www.maledatimes.com በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በንጹሃን ሰልፈኞች ላይ መንግስት እየፈጸመውን የሚገኘውን ግፍ ለማውገዝ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በበርሊን ለማድረግ ወሰኑ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በንጹሃን ሰልፈኞች ላይ መንግስት እየፈጸመውን የሚገኘውን ግፍ ለማውገዝ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በበርሊን ለማድረግ ወሰኑ።

By   /   August 8, 2016  /   Comments Off on በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በንጹሃን ሰልፈኞች ላይ መንግስት እየፈጸመውን የሚገኘውን ግፍ ለማውገዝ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በበርሊን ለማድረግ ወሰኑ።

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 41 Second

ኢትዮጵያውያን በጀርመን ኑረምበርግ በምትባል ከተማ ነሃሴ 1 2008 ዓም ባደረጉት ታላቅ ስብሰባ በመላው የኢትዮጵያ ክፍል እየተቀጣጠለ ባለው የሀዝብ ለአምባገነናዊ ስርአት አልገዛ ባይነት ምክንያት በመንግስት ታጣቂዎች እየተፈጸመ ያለውን ግድያ እስራት እንዲሁም ድብደባ አውግዘዋል። በተጨማሪም በጀርመን የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአሰቃቂ ሁኔታ በንጹሃን ኦሮሞ እና አማራ ህዝብ የመንግስት ታጣቂዎች እየፈጸሙ ላሉት የነፍስ መገደል እና እስራት በመቃወም በጀርመን በርሊን ከተማ ድምጻቸውን ለአለም ለማሰማት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ለማዘጋጀት ፕሮግራም አዘጋጅተዋል።

በስብሰባውም የአርበኞች ግንቦት ሰባት የኮምኒኬሽን ሀላፊ አርበኛ ኑር ጀባ ከኤርትራ ቀጥታ በስልክ መስመር በመግባት ለታዳሚው ከእያንዳዱ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚነሱት ህዝባዊ አመጽ ጀርባ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ከፍተኛ እንቅስቃሴ አለበት በማለት ማረጋገጫ ሰጥቶል። የኮምኒኬሽን ሀላፊው አርበኛ ኑር ጀባ በማከልም አምባገነናዊነትን ዘረኝነትን እንዲሁም ኢፍትሃዊነትን በመቃወም በአደባባይ በመንግስት ሀይሎች በጥይት ለረገፉት ንጹሃን የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆች የወያኔ መንግስት ሃላፊነቱን ሙሉ በሙሉ መውሰድ እንዳለበት አሳስቧል። እንደ አርበኛ ኑር ጀባ ገለጻ መሰረት አርበኞች ግንቦት ሰባት የወያኔን መንግስት በ3 ዓይነት መንገድ እየታገለ መሆኑን ለታዳሚው ገልጸዏል። 1ኛው ህዝባዊ አመጽ በአገር ውስጥ በማነሳሳትና በመደገፍ 2ኛው ከኢትዮጵያ ውጭ ወያኔንና የወያኔ ድርጅቶችን የማዳከም እንቅስቃሴ 3ኛው የትጥቅ ትግል ናቸው። በተለያዩ ጊዜያት የወያኔን ስርዓት በሀይል ለመጣል በሚደረገው የትጥቅ ትግል በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እያደረጉት የሚገኘውን የሞራል የቁሳቁስ የገንዘብ እርዳታ አርበኛ ኑር ጀባ በሰራዊቱ ስም ታላቅ ምስጋናውን በማስተላለፍ ፤ ይሀ ዓይነቱ ድጋፍ በሰፊው እንዲቀጥል ጥሪ አስተላልፉዋል። ታዳሚውም በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች
የሚገኘው የኢትዮጵያ ህዝብ በጨቋኞች አምባገነኖችና ከፋፋዮች መገዛት በቃኝ ብሎ በአደባባይ ጸረ ወያኔ ትግሉን ለወራት አፏፉሞ በመቀጠሉ እና እጅግ አስገራሚ መስዋቶችን እየከፈለ በመሆኑ ለዚህ ትግልን የተፈለገውን ግብ እንዲመታ ለመደገፍ ወስነዋል። በዚህ የአቁዋም መግለጫ በውጭ አገር የሚኖሩ መላው ኢትዮጵያውያን በንጹሀን ህዝቦች ላይ ከፍተኛ ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ እና ግድያ ሲፈጸም ቸል ማለት እንደሌለበት ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።

ይህንን ተከትሎም ታዳሚው ለኢትዮጳያ ህዝብ ያለውን አጋርነት ከዚሀ በታች በተዘረዘሩት እንቅስቃሲዎች ገልጸዋል።
1ኛ የወያኔ ኢህአዲግ በህዝባችን ላይ እየፈጸመ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ለአለም አቀፍ ህብረተሰብ በማጋለጥ
2ኛ በበርሊን ከተማ ከፍተኛ የተቁዋሞ ሰልፍ በማዘጋጀት የአለም አቀፍ ማህበረሰብ በወያኔ ላይ ተጽእኖ እንዲያደርግ በመታገል
3ኛ አለአግባብ የታሰሩ የህዝብ ተወካዮች ጋዜጠኞች የፖለቲካና የሀይማኖት መሪዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ከፍተኛ ግፊት በማድረግ
4ኛ ወያኔ ኢህአዲግ ሃገሩንና ህዝቡን ማስተዳደር ስላልቻለ በአስቸኩዋይ ከስልጣን የሚወርድበትን እንዲሁም ስልጣኑን ለህዝብ አስረክቦ የሽግግር መንግስት ለመመስረት የሚያስችል ነጻና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ መንገዶች በመፍጠርና በማመቻቸት ናቸው።

ዘርይሁን ሹመቴ ከጀርመን

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on August 8, 2016
  • By:
  • Last Modified: August 8, 2016 @ 1:43 pm
  • Filed Under: Ethiopia

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar