www.maledatimes.com የሣንባ ምች (Pneumonia) (በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሣንባ ምች (Pneumonia) (በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)

By   /   November 29, 2014  /   Comments Off on የሣንባ ምች (Pneumonia) (በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 9 Second

የሣንባ ምች (Pneumonia)
(በዶክተር ሆነሊያት ኤፍሬም)

የሣንባ ምች የምንለው በሣንባ ላይ ሚከሰትን ኢንፌክሽን ነው፡፡

► የሣንባ ምች እንዴት ይከሰታል?
✔ በባክቴሪያ
✔ በቫይረስ
✔ በሽታን የመከላከል አቅማቸው የደከመ ሰዎች ላይ ደግሞ በፈንገስ ምክንያትም ይከሰታል፡፡

አንድ ሰው አየር በሚያስገባ ጊዜ እነዚህን በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ወደ ውስጥ ያስገባል፡፡ይህም ወደ ሣንባ በመሄድ ኢንፌክሽን ይፈጥራል፡፡

► ለሣንባ ምች ተጋላጭነት የሚዳርጉ ሁኔታዎች
✔ ዕድሜ፡-ዕድሜያቸው ከ1 ዓመት በታች የሆኑ እና ከ65 ዓመት ዕድሜ በላይ የሆኑ ሰዎች
✔ በሽታን የመከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች
✔ በጉንፋን የተጠቁ ሰዎች
✔ የአስም ሕመም ተጠቂ የሆኑ ሰዎች
✔ ሲጋራን ማጤስ
✔ የአልኮል መጠጥን እጅግ ማዘውተር

► የሣንባ ምች ሕመም ምልክቶች
✔ አክታ የተቀላቀለ ሳል
✔ ትኩሳት
✔ ትንፋሽ ማጠር
✔ የራስ ምታት
✔ ብርድ ብርድ ማለት
✔ የደረት ውጋት በሳል ጊዜ የሚብስ
✔ የልብ ትርታ መጨመር
✔ ላብ ላብ ማለት
✔ የሰውነት ድካም
✔ የምግብ ፍላጎት መቀነስ
✔ ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
✔ ተቅማጥ ናቸዉ

► የሣንባ ምችን እንዴት መከላከል ይቻላል?
✔ ሲጋራ ማጤስን ማቆም
✔ እጅን በሚገባ መታጠብ

► የሣንባ ምችን ሕምተኞች በቤት ውስጥ ሊያደርጓቸው የሚችላቸው ሕክምናዎች፤
✔ ፈሳሽ በብዛት መውሰድ
✔ ዕረፍት ማድርግ
✔ ትኩሳትን ማስታገሻ በመውሰድ መቆጣጠር

በቫይረስ የሚከሰት የሣንባ ምች በአብዛኛውን ጊዜ በጉንፋን ምልክቶች የሚጀምር ሲሆን ትኩሳት፤ ደረቅ ሳል፤ ራስ ምታት፤ ቁርጥማት እና የድካም ስሜትን ያስከትላል፡፡ ትንፋሽ ማጠር እና አክታ ከአንድ ቀን በኋላ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡

በባክቴሪያ የሚከሰት የሣንባ ምች ከፍተኛ ትኩሳት፤አክታን የቀላቀለ ሳል፤ከፍተኛ የሰውነት ማላብ፤የልብ ምት መጨመር እና በፍጥነት የሚጨምር የአተነፋፈስ ሥርዓት ይኖራቸዋል፡፡

የሣንባ ምች ሕክምና ህመሙን እንዳስከተለው ተህዋስያን ዓይነት፤ እንደ ሕመሙ ክብደት እና ተጨማሪ ሕመም መኖር ሁኔታ ይለያያል፡፡

በሕመሙ የተጠቁ ሰዎች ወደ ሕክምና ቦታ በመሄድ ሐኪምን በማማከር ሕክምናውን በመውሰድና በሚገባ በመከታተል ከበሽታው ይድናሉ፡፡

ጤና ይስጥልኝ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on November 29, 2014
  • By:
  • Last Modified: November 29, 2014 @ 2:55 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar