www.maledatimes.com ዋና ዋና ስልጣኖች አሁንም በሕወሓት እንደተያዙ ነው | ቴዎድሮስ አድሃኖም ተነስቶ ኦሮሞነት የተለጠፈለት ትግሬው ወርቅነህ ገበየሁ የውጭ ጉዳይ ሚ/ርን ቦታ ያዘ | የአባይ ጸሐዬ የቀድሞ ሚስት ሚ/ር ሆነች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ዋና ዋና ስልጣኖች አሁንም በሕወሓት እንደተያዙ ነው | ቴዎድሮስ አድሃኖም ተነስቶ ኦሮሞነት የተለጠፈለት ትግሬው ወርቅነህ ገበየሁ የውጭ ጉዳይ ሚ/ርን ቦታ ያዘ | የአባይ ጸሐዬ የቀድሞ ሚስት ሚ/ር ሆነች

By   /   November 1, 2016  /   Comments Off on ዋና ዋና ስልጣኖች አሁንም በሕወሓት እንደተያዙ ነው | ቴዎድሮስ አድሃኖም ተነስቶ ኦሮሞነት የተለጠፈለት ትግሬው ወርቅነህ ገበየሁ የውጭ ጉዳይ ሚ/ርን ቦታ ያዘ | የአባይ ጸሐዬ የቀድሞ ሚስት ሚ/ር ሆነች

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 55 Second

  አቶ አባይ ጸሐዬ የቀድሞ ሚስት የነበረችው ወ/ሮ ፈትለወርቅ (ሞንጆሪኖ) ገብረእግዛቤር

(ዘ-ሐበሻ) የትግራይ ነጻ አውጪው መንግስት ተላላኪ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ በዛሬው ዕለት አዲሱን ካቢኒያቸውን ይፋ አደረጉ:: አሁንም የመንግስት ቁልፍ ስልጣኖች በሕወሓት እጅ እንደሚገኙ ታውቋል::

መከላከያውን እና ደህነንቱን ከበላይ የሚመሩት ሕወሓቱ ደብረጽዮን አሁን በስልጣን ላይ ያሉ ሲሆን; በኦሮሞ ስም የሚነግደው ሌላኛው ትግሬ ወርቅነህ ገበየሁ የውጭ ጉዳይ ሚ/ርነቱን ቦታ ይዟል:: የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስተርነቱን ቦታም ሕወሓት በአብርሃም ተከስተ በኩል ወስዳዋለች::

(የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የሆነው ወርቅነህ ገበየሁ ትግሬ ስለመሆኑ ማስረጃ ለማድመጥ እዚህ ይጫኑ)

የትግራዩ ነጻ አውጪ መንግስት ስማቸውን የቀየሩ የትግራይ ተወላጅ የኦህዴድና የብአዴን ባለስልጣናትን በድርጅቶቹ ስም ሹሟል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ከነዚም መካከል ከበደ ጫኔ ይጠቀሳል ይላሉ:: ከበደ በብ አዴን ስም የተቀመጠ ትግሬ ነው:: ጉምሩክ ተሰጥቶታል::

በሌላ በኩልም የአቶ አባይ ጸሐዬ የቀድሞ ሚስት የነበረችው ወ/ሮ ፈትለወርቅ (ሞንጆሪኖ) ገብረእግዛቤር፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ ሆና ተሹማለች:: ወ/ሮ ፈትለ ወርቅ የአዲስ አበባው የካሳንቺሱ መንግስት ዋና አካል ናት::

የተሿሚዎች ስም ዝርዝር
1. ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ
2. ለፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ሚኒስትርነት አቶ ታገሰ ጫፎ
3. ለገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስትርነት ዶ/ር አብርሃም ተከስተ
4. ለንግድ ሚኒስትርነት ዶ/ር በቀለ ሙላዱ
5. ለእንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ሚኒስትርነት ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ
6. ለእርሻና የተፈጥሮ ሃብት ሚኒስትርነት ዶ/ር እያሱ አብርሃ
7. ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርነት ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ
8. ለትራንስፖርት ሚኒስትርነት አቶ አህመድ ሽዴ
9. ለከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትርነት ዶ/ር አምባቸው መኮንን
10. ለኮንስትራክሽን ሚኒስትርነት ኢንጂነር አይሻ መሃመድ
11. ለየውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስትርነት ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ
12. ለማዕድን፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትርነት አቶ መቱማ መቃሳ
13. ለአካባቢ ደንና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትርነት ዶ/ር ገመዶ ዳሌ
14. ለትምህርት ሚኒስትርነት ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም
15. ለጤና ጥበቃ ሚኒስትርነት ፕሮፌሰር ይፍሩ ብርሃነ
16. ለመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትርነት ዶ/ር ግርማ አመንቴ
17. ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስትርነት ዶ/ር ሂሩት ወልደማርያም
18. ለሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትርነት ወ/ሮ ደሚቱ ሃምቢሳ
19. ለወጣቶችና ስፓርት ሚኒስትርነት አቶ ርስቱ ይርዳው
20. ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊ ሚኒስትርነት አቶ ከበደ ጫኔ
21. ለመንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሃላፊ ሚኒስትርነት ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ

ባሉበት የሚቀጥሉ
1. አቶ ደመቀ መኮንን (ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር)፣
2. አቶ ሲራጅ ፈርጌሳ፣
3. አቶ ካሳ ተክለብርሃን
4. አቶ ጌታቸው አምባዬ
5. ዶ/ር ደብረፅዮን ደብረሚካዔል
6. አቶ አህመድ አብተው
7. ዶ/ር ይናገር ደሴ
8. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ እና
9. አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on November 1, 2016
  • By:
  • Last Modified: November 1, 2016 @ 1:18 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar