www.maledatimes.com በህዝባዊ ተቋውሞ የተወጠረው ወያኔ በጀርመኑዋ ካንስለር አንጌላ ሜርክል ጫና ሊገጥመው ነው ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በህዝባዊ ተቋውሞ የተወጠረው ወያኔ በጀርመኑዋ ካንስለር አንጌላ ሜርክል ጫና ሊገጥመው ነው ።

By   /   October 7, 2016  /   Comments Off on በህዝባዊ ተቋውሞ የተወጠረው ወያኔ በጀርመኑዋ ካንስለር አንጌላ ሜርክል ጫና ሊገጥመው ነው ።

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 29 Second

ለተጠናከረው ዘገባ ዘርይሁን ሹመቴ ከጀርመን
161005_press_release_merkel_visit
የጀርመኑዋ መርሃ መንግስት አንጌላ መርክል (Chancellor Dr. Angela Merkel) በ 11/10/ 2016 እኤአ ( 30/ 01/ 2009 ዓም) ይፋዊ የሰራ ጉብኝት በኢትዮጵያ እንደሚያደርጉ ታወቀ። የወያኔ መንግስት በአገር ውስጥ በከፍተኛ የህዝብ ተቋውሞና አልገዛም ባይነት ተወጥሮ ባለበት ባአሁኑ ወቅት እንደዚህ ያለው ጉብኝት ከወዳጆቹ ምእራባውያን ለተጨማሪ ነቀፌታ እንዲሁም ጠጠር ላለ ጫና ሊዳርገው ይችላል። በቢሾፍቱ የኢረቻ በአልን ለማክበር በወጡት ኢትዮጵያውያን ላይ የወያኔ መንግስት በተጠቀመው የአስለቃሽ ጢስ ጥይት ምክንያት ህይወታቸው ያለፈው ወደ 680 በደረሰበት ፣ በመላው የአማራ ተወላጅ ላይ ግልጽ የሆነ ጦርነት በታወጀበት ፣ በአፍሪቃ መቀመጫና የተለያዩ አገራት ኤምባሲ በሚገኝባት በአዲስ አባባ የኢንተርኔትና የማህበራዊ ሚዲያዎች በተዘጉበት በዚህ ጊዜ ወያኔ እንኩዋን በቀጠናው በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም ማስፈን እንደተሳነው እንዴት አድርጎ ለጀርመኑዋ ካንስለር አንጌላ መርክል ማስረዳት እንደሚችል ትልቅ የቤት ስራና የራስ ምታት ሆኖበታል። በአዲስ አበባ የጀርመን ኤምባሲ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ መሰረት የአንጌላ መርክል የስራ ጉብኝታቸው ዋናው ምክንያት በቀድሞ የታንዛኒያ መሪ በነበሩት ጁሊዬስ ኔሬሬ (Julius Nyerere) ስም የተሰየመውን አዲሱን የሰላምና ደህነት ህንጻ ለማስመረቅ እንደሆነ መረዳት ተችሏል። ካንስለር ሜርክል በዚሁ ህንጻ ንግግር እንደሚያደርጉም መግለጫው ጠቅሱዋል። ይህ ህንጻ በጀርመን መንግስት የገንዘብ እርዳታ እንዲሁም የጀርመን ተቋራጭ የተገነባ መሆኑን ኤምባሲው በመግለጫው አስፍሯል። የመላ ኢትዮጵያውያንን ሰላምና ደህንነት እየነፈገ አምባገነኑ የወያኔ መንግስት በቀጠናው ሰላምን አሰፍናለሁ በሚል ሰበብ የስልጣን እድሜውን ለአንድም ቀን ብትሆን ለማራዘም ለምእራብያውያን ጉዳይ አስፈጻሚና ሎሌ ከሆነ ሁለት አስርተ አመታት አልፈውታል። በርግጥም የወያኔ መንግስት ለውስጥ (ለህዝቡ) ቀካ ለውጭ አልጋ ነው። የጀርመን መንግስት በከፍተኛ ገንዘብ ይህንን ህንጻ ያሰራው ገና ለገና ወያኔ ደሃውን የኢትዮጵያ ሰራዊትን( የተደላደሉትን የአጋዚ ወታደሮችን አያካትትም ) በሱማሌ ይገብርልናል በሚል እሳቤ እንጂ እውነተኛ ሰላምን ደህንነትን እንዲሁም ዲሞክራሲን አስቦ እንዳልሆነ መረዳት ይቻላል። ለዚህም ማስረጃ በወያኔ መንግስት ትእዛዝ የአጋዚ ወታደሮች በኦርምያ፣ በጎንደር፣ በባህር ዳር፣ በጎጃም፣ በኮንሶ፣ በጋምቤላ እንዲሁም በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ያደረሱትን አረመናዊ የሆነ ግድያ መመልከት በቂ ነው። ወያኔ የበግ ለምድ ለብሶ ተኩላ መሆኑን( እንኩዋን አሽባሪን ሊዋጋ እራሱ አሽባሪ መሆኑን) በሰላማዊ መንገድ ተቋውሟቸውን ለመግለጽ አደባባይ በወጡ ንጹሃን ዜጎች ላይ እየወሰደ ባለው ግድያ፣ አፈና፣ እስራትና ድብደባ በተግባር ለአለም አረጋግጧል።

ምእራብያውያኑ አፍሪቃን የመቀራመት አባዚያቸው በአሃጉሪቷ ውስጥ በከፍተኛ ተቀባይነት እንቅስቃሴ በምታደርገው ቻይና ምክንያት እንደገና እያገረሸባቸው ይገኛል። 200 ሚሊዮን
ዶላር በማውጣት የቻይና መንግስት በ 2012 እኤአ የአፍሪቃ ህብረት ህንጻን በስጦታ መስጠቱ ምእራባውያንም አትኩሮታቸውን ወደ አፍሪቃ እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል። ለዚህም ይመስላል የጀርመን መንግስት ይህን በጁሊዬስ ኔሬሬ ስም የተሰየመውን አዲሱን የሰላምና ደህነት ህንጻ ፈንድ በማድረግ ያሰራው። ከጸጥታና ደህንነት በተጨማሪ የካንስለር አንጌላ መርክል የኢትዮጵያ ጉብኝት የስደተኛ ጉዳይን ይጨምራል ተብሎ ይገመታል። በ 11/ 10/ 2016 የጀርመን ኤምባሲ ከአለም የምግብ ፕሮግርም(WFP) ጋር በመሆን ባወጣው ጥምር ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር የሆኑት ዮሃም ሽሚትስ (JoachimSchmidt) የስደተኛ ጉዳይ በጀርመን ውስጥ አንገብጋቢ የፖለቲካ ጥያቄ መሆኑን ገልጸዋል(http://www.wfp.org/news/news-release/germany-provides-more-critical-support-refugee-food-assistance-ethiopia) ። የወያኔ መንግስት ቁንጮ የሆኑት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ በአየር መዛባት ወይም ኤል- ኒኖ መንስኤ ተከስቶ በነበረው የረሃብ ችግር በኢትዮጵያ ውስጥ ተጠልለዋል ያሉትን የደቡብ ሱዳን፣የኤርትራንና የሶማሌን ስደተኞችን እንደ ምክንያት ማቅረባቸው ይታወሳል(http://www.aljazeera.com/news/2016/03/ethiopia-calls-international-drought-bites-160317142601295.html ) ። እነዚህ ስደተኞች ወደ አወሮፓ እንዳይመጡ ለመከላከል ምእራባውያኑ ለወያኔ ዳጎስ ያለ ገንዘብ በየአመቱ እንደሚለግሱት ቢታወቅም በቅርቡ የአውሮፓ ህብረት የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያውያን ላይ በሚያደርገው የመብት ጥሰትና ግድያ ምክንያት ያቀደውን የገንዘብ እርዳታ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ በ 06/ 09/ 2016 እኤአ መወሰኑ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on October 7, 2016
  • By:
  • Last Modified: October 7, 2016 @ 9:43 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar