www.maledatimes.com ቴዲ አፍሮ በሰርጉ ቀን ለአካል ጉዳተኞች በብሄራዊ ቴአትር 100.000 ሺህ ብር ለገሰ ሌሎችም ድንቃድንቅ ስጦታዎች ከአድናቂዎቹ እና ከወዳጆቹ ተሰጠው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ቴዲ አፍሮ በሰርጉ ቀን ለአካል ጉዳተኞች በብሄራዊ ቴአትር 100.000 ሺህ ብር ለገሰ ሌሎችም ድንቃድንቅ ስጦታዎች ከአድናቂዎቹ እና ከወዳጆቹ ተሰጠው

By   /   September 27, 2012  /   Comments Off on ቴዲ አፍሮ በሰርጉ ቀን ለአካል ጉዳተኞች በብሄራዊ ቴአትር 100.000 ሺህ ብር ለገሰ ሌሎችም ድንቃድንቅ ስጦታዎች ከአድናቂዎቹ እና ከወዳጆቹ ተሰጠው

    Print       Email
0 0
Read Time:6 Minute, 24 Second

ቴዲ አፍሮ በሰርጉ ቀን ለአካል ጉዳተኞች  በብሄራዊ ቴአትር 100.000 ሺህ ብር ለገሰ

ሌሎችም ድንቃድንቅ ስጦታዎች ከአድናቂዎቹ እና ከወዳጆቹ ተሰጠው

ወጣቱ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮን የማይወድ እና የማያደንቅ ወጣት አዛውንት የለም ሆኖም ይህንን የሰርጉን ቀን አስመልክቶ ወዳጅ ዘመዶቹ ታላቅ የደስታ ቀናቸው ነበር ።በዛሬው እለት የተፈጸመው ይህ ሰርጉ ደማቅ ከመሆኑም በላይ ታሪክ የተሰራበት እለት መሆኑን ታዳሚዎቹ ገልጸዋል ።ብዙ አርቲስቶች የተሳተፉበት ይህ የሰርግ በአል የእርሱን ኩራትም ሆነው በሰርጉ እለት አሳይተውታል። ቴዲ አፍሮ ለውዱ ባለቤቱ እሱ ከመድረክ ላይ ሆኖ ሙሽሪት ከሚዜዎቿ ጋር ከመድረክ ስር እየጨፈረች ጸባየ ሰናይ የሚለውን ዘፈኑን አቀንቅኖላታል ።ከዚያም በላይ አለማየሁ እሸቴ አዲስ አበባ ቤቴ የሚለውን ዘፈን ሲዘፍን ተሰምቷል በዚህም ዘፈን ላይ መድረክ ላይ በመውጣት የጋራ ዳንሳቸውን አሳይተዋል ።በመጨረሻም የሰርግ ዘፈን ሲዘፈን በታዳሚው ፊትለፊት እየተሳሳሙ የፍቅር ጉያቸውን በሞቀ ትንፋሻቸው አሙቀውታል ሌሎችም የሙዚቃ ባለሙያዎች ስራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን ከሰአት ማጠር የተነሳ ሃይልዬ ታደሰ እና ታምራት ደስታ ብቻ ሳይዘፍኑ ፕሮግራሙ ተጠናቆአል ።ይህ የቴዲ አለም ዛሬ ታላቅ ቀን ነበር ያሉት ታዳሚዎቹ ቴዲ ለዚህች አገር እና ለሙዚቃ ወዳጆቹ ብዙ መሰዋእትነትን ከፍሎአል አሁንም በዚህ ክብረ በአሉ ላይ ወዳጆቹ መንገዶችን ሞልተው ሞተር ሳይክል አሸከርካሪዎች በተለያዩ ሾዎች እያሳዩ ፍቅራቸውን ለግሰውታል አድናቆታቸውንም ቸረውታል ።ከዚያ በተለየ መልኩ ሻንበል እና ሰአሊ ለማ ጉያ አስደናቂ የሆነ ስጦታ ለቴዲ አፍሮ ቴዲ ስጦታ ያወረሱት ሲሆን ከስእሎቻቸው መሃል ለዚህ ለሰርጉ ቀን ተብሎ የተሳለ የአጼ ቴዎድሮስን ስእል ከአንበሳ ጋር ያለበትን ታላቅ ስጦታ ሲያበረክቱለት የህዝቡ ስሜት ታላቅ ነበር ብለዋል ።በተለይም ለማለዳ ታይምስ የደረሱት ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በዚህ ስጦታ ላይ ተዲ ሳቅ እና ለቅሶ  ሲታይበት ሰአሊውን አቅፎ ለረጂም ሰአት ስሟቸዋል። ኢዮብ መኮንን (ብረባም ባልረባም ትወጂኛለሽን) ሲያቀነቅን ጎሳዬ ተስፋዬ ከራሱ ዘፈኖች እና ከቴዲ ዘፈን ዘፍኖአል ሸዋንዳኝ የቀረብኝ የለም ሲል አለማየሁ እሸቴ አዲስ አበባ ቤቴ ብሏል ታደለ ገመቹ ኦሮምኛ ሲያዘም ግርማ ካሳ ፣ተሾመ ወልዴ አበጋዝ ክብረ ወርቅ ፣ዳግማዊ አሊ ፣ሳምሶን ጃፋር ፣ፋሲል ውሂብ፣አሸናፊ አሊ ፣አቡጊዳ ባንድ ፣ኤክስፕረስ ባንድ፣ ክብረት ዘኪዎስ ፣ታምራት ሃይሉ (ቁም ነገር መጽሄት) :ታምራት ደስታ

እና ሃይልዬ ታደሰ የመድረኩ አጋፋሪዎች ነበሩ ።ከላይ እንደጠቀስነው በፕሮግራሙ መጣበብ ምክንያት ሃይልዬ እና ታምራት ብቻ ሳይዘፍኑ የሰርጉ ሁኔታ ተጠናቆአል።ሁሉም አርቲስቶች በጣም ተደናቂ የሆኑትን እና በህዝብ ዘንድ ተወዳጅ ዘፈኖቻቸውን አቅርበዋል።

በዚህ የክቡር ቀን ለአካል ጉዳተኞች የአንድ መቶ ሺህ ብር በብሄራዊ ቴአትር ጋር ማስረከቡን ይበልጥ ኩራት ለህዝቡ ሆኖታል ፣የአካል ጉዳተኞችም ደስታቸውን እና የሰርጉን ድምቀት ሆነውት አልፈዋል ።

ማለዳ ታይምስ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar