www.maledatimes.com ወያኔ በባሕርዳር፣ ጎጃም ዐማራ እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ በቃን - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ወያኔ በባሕርዳር፣ ጎጃም ዐማራ እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ በቃን

By   /   August 7, 2016  /   Comments Off on ወያኔ በባሕርዳር፣ ጎጃም ዐማራ እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ በቃን

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 42 Second

በሙሉቀን ተስፋው
የቆሰሉና የሞቱ ሰዎች ቁጥር አይታወቅም፤ ዓባይ ማዶ ኮበል በቃጠሎ ወድሟል
• ከጎንደር የሚሔዱ ዐማሮች ዘንዘሊማ ላይ መታገዳቸው ለግጭቱ መንስኤ ሆኗል
በጎጃም እምብርት ባሕር ዳር ዐማሮች በጠዋት ነበር ወደ ተጋድሎ ሰልፍ የወጡት፡፡ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በሰላማዊ መንገድ በዐማራ ወገኖቻቸው ላይ የሚደርሰውን በደል እና የጅምላ ግድያ በማውገዝ ወደ መስቀል አደባባይ ሕዝቡ በአንድነት ሔደ፡፡ በዚህ መካከል ከጎንደር ለተጋድሎ የሚመጡ ዐማሮች ዘንዘሊማ ላይ በወያኔ ጦር ወደ ባሕር ዳር መግባት እንዳይችሉ መታገዳቸው ተሰማ፡፡ ሕዝቡ ተመልሶ ከጎንደር አካባቢ የመጡትን ወገኖችን ለማስለቅ ወደ ዓባይ ማዶ መንገድ አመራ፡፡ በቀበሌ 18  የሚገኘውን የመንግስት መስሪያ ቤቶችን በአማራው ህዝብ ቁጥጥር ስር መዋሉ እና ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ነጻነቱን ለማስከበር መታሩ ምን ያህል በመንግስት ላይ ያለውን ጥላቻ የሚያሳይ ሲሆን  በሌሎች በአማራ ክልል የሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ስልት ተጠቅመው የክልሉን ወታደራዊ ስርአት በቁጥጥሩ ስል ለማድረግ የሚቻለውን ሁሉ ለማድረግ የተለያዩ ቅየሳዎችን እያደረገ እንደሆነ ከአማራ ክልል ለማለዳ ታይምስ የደረሰው ዘገባ ያመለክታል ።
የዐማራ ተጋድሎ ተሳታፊዎች እግረ መንገዳቸውን ባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ (ፖሊ ካምፓስ)፣ ክልል ምክር ቤት፣ አማራ ብድርና ተቋምና ሌሎች መሥሪያ ቤቶች አካባቢ ያሉ የወያኔን ድሪቶ ባንዲራ የአባቶቻችን ደም በፈሰሰባት ትክክለኛ ሰንደቅዓላማ በመቀየር እንዲሁም የክልሉ ምክር ቤት ፊት ለፊት የነበረውን የመለስ ቢል ቦርድ በማቃጠል ወደ ዓባይ ማዶ ነገዶ፡፡ ባሕር ዳር ከተማ የቀረ አንድም ዐማራ አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡
የዓባይን ድልድልይ ተሻግረው ወደ ዘንዘሊማ ለመሔድ መንገድ ሲጀምሩ አዲስ ዓለም ገበያ አካባቢ ‹‹ኮበል›› የሚባል የወያኔ ምልስ ወታደሮች ንብረት የሆነ ስጋ ቤትና ግዙፍ የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶች ማምረቻ ድርጅት አለ፡፡ ይህ ድርጅት በተለምዶም ‹‹ዳሸን ቢር ጋርደን›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከዚህ ግቢ ውስጥ በሰለማዊ መልኩ ተጋድሎውን ሲቀጥል በነበረው ሕዝብ ላይ የተኩስ እሩምታ ተከፈተ፡፡ ኮበል ማዶ ካሉ ኮንዶሚኒየም ሕንጻዎች ፎቅ ላይ የወጡ የወያኔ አልሞ ተኳሾች በተቃራኒ አቅጣጫ ከሕዝቡ ላይ ጥይት አርከፈከፉ፡፡ ባዶ እጃቸውን የነበሩ ዐማሮችን ደም ወያኔዎች አፈሰሱ፡፡
በዚህ የተበሳጨው የዐማራ ነበልባል ወጣት ከማደያ ነዳጅ እየቀዳ የኮበል ኢንዳስትሪን ሙሉ በሙሉ በእሳት አጋዬ፡፡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ዐማሮች ሌሎችን ለማኖር ሲሉ ተሰውተዋል፡፡ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል፡፡ አሁን በዓባይ ማዶ መካከለኛ ክሊኒክና በአዲስ ዓለም ጠቅላላ ሆስፒታል በርካታ እስረኛና ቁስለኛ እንዳለ ነው ከቦታው ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው፡፡
ባሕር ዳር በአሁኑ ሰአት ዝናብ ቢሆንም ወጣቶች ተጋድሏቸውን አላቆሙም፡፡ ‹‹ደም ሰፈስ ደም ይፈላል›› እንዲሉ አበው፤ የዐማራ ወጣቶች ተጋድሎ ያለምንም ጥርጥር በሰማእት ወንድሞቻችን አጥንት ካስማ መሠረት ላይ ይገነባል፡፡
ይህ ሁሉ ግን የመጀመሪያው መጨረሻ ነው!!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on August 7, 2016
  • By:
  • Last Modified: August 7, 2016 @ 5:47 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar