www.maledatimes.com የውያኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልኡካን ብድን በኖርዌይ ኦስሎ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማችው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የውያኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልኡካን ብድን በኖርዌይ ኦስሎ  ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማችው

By   /   October 17, 2014  /   Comments Off on የውያኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልኡካን ብድን በኖርዌይ ኦስሎ  ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማችው

    Print       Email
0 0
Read Time:55 Second

የኖርዌይ አፍሪካ የንግድ ማህበር በኦክቶበር 16, 2014  ባዘጋጀው ሴሚናር ላይ ለመካፈል በማህበሩ  ተጋባዠ በመሆን ወደ ኖርዌይ የመጡ የውያኔ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቲዮድሮስ አድሃኖም  እና በስዊዲን የኢትዮጲያ  አምባሳደር የሆኑት ወይንሽት ታደስ እንዲሁም  ሌሎች ተላላኪ የወያኔ ባለ ስልጣናት በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በተጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ፣ በኖርዌይ ኦስሎ እና በአካባቢው የሚኖሩ የድርጅቱ አባሎችና ደጋፊዎች በተገኙበት ታላቅ ተቃውሞ  ገጠማችው::

በስፍራው ቁጣቸውን ለማሰማት ቁጥራችው በርከት ያሉ ኢትዮጲያውያኖች ከጠዋቱ 7 ስአት ጀምሮ በግዜው የነበረው የወቅቱ ዝናብና ብርድ ሳይበግራችው ከልማት በፊት ስብአዊ መብት ይከበር በሚል መሪ ቃል ሴሚናሩ በተደረገበት አዳራሽ ፊት ለፊት በመገኘት የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ቁጣቸውን ገልጸዋል ::

በጊዜው የነበረው የተቃዋሚዎች ብዛትና  ቁጣን የተቀላበት ተቃውሞ  ያሰጋው የኖርዌይ ፖሊስ በርካታ የፓሊስ ሀይልን ብማ ስማርት እና አካባቢውን በመዝጋት  ተቃውማውን ለመግታት ሲምክሩ ታይተዋል።

በተጨማሪም ሴሚናሩን ያዘጋጀው አካል ከተቃውሞ አስተባባሪ ጊዚያዊ ግብረሃይል የቀረበውን ተደጋጋሚ ጥያቄ ለመቀበል  ፈቃደኛ ባልመሆናችው በዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጲያ  ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በተወካዩ አማካኝነት ለኖርዌይ የንግድ ማህበር የመረጃ  ክፍል ሃላፊ ለሆኑት  ለሚተር ሩነ  አስረክበዋል ።

በመጨረሻም ተቃውሞዋችውን ሲገልጥጹ የነበሩ ኢትዮጲያውያኖች ተቃውሞዋችው በዚሁ ሳይገታ በሴሚናሩ ላይ ራሳችውን ስውረው ሲሳተፉ የነበሩ የወያኔ ልኡካን አባላት በድብቅ ወደ ማረፊያ ሆቴላችው ሲያመሩ ለተቃውሞ ተዘጋጅተው በነበሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጲያውያኖች ቁጣችውን እንቁላል በመወርወር ውርደትን  አከናንበዋቸዋል   view

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on October 17, 2014
  • By:
  • Last Modified: October 17, 2014 @ 10:26 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar