶአቸዋል ።  ለዚህም ትልቁ ዋጋ በማራኪ ዋና አዘጋጅ አሻራ ተጥሎባቸዋል ። በይርጋጨፌ ያደገው ሚሊዮን ሽርቤ የዋዛ ሰው አልነበረም ፣የስነጽሁፍ ብስለቱም ከፍተኛ እና የነጥሩ ነበሩ ታዲያ  የማራኪ መጽሄት አዘጋጅ እና ባለቤት የነበረው ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹርቤ ስደትን በጀመረ በአንድ ወር ከ ስድስት ቀኑ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል ።

ከትውልድ ሃገሩ ከመሰደዱ በፊት ከማለዳ ታይምስ አዘጋጆች ጋር በነበረው የጥብቅ ወዳጅነት በየጊዜው ይሰራቸው የነበሩትን የመጽሄት ይዘቶች በኤሌክትሮኒክስ የመላኪያ መንገድ እያያዘ ይልክላቸው ነበር ።  ሆኖም የዚያን ደግ ጊዜ ጠበቀ ወዳጅነታቸውን ዛሬ በድንገት ሲለያቸው የተሰማቸው ስሜት የባዶነት ስሜት እንደሆነ ህብረተሰብ እንዲያውቀው ለመረዳት ያህል ቢገለጽም አሟሟቱ በስደት ላይ ያለ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ልብ የነካ እንደሆነ ለማወቅ ተችሎአል ። ታዲያ በተለያዩ ቦታዎች ሆነው ይህንን ወጣት እና ታታሪ በብእሮቹ የሰሉ ትችቶችንም ሆነ ምክሮችን አስተማሪ የሆን ቁምነገሮችን ሲያቀርብ የነበው ወጣት  በሞት ክፋት መለየት ከልብ አዝነው የበኩላቸውን ለማድረግ የጣሩ እንዲሁም ለተቀሩት 26ጋዜጠኞችን ማለትም በኬንያ በኡጋንዳ እና እንዲሁም በየመን ተሰደው ችግርን በመግፋት ላይ ለሚገኙት ሁሉ የበኩላችሁን አስተዋእጾ ለማድረግ ጥረት እያደረጋችሁ ላላችሁት መልካም ወገኖች እኛም ለምታደርጉልን ጥረት ሁሉ ከልብ እናመሰግናለን በማለት የስራ ባልደረቦቻችንን ድምጽ ከፍ አድርገንእናሰማለን ።

ይህም ድጋፋችሁ ቀጣይነት ባለው መንገድ ቢሆን እና እያንዳንዱ ግለሰብ በሚችለው አቅሙ ካሉት ጋዜጠኖች በነፍስ ወክፍ አንድ ሰው በወር በመርዳት ህይወታቸውን መታደግ ቢችሉ እናም ድስታውን እጥፍ ድርብ ሊሆንልን ይችላል ብለን እንገምታለን ታዲያ ህዝብን ለማገልገል ብለው እራሳቸውን በስራቸው አማካይነት መስዋእትነትን እንዲከፍሉ የተደረጉትን እነዚህን ንጹሃን ጋዜጠኞችን መታደግ ይሳነን ይሆን ብለን እራሳችንን እንድንጠይቅ ይረዳናል ለዚህም ምላሹ እኛው ጋር አለ ብለንም ልናገኝ ስለምንችል ብናስብበት መልካም ነው እያልን ዛሬ እንደ መረጃነት የጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹርቤ ከሆኑት ስራዎች መካከል አንደኛዋን አንቀጽ ከማህደራችን ላይ አግኝተነዋል እና እኛም ለእናንተ እናካፍላችሁ ዘንድ ወደድን ስለዚህ ሚሊዮንን ሳታቁት ለተለያችሁ ሁሉ ስራዎቹ ግን ዝንት አለም ከእናንተ ጋር ይኖር ዘንድ አንዷን ህትመት እነሆ እንበላችሁ

https://www.dropbox.com/s/804pq7fjberbmvo/Maraki%2037.zip?dl=0

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on October 16, 2014
  • By:
  • Last Modified: October 17, 2014 @ 1:22 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar