www.maledatimes.com የበረከት አዜብና የስብሃት ፍጥጫ ከ ኢየሩሳሌም አርአያ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የበረከት አዜብና የስብሃት ፍጥጫ ከ ኢየሩሳሌም አርአያ

By   /   September 22, 2012  /   1 Comment

    Print       Email
0 0
Read Time:16 Minute, 22 Second
                 
 በሽማግሌው ስብሀት ነጋና በረከት ስምኦን መካከል ስር ሰዶ የቆየው የውስጥ ሽኩቻ እየከረረ ሔዶአል ።አዜብ መስፍን ከበረከት ጎን ተሰልፈዋል።አዜብ ለፓርቲው ሊቀምንበርነት «ይመጥናሉ» ያሉዋቸውንና «መለስን ይተካሉ» ሲሉ በድፍረት የተሟገቱላቸው ሁለት አመራር አባላት ተቀባይነት አለማግኘታቸው አበስጭቶአቸዋል። አዜብ የጠ/ሚ/ር እንዲሆኑ የተሟገቱላቸው ቴዎድሮስ አድሀኖም ከእጩነት ራሳቸውን በማግለል ኩም አድርገዋቸዋል።
         ሕወሀትን ከጀርባ በማሽከርከር የሚታወቁት ስብሀት ነጋ ለቀጣዩ ፍልሚያ ሀይል እያደራጁ ነው። ለበረከት ያላቸው ጥላቻ-ንቀት ጭምር የተላበሰ ነው። አዜብን ለመበቀል ግዜው አሁን እንደሆነ አረጋግጠዋል።የስብሀትና አዜብ ቁርሾ የተጠነሰሰው ከአምስት አመት በፊት ነበር። በወቅቱ የተወሰኑ የህውሀት ማ/ኮሚቴ አመራሮችን የሰበሰቡት አዜብ«ስብሀት ከኤፈርት ሃላፊነቱ መነሳት አለበት » ይላሉ። ትእዛዙን የተቀበሉት እነቴዎድሮስ  ሀጎስ መልእክቱን ለሽማግሌው ያደርስሉ። ስብሀትም በቁጣ«ጉአል ጎላ ክትቅመጠሉ ድያ?ሞይተ ድየ ብደወይ?» ማለትም «የጎላ ልጅ ልትቀመጥበት ነው? ሞቼ ነው በቁሜ?» ነበር ያሉት። «የሚስቱን ትእዛዝ ሳያወላዳ ተግባራዊ ያደርጋል» ሲሉ በገረሜታ የሚገልጹአቸው መለስ በወቅቱ በአዜብ የቀረበውን ስብሀት  ነጋን የማስነሳት ሀሳብ ከመተግበር ወደሁዋላ አላሉም።
«ፉከራ»ብቻ ሆነው የቀሩት ሽማግሌው ከኤፈርት፣በሁዋላም ከፓርቲው አመራር እንዲወጡ በማድረግ አዜብ የበላይነታቸውን አሳዩ። ስብሀት ነጋ ከስልጣን ከተነሱ በሁዋላ  የባልና ሚስቱን ስም እየጠቀሱ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ከማውገዝ አልቦዘኑም። አዜብ ከሽማግሌው አልፈው «ታማኝ» የተባሉ ጄኔራሎችን ሳይቀር ከሀላፊነት እንዲወገዱ  አድርገዋል። ከነዚህም ጄ/ል ወዲ አሸብር እና ጄ/ል ዮሀንስ(ጆኒ) ሲጠቀሱ፣ የዛሬ አምስት አመት  ለጄ/ል ሳሞራ በተላለፈ ቀጭን ትእዛዝ  ወዲ አሽብር  ለአንድ አመት የቁም እስረኛ  እንዲሆኑ ተደርገዋል።
እግዱ ተነስቶላቸው የሚመለሱበት፣ በሁዋላም ጠቅልለው  የሚወጡበት አካሄድ ለፓርቲው ቅርብ ለሆኑ አባላት ጭምር ግራ ያጋባ እንቆቅልሽ እንደነበር ይጠቁማሉ። አዜብ ብዙ ርቀት ለመጝዋዝ የጣሩት የስብሀትን አካሄድ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነበር። ነገርግን ያሰቡት እቅድ ሙሉ ለሙሉ ሳይሳካ የአሁኑ ጠንካራ ፍልሚያ ላይ ደርሰዋል።ስብሀት ከፓርቲው ሲለቁ «የእኔ» የሚሉአቸውን ሰዎች ቁልፍ ቁልፍ ቦታ እንዲጨብጡ አድርገዋል። የህወሀት ማ/ኮሚቴ ውስጥ የስብሀት ሁለት እህቶች አሉ።የፌደራል ደህንነት ቢሮ የሚመራው በጸጋዬ በርሄ (ሀለቃ)ሲሆን፣ የጸጋዬ ባለቤት ቅዱሳን ነጋ፣ የስብሀት ነጋ ታናሽ እህት ናት። ስብሀት በአዜብና በረከት ላይ ለከፈቱት የውስጥ ዘመቻ ከጎን ካሰለፉት አንዱ አርከበ እቁባይ ይገኙበታል።አርከበ  ከአዜብ በተደጋጋሚ የደረሰባቸው ጥቃት ለመጠጥ ሱሰኝነትና ብስጭት ዳርጎአችው ቆይቶአል። የእግዜር ሰላምታ መለዋወጥ ካቆሙ ክርመዋል። ስብሀት አርከበን ከጎን ሲያሰልፉ ሌላም አላማ አንግበው ነው። ይኽውም የውጭ ጉዳይ ሚንስትርነቱን ስልጣን ይረከባል ተብሎ የሚጠበቀው አቶ ብርሀነ ገ/ክርስቶስ ታናሽ እህት ንግስቲ ገ/ክርስቶስ የአርከበ ባለቤት ናት። ብርሀነ የነበረው ወዳጅነትና ታማኝነት ከመለስ ጋር አብሮ ምእራፉ ተዘግቶአል።
የፍጥጫው አንዱ አካል የሆነው የመከላከያ ጄነራሎች ሹመት ይገኝበታል። በአንዳንድ ወገኖች የሚሰነዘር ተገቢ ጥያቄ አለ። «የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥና ጠ/ሚ/ር በሌለበት እንዴትና በማን ሹመቱ ተሰጠ? ጸደቀ?» የሚል ሲሆን፣ ለዚህ ደግሞ ከመንግስት አፈ ቀላጤዎች የሚስጠው ምላሽ ሹመቱ ቀደም ሲል በአቶ መለስ የጸደቀ እንደሆነ ሲናገሩ ተደምጠዋል።
ይህ ግን ውሀ የማይቕጥር ነው ሲሉ የመከላከያ ምንጮች ማስተባበያውን ያጣጥላሉ። ምክንያቱንም ሲያስረዱ ከተሾሙት ጄነራሎች መካከል በአንጃነት ተፈርጀው የቆዩ፣ በመለስ በጥሩ አይን የማይታዩና ለረጅም አመት ለእስር የተዳረጉ እንዳሉም                              ይገልጻሉ። ሀቁ ይህ ሆኖ ሳለ መለስ እነዚህን  ይሾማሉ ብሎ ማሰብ ጨርሶ የማይታሰብ ነው ሲሉ ያክላሉ። እርከን ጠብቀው የተሾሙ  እንዳሉም ይጠቁማሉ። ቢሆንም ግን ህገ መንግስቱን ያልተከተለና ተገቢውን መንገድ  የልተከናወነ ሹመት እንደሆነ አልሽሽጉም።
 የብ/ጄኔራል ሹመት ከሰጣቸው አንዱ ኮ/ል አታክልቲ በርሄ  ይገኝበታል። ከዚህም ቀደም ባቀረብኩት መጣጥፌ «መለስ ካጠፋቸው የፓርቲው አባላት» ይኸው ኮ/ል እንደሚገኝበት ጠቅሼ ነበር። በተሰነይ ግንባር ከፍተኛ ጀግንነት የፈጸመው ኮ/ል አታክልቲ  ከጦርነቱ በሁዋላ መለስን ሀይለ-ቃል በመናገሩና በማውገዙ እስር ቤት ወርዶ ለረጅም አመት ድምጹ ጠፍቶ ቆይቶአል።በ 2000 አ.ም  ከእስር ተለቆ እንደቆየና በቅርቡ የብ/ጀነራልነት ሹመት አግኝቶ በተሻለ ሀላፊነት ላይ መቀመጡ ታውቆአል።
ሌላዋ የሴት ጄነራል ተሿሚ አስካለ ብርሀኔ ትባላለች። ህወሀትን የተቀላቀለችው ከበርካታ ታዳጊ  እኩዮችዋ ጋር ሲሆን ጊዜው ደግሞ ግንቦት 1970 አ.ም ነበር። አብረዋት ጫካ ከገቡት ሴቶች ሁሉም ማለት ይቻላል በነመለስ ተገፍተው ሜዳ ተጥለዋል። ጀነራል አስካለ ይህን ሹመት ማግኘትዋ አስገራሚ የሚያደርገው ነጥብ አለ። የቀድሞ አየር ሀይል አዛዥ ጀ/ል አበበ (ጆቤ) ባለቤት ስትሆን ፣ጆቤን ጨምሮ የጦር አዛዦችና ከፍተወታደራዊ መኮንኖች  እንዲባረሩ የተደረገው በመለስ ህገወጥ ውሳኔና ፊርማ እንደነበር ምንጮቹ ያስታውሳሉ።
የጄ/ል አስካለ ባለቤት- እህት ከተባረሩትና ከተንገላቱት መካከል ይጠቀሳሉ። የህወሀት ፖሊት ቢሮ አመራር የነበሩት አለምሰገድ ገ/አምላክ ባለቤት ሀመልማል ተ/ሀይማኖት ስትሆን ጋዜጠኛ ሀመልማል የጄ/ል አበበ ተክለሀይማኖት እህት ናት። ከራዲዮ ፋና እና ከፓርቲው እንድትባረር የተደረገው ባለቤትዋ ከመለስ ጋር በመለያየታቸው እንዲሁም ወንድሟ በመባረሩ ነበር።
በሌላም በኩል በአንጃ ደጋፊነት ተፈርጀው ከቆዩትና በመለስ በጥሩ አይን ከማይታዩት መካከል ፍስሀ በየነ፣አብርሀም አረጋይ፣የማነ ሙሉ፣ማአሹ ሀጎስ፣ግኡሽ ጽጌና ገብሩ ገ/ሚካኤል የብ/ጀነራልነት ሹመት ካገኙት ይጠቀሳሉ።አብዛኞቹ በሎጀስቲክ መምሪያ ሲሰሩ የቆዩ ናቸው። ከዚሁሉ ጀርባ እጃቸውን አርዝመው የሹመቱን ሚና የከወኑት ስብሀት ነጋ እንደሆኑ ሲታወቅ በሁለቱ ባላንጣዎች ላይ (አዜብና በረከት)የጥፋት ሴራ ማዘጋጀቱን ገፍተውበታል።
በደብረ ዘይት የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ሹም ጄ/ል ወዲ ዳኘው በሚመራው መንግስታዊ ተቛም አቶ ቢተው በላይ ስራ መጀመራቸው ታውቛል። በመለስ ታግደውና ታስረው የነበሩት ቢተው ቁልፍ በሆነ ቢሮ መመደባቸው ሚስጥሩ ስብሀት ነጋ እንደሆኑ ተጠቁሟል። የሜ/ጄነራልነት ሹመት ካገኙት አንዱ መሀሪ ዘውዴ ሲጠቀሱ የፓርቲው አባላት «ወዲ ዘውዴ» እያሉ የሚጠሩአቸው እኚህ ጄ/ል ከትግሉ ዘመን ጀምሮ የሳሞራ ቅርብ ወዳጅ እንደሆኑ ለማወቅ ተችሎአል።
በመጨረሻም በመከላከያ ቢሮ የምስራቅ እዝ ዋና እዛዥ ሆነው የቆዩት ጄ/ል ባጫ ደበሌ ባለፈው አመት በእረፍት ሰበብ ከሀላፊነት እርቀው እንዲቆዩ ከተደረገ በሁዋላ በዛው እንደተባረሩ ተገልጾላቸዋል። በአሁኑ ወቅት አሜሪካ እንዳሉ ሲታወቅ የት ከተማ እንዳሉና ለምን እንደመጡ ማወቅ አልተቻልም።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on September 22, 2012
  • By:
  • Last Modified: September 22, 2012 @ 8:05 pm
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

One thought on “የበረከት አዜብና የስብሃት ፍጥጫ ከ ኢየሩሳሌም አርአያ

  1. What I would recommand is as any patriotic Ethiopian. Stop believing change will come through a peaceful method. This people are psychopats, who been in the bush for a longest time and the only communication they realize is gun power. As such hit them where it hurts, organize both the muslim & christian youth and start attacking the woyane business and the woyanes that kill them and kill their family and robbing them in a broad day light.

    The only language a hyna can understand is you hit him where it hurts.

    That is the truth a thugh like sebhat nega, azeb mesfin, and bereket simon…and the rest woyane. Enough is enough, they will kill you any way you might as well die a hero death than being under this brutal murderers destroying our country.

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar