www.maledatimes.com የማለዳ ወግ …የእኔ ፣ ያንተ ፣ የእናንተ ፣ የእኛ ተጠቂዎች ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የማለዳ ወግ …የእኔ ፣ ያንተ ፣ የእናንተ ፣ የእኛ ተጠቂዎች  !

By   /   November 3, 2015  /   Comments Off on የማለዳ ወግ …የእኔ ፣ ያንተ ፣ የእናንተ ፣ የእኛ ተጠቂዎች  !

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 4 Second

=======================================
* * በጅዳ ቆንስልና በሪያድ ኢንባሲ በር የሚጣሉ ወገኖች …

ትናንት ጥሩ አልተሰማኝም ነበርና ወደ ሀኪም ጎራ ብየ ምርምራ ካደረግኩ በኋላ መድሃኒት ተሰጥቶኝ ተመለስኩ ፣ ዛሬ እረፍቱንም ወሰድኩና ከትናንት ዛሬ ተሽሎኛል ።  በጭንቅ በጉዳቴ መልካም ምኞቻችሁን ለገለጻችሁልኝ ምስጋናየ ከፍ ያለ ነው አመሰግናለሁ  !

ከህመሙ አገግሜያለሁና በቀጠሮየ ሰዓት ካልደረስኩላቸው የብላቴናው መሀመድን እናት እርዳታ አድራጊ ወገኖቸ የቻልኩትን እርዳታ ለመሰብሰብ ወጣ ባልኩበት አጋጣሚ ስልክ ተደወለልኝ ። አነሳሁት ፣ ከሰላምታ በኋላ ” ጠፋህ ?  የት ነው ያለህ  ? ”  ከሚለው አጭር የተለመደ የሰላምታ ማጀቢያ በኋላ ወዳጀ ወደ መልዕክታቸው  ገቡ …
” አንተ ነብዩ የት ጠፋህ  ? ”  ሲሉ ደገሙና  ስመለጥፋቴ ጠይቀውኝ  ሲቀጥሉ ”  ናና አንድ እህት ከጅዳ ቆንስል በር ወድቃለች ፣ ጸሀይ እየደበደበ አድክሟታል  ! እነሱ ( የቆንስል ሰዎች ማለታቸው ነው)  ቢነግሯቸው አይሰሙም ።  ሌላም ሶስት እህቶች ከቆንስሉ አጠገብ ካለው ንጉድ ፉአድ ሆስፒታል ያለ ጠያቂ ተኝተዋል ። ጎብኟቸውና ችግራቸውን ተረዱ ወይ መፍትሄ ፈልጉ ወይ ወደ ሀገር  ስደዷቸው ብል የሚሰማ የለም  ! አንተን ከሰሙህ ናና እያቸው!  ” ብለው ቁጣ የተቀላቀለበት መልዕክት አስተላለፈውልኝ ተጣድፈው ስልኩን ዘጉት … !  የእኒህ ወንድም መረጃ ሲያቀብሉኝ በስጨት ማለት ምክንያቱ ገብቶኛልና አልተከፋሁም ፣ ይልቁንም ስለሰጡኝ መረጃ አመሰገንኳቸው ። …

አሁን አሁን በኮንትራት መጥተው ጠፍተው ሲሰሩ የነበሩት ፣ በባህርም ሆነ በቀድሞው ሃጅና ኡምራ  መጥተው በአሰሪዎቻቸው መደፈር መደብደብን ጨምሮ   ፈርጀ ብዙ በሆነ ምክንያት  የተለያየ ጥቃትም ሆነ ህመም ሲያጠቃቸው መጥተው የሚወድቁት በዚሁ በጅዳ ቆንሰል በር ነው ። ለምን ቢባል ዘንድሮ  ህጋዊ መኖሪያ ፍቃድ የሌላቸውን ማስጠጋት አደጋ አለውና ነው ፣ አደጋው ደግሞ ቤተሰብን ጠቅልሎ ከሀገር መባረር ነውና ያስፈራል ። ይህ የከፋ ችግር የተጋረጠበት የጨነቀው ነዋሪ እየፈራ እየተባ ያስጠጋው ነዋሪ ወደ ሀገር ይገባ ዘንድ ከቆንሰል መስሪያ ቤቱ ጋር ሞግቶ አልሳካለት ሲል ከቀጣዩ አደጋ ራሱን ለመከላከል የስጋ ዘመዱን ሳይቀር በጠራራው ጸሀይ ጨክኖ አምጥቶ የሚጥለው በቆንስሉ በር ላይ ነው  !

ያን ሰሞን አንድ ወዳጀ ” በቆንስሉ በር የወደቀች ልጅ አለች እያት ታሳዝናለች! ” የሚል መረጃ አደረሰኝና ወደ ዚያው አቀናሁ ፣ ሙቀት ያደከማት ፣ ውሃ ጥም ያደረቃትን እህት አገኘኋት ፣ ከመኪናየ ውስጥ የነበረውን ውሃ ስሰጣት ተንሰፍስፈሰ ስትጠታው የተሰማኝን ህመም ሳስበው እታመማለሁ … ልጅቱ በዥጉርጉሩ ፎቴ ተዘርራ የምታዮዋትን ናት  ፣ ውሃው ድካሟን አልመለሰውም ፣ ተንፈስ ማለት ችላለች … ያም ቢሆን የዋለባት ሙቀቱ አድክሟት ያዝ ለቀቅ እያደረገች  ያጫወተችኝ የቅርብ ዘመዶችዋ በቆንስል መስሪያ ቤቱ በኩል ወደ ሀገር የመጓጓዣ ሰነድ አውጥተው ለመስደድ ሞክረው አልሆን ሲላቸው አምጥተው እንደጣሏት ነበር  … ስሜቴ በጣሙን ተነክቶ ወደ አምባሳደር ውብሸት በላኩት መልዕክት ቦታውን ሳልለቅ ወደ መጠለያው ለመግባት ፈቃድ በማግኘቷ ቆንስሉ ልትሞት የነበረቸውን እህትን የታደጋትን ያህል ተደሰትኩ …

ዛሬ ከሰዓታት በፊት ያየኋት እህት በጠራራው ጸሃይ በቆንስሉ በር ተዘርራ ተኝታ ነበር ፣ አትሰማም አትናገር ። ብዙዎቻችን ከንፈራችን እየመጠጥን ስናልፋት በመኪና የሚተላለፉት አረቦች ሲያዩዋት መኪናቸውን አቁመው ” ለምን ወደ ግቢ  አታስገቧትም ? ለምን አንቡላንስ አትጠሩም ? ”  እያለ እያዘኑ ” ፈጣሪ ይድረስልሽ ፣ ምስኪን! ” እያሉ  ይሄዳሉ … እያየን ወደ ሀላፊዎች ስልክ ደውለን ለማሳወቅ እንኳ ” ተቃዋሚ ምንቴስ ” እንባላለን ብለን ከምንፈራው  ብዙዎች የተሻሉ የምላቸው  የሳውዲ መንግስት የቆንስሉ ጠባቂዎች ደጋግመው ወደ ቀይ ጨረቃ ደውለው አንቡላንስ አልመጣ ቢልም ጉዳዩን ወደ አንድ ጉምቱ ባለስልጣን በመድረሱ አንቡላንሱ ፈጥኖ ሳይመጣ አይቀርም  ! እኔም እንደ አልፎ ሂያጁ አረብ ” ምስኪን  !  ፈጣሪ ይድረስልሽ  ! ” ከማለት ውጭ የምለው የለም…  !

እኛ ቅንጡዎች ”  ራሳችን ፣ ሆድ እቃ ፣ እግር እጅ  ፣ አይናችን   አመመን  !” ብለን አገር ይያዝ ብለን በምንቀውጥበት ሰማይ ስር ያየሁት የማይታመን አይደለም ፣ ይህችና ይህችን መሰል እህቶች በሀገራችን የመንግስት ተወካይ ፣ የማህበረሰብና የፖለቲካ ድርጅት ተወካዮችና የደላ የሞላልን ሳይሆን ሳይደላን በሽፍንፍን ህይዎት  አሸሸ ገዳሜ በምንልበት አዳራሽና ቆንስል በር በተደጋጋሚ ይጣላሉ ፣ ያለላቸው ተርፈው ያላለላቸው “ሰርታ ታሻሽለኛለች !”  ብሎ ለላከላቸው ወላጅ የህይዎት እንቆቅልሽ ይሆኑ ዘንድ  ማንነታቸው ሳይታወቅ ወደ ማይቀረው አለም ይሸኛሉ 🙁   … የሳውዲ መንግስት በነጻ የሚሰጠው  ህክምና አይደለም ቀዝቃዛ ውሃ ናፍቋቸው ፣ ይህችን አለም ሲሰናበቱ ማየት በእርግጥ ያማል … 🙁 ይህን አይቶ ዝም ማለቱም ለእኔ ሌላ እዳ ነውና ያማችሁ ዘንድ ብቻ ሳይሆን የሚመለከታቸው መፍትሄ ይፈልጉለት ዘንድ እነግራችኋለሁ !

ደረቁ እውነት ይህ ነው … እኒህ በየሜዳው ተጥለው የሚጠፉት እህቶች ከወላጅ ጀምሮ ፣ የመንግስት ፣ የነዋሪው ፣  የማህበረሰብ ተወካዮች ፣ ይህ መከራ መቋጫ እንዲመጣ ያልተጉት ፖለቲከኞችን  ጨምሮ በግል የእኔ ፣ ያንተ ፣ ያንችም የሁላችንም ተጠቂዎች ናቸው  ! በጅዳ ቆንስልና በሪያ ኢንባሲ በር የሚጣሉ ወገኖች …ተጠቂዎች ናቸው  !

ቸር ያሰማን ስል ለብላቴናው መሀመድ እናት ለእናት ሀሊማ የምታደርጉትን እርዳታ እንዳትረሱ በማስታወስ ነው  ! የመሀመድ ቤተሰብ ፍትህ እስኪያገኙ ከንፈር ከመምጠጥ ባለፈ የከበደውን አንግልትና ወጫቸው ለመሸፈን ቢገድ ለቤት ኪራይና ትራንስፖርት የቻልነውን በማድረግ መከራውን ልንጋራ ይገባል ። አነሰ በዛ አትበሉ ፣ ብርቱዋን እናት ሃሊማን ቢያንስ ለማረፊያና ለትራንስፖርት ለመርዳት ፈቃደኛ የሆናችሁ በስልክ ቁጥር 0505682531 ደውሉ ካላችሁበት ድረስ መጥቸ እርዳታውን እቀበላለሁ !

ሰላም  !

ነቢዩ ሲራክ
ጥቅምት 20 ቀን 2008 ዓም

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on November 3, 2015
  • By:
  • Last Modified: November 3, 2015 @ 5:06 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar