www.maledatimes.com በአፍሪካ የጅምላ ግድያን (የዘር ማጥፋት) አስመልክቶ ፓናል ዲስከሽን ተካሄደ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በአፍሪካ የጅምላ ግድያን (የዘር ማጥፋት) አስመልክቶ ፓናል ዲስከሽን ተካሄደ

By   /   November 1, 2016  /   Comments Off on በአፍሪካ የጅምላ ግድያን (የዘር ማጥፋት) አስመልክቶ ፓናል ዲስከሽን ተካሄደ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 24 Second

በኖርዝ ኢስተርን ኢልኖይስ ዮኒቨርሲቲ የአፍሪካ ጥናት እና ምርምርም ተቋም ውስጥ በተካሄደው የአፍሪካ መሪዎች የዝር ጅምላ ግድያን አስመልክቶ በተለያዩ አፍሪካ አገራቶኦች እንዴት ዘርን ያመላከተ የጅምላ ግድያ እንደ ተከናወነ ገልጸዋል ።

የመጀመሪያውን ገለጻ በሁቱ እና ቱሲ ስለነበረው ከተማሪውች ጥናታዊ ጽሁፍ የቀረበ ሲሆን ከማለዳው ጀምሮ የተለያዩ ተማሪዎች እና ምሁራኖች የግላቸውን አስተያየት እና ጥናታዊ ስሁፎችን አቅርበው ለህዝቡ የመወያያ መድረክ ፈጥረዋል ።

በአፍሪካ በተለያዩ ሃገራቶች በተለያዩ ጊዜያቶች የቀረቡት የዘር ማጥፋት ወንጀል ከፍተኛ ቁጥርን ይይዛል ሲሉ ጥናቶች ሲያመለክቱ ከነዚህም ውስጥ ሩዋንዳ ቀዳሚነቱን ይዛ ትገኛለች ።

እስከዛሬ ድረስ ከቅኝ ግዛት ያልተላቀቁት አፍሪካ ሃገራቶች በተለያየ የአስተዳደር ጭቆና ከፍተኛውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በራሳቸው ዜጎች እንዲፈጸምባቸው ከተለያዩ የአውሮጳ ሃገራቶች ጫና እንደሚደረግባቸው ተጠቁሞአል።በሌላም በኩል በሩዋንዳ ከተደረገው ጭፍጨፋ እንደሚያመለክተው ከሆነ ፣ጭፍጨፋው ከመካሄዱ 3 አመታት ቀደም ብሎ የቋንቋ መለወጥ እና ህዝብን በተለያየ ጎራ ማየቱ ክፍተኛውን የግድያ ጫና እንዲኖር አድርጓል ሲሉ የአፍሪካ ጥናት እና ምርምር ተመራማሪ ገልጸዋል።

የሩዋንዳ ተወላጅ የሆነችው ጄኒም በ1972 በሃገሯ የተፈጠረውን የዘር ማጥፋት በግልጽ ምን አይነት እንደነበር እና እንዴት ከዚያ አሰቃቂ የጅምላ ግድያ እንደተረፈች የገለጸች ሲሆን ፣ እንዴት በባህል በህዝብ እና በሃገር እንዴት አይነት የዘር ማጥፋት እንደተካሄደ በጥልቀት ማወቅ እና ለማወቅ መጣር እንዳለብን አመክራ ትገልጻለች ፣በተለይም ብዙ አይነት የዘር እና የቋንቋ  ተናጋሪ ባለበት በዚህ ሰፊ አለም ላይ በተለያዩ አጋጣሚዎች ልናውቃቸው የምንችላቸውን ነገሮች ጠልቀን እንዴት በአፍሪካ ሃገራት ላይ የጅምላ ግድያ ተከናወነ ብለን ጥልቅ የሆነ ምርምር ማድረግ አለብን ብላ ትጠቁማለች ።

በሌላ በኩልም የዚሁ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆነችው ወጣት ሳራ እንደ ባህር በጥልቅ በሆነው የአፍሪካ አገር ላይ የሚካሄደውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በሰፊው በአፍሪካ መካሄዱን እና በዚሁ አገር ብዙ ነገሮችን  ማካለል እና ማጥናት እንደቻለች ገልጻለች ።

በናጀሪያ ስለተካሄደውም የጅምላ ግድያ አስመልክቶም የካቶሊክ ቶዮሎጂ እና የሳይኮሎጂ ጥናት ተመራማሪ እና የአፍሪካን ጥናት ተቋም  ሰፊ ዘገባ ለማቅረብ ሞክረዋል ።

በቀጣይም የኢትዮጵያው የሰበአዊ መብት ተከራካሪ እና  አክቲቪስት ኦባንግ ሜቶ በአሳለፍነው 25 አመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ስለተካሄደው  የዘር ማጥፋት ወንጀል እና እንቅስቃሴውን አስመልክቶ በ4 ፡15 እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on November 1, 2016
  • By:
  • Last Modified: November 1, 2016 @ 3:45 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar