www.maledatimes.com የህወሃት ታጋዮች እና በአሁን ሰአት በደህንነት አገልግሎት ላይ የሚገኙ ፬ አባሎች በእናት ፓርቲያቸው ተከሰሱ ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የህወሃት ታጋዮች እና በአሁን ሰአት በደህንነት አገልግሎት ላይ የሚገኙ ፬ አባሎች በእናት ፓርቲያቸው ተከሰሱ !

By   /   November 29, 2014  /   Comments Off on የህወሃት ታጋዮች እና በአሁን ሰአት በደህንነት አገልግሎት ላይ የሚገኙ ፬ አባሎች በእናት ፓርቲያቸው ተከሰሱ !

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 21 Second

ከአስገደ ገ/ስላሴ ወ/ሚካኤል
የአንድነት ለፍትህና ዲሞክራሲ (አንድነት) አባል ወጣት ሽሻይ አዘናው ለ24 ቀን መሰወሩ ተያይዞ በ26/02/2007ዓ.ም ከሚሰራበት የስራ ቦታው ታፍኖ በመቐለ ኮሙሽን ፖሊስ ክልል ትግራይ ልዩና ፅኑ እስርቤት ታስሮ ህገ መንግስታዊን መብቱ በመከልከል ጠበቃ እንዳያአማክረው ምግብ እንዳይገባለት ፡ ዘሞዶቹና ጓደኞቹ እንዳያዩት ተነፍጎት 12 ቀን ያህል በህቡእ ታሰሮበት ከነበረበት ተሰውሮ እስከ 18/03/2007ዓ.ም በጠቅላላ ለ24 ቀን በመሰወሩ መጀመርያ ከሰራ ቦታው አስገድደው ቤቱ በርቡረው አስፈላጊ ቁሳቁስ ወስደው የቀረው ንብረቱ ሃላፊነት በጎደለው ጥለውት አስረው ለክልሉ ፖሊስ ኮምሽን መርማሪ ኮማንዶሮች ያስረከቡና፡ የክልሉ የምርመራ ኮማንደሮች ደግሞ ወጣቱ አስረው 24 ቀን በመሰወራቸው ምክንያት በመቐለ ቀዳማይ ወያነ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት በወንጀል ተከስው መሪማሪ ፖሊስየተከሰሱት ኮማንደሮች የማጣራት ምስክርነት ለመቀበል ለ23/03/2007ዓ.ም ለምስክሮች እንዲቀሩ ትእዛዝ ሰጥዋል፡፡
ከተከሰሱት ውስጥ የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. ኮማንደር ገ/ሂወት ካሕሳይ የመቐለ ከተማ ፖሊስ ዋና ኣዛዥ
2. ኮማንደር ሙሩፅ በረኸ የመቐለ ከተማ ፖሊስ ምክትል ኣዛዥ
3. ኮማንደር አለም ምስግና የክልል ትግራይ ፖሊስ ኮምሽን ዋና የምርመራ ኣዛዥ
4. ኮማንደር ሰዓረ ምራጭ የክልል ፖሊስ ኮምሽን የምርመራ ተክኒክ `ላፊ
5. ሓጎስ በሚል ሥም የሚታወቅ የድህንነት አባል
የክሱ ዝርዝር ይዘት
የሃገራችን ህገመንግስት በመጣስ፡ ህግ አማካሪ በመከለከላቸው ምግብ እንዳይገባ ፡ ከዘመዳቸውና ጓዶኞቹ እንዳገናኝ ከማድረግ አልፉ ሽሻይ አዘናው አሁንም የለም ተሰውረወዋል በተጨማሪም እስካሁን አሁን በህቡእ ይሁን በግልፅ ፍርድቤቱ መቅረቡ አይታወቅም በማለት ክስ ዛሬ 18/03/2007ዓ.ም ገብቷል ፍትህ ይገኝ ይሆን ክትትሉ ለህዝቡ ከሻሽ ለአንድነት ለፍትህ ለዲሞክራሲ(አንድነት) በመወከል አቶ አስገደ ገ/ስላሴ፡-
የፖሊስ ኮማንደሮችና የድህንነት አባሉ ለፈፀሙት ወምጀል በምስክርነት የተመዘገቡ
1. መምህር ታደሰ ቢተውልኝ ከመቐለ
2. አቶ ገ/ሚካኤል ከመቐለ
3. ዓንዶም ገ/ስላሴ ከመቐለ
4. መምህር ገብሩ ሳሚኤል ከመቐለ
5. ጉዑሽ አዘናው ወረታ ከሰሜን ምዕራብ ዞን
ከላይ የተዘረዘሩት ተከሳሽ የፖሊስ ኮማንደሮች ከ30 አመት በላይ የህ.ወ.ሓ.ት ታጋዮች የነበሩ ናቸው፡፡ናቸው፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on November 29, 2014
  • By:
  • Last Modified: November 29, 2014 @ 10:17 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar