www.maledatimes.com ድር ቢያብር አንበሳ ያስር(ዳንኤል መኩሪያ) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ድር ቢያብር አንበሳ ያስር(ዳንኤል መኩሪያ)

By   /   October 8, 2012  /   Comments Off on ድር ቢያብር አንበሳ ያስር(ዳንኤል መኩሪያ)

    Print       Email
0 0
Read Time:10 Minute, 27 Second

አገራችን ኢትዮጵያ የብዙ ቋንቋዎች፡ባህሎችና ዕምነቶች ሀገር ከመሆንዋ ጋር የብዙ ስነ ቃሎች፡ተረቶችና ምሳሌዎችም ባለቤት ናት።እነዚህ አገራዊ እሴቶች የማስተማር፧የመምከር፡የመገሰጽና የማስጠንቀቅ ኃይል አላቸው።ከላይ በርዕሴ የተጠቀምኩበት የአማሪኛ ምሳሌ በጣም ቀጭን የሆነችውና በጣም በትንሽ ሀይል ልትበጣጠስ የምትችለው ድር ( የፈትል ክር) በጉልበቱና በሃይሉ የአራዊት ሁሉ ንጉሥ የሆነውን አያ አንበሳን የማሰር ብቃት እንዳላት የሚያሳይ ሲሆን የድሩ ጥንካሬ የሚመነጨው ግን ከተሰራችበት የጥጥ ዓይነት ወይም ዝርያ ሳይሆን እንደ እርስዋው ደካማና ቀጫጭን ከሆኑ ሌሎች ድሮች ጋር ሆና አንበሳውን ለመጣል በሚደረግ ትግል ውስጥ ለመሳተፍ ከተደረሰ የጋራ ስምምነትና ትብብር ነው።

እስኪ አንድ ጥያቄ ራሳችንን እንጠይቅ፦አንዲቷ ድር ብቻዋን  አንበሳውን ለማሰር ብትሞክር ትችላለችን?ሳትበጠስስ ምን ያህል ጊዜ ትቆያለች?

መልሱ፥ብቻዋን አንበሳውን ለማሰር አትችልም፤ብቻዋን ለማሰር ብትሞክር ግን ዕድሜዋ ከጥቂት ሰከንዶች አይዘልም፥የሚል ይሆናል። ድር  አንበሳን የማሰር ብቃት ሊያገኝ የሚችልበት ብቸኛዉ ሚስጥር አንድ ነው፦መተባበር። የጠቅላላው ድር ጉልበት ሊተባበሩ በወሰኑትና እርስ በእርሰ በተያያዙት የድሮች ብዛት ይወሰናል፡አንድ ርግጠኛ ነገር ግን አለ፥ድሮቹ ከተባበሩ አንበሳው ይታሰራል፤ለመንቀሳቀስ ጉልበትን ያጣል፡ ሌሎችን ሊበላም ሆነ ሊጎዳ አይችልም በሂደትም ይሞታል።ጉልበታሙ አንበሳ በደካሞቹ ድሮች የትናትና ታሪክ ይሆናል።

ይህንን ጽሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ዋና ጉዳይ ኢትዮጵያውያን የምንታማበት ተባብሮ ለመስራት ያለመቻል ችግር ሲሆን አንባገነኑን የአገራችንን መንግሥት ለመቀየር በሚንቁሳቀሱ ተቃዋሚ ድርጅቶች ላይ ያተኩራል። ኢትዮጵያውያን በህብረት መብላት እንጅ  በህብረት መስራት እንደማንችል በብዙዎች ሲነገር ሰምቻለሁ፥በሩጫ ውድድር በአለም ያገኘነውን የረጅም ጊዜ ታዋቂነት ከደካማው የእግር ኳስ (የህብረት) ጨዋታ ሪኮርድ ጋር በማወዳደር ነገሩን ለማሳመን የሚሞክሩ ሰዎች አጋጥመውኛል፥ድምዳሜቸው ትክክል እንዳልሆነ ለማሳየት የቅርብ ጊዜው የኢትዮጵያ ሴቶች የእግር ኳስ ቡድን እንቅስቃሴና ተስፉ ሰጭ ውጤት መጥቀስ ይበቃኛል። የባህላችን ችግር ነው እንዳልል ባህላችን በህብረት የመብላት ብቻ ሳይሆን በህብረት የመስራት፥ በህብረት ሐዘንና ችግርን የመጋራት፧ በህብረት የጋራ ጠላትን የመከላከል ዘመናትን የዘለለ ባህል እንደሆነ ለማሳየት ዕድር፧ዕቁብ፡ጅጌ፡ደቦ የመሳሰሉትን አገራዊ ዕሴቶችና በባዕዳን ወራሪዎች ተከፍተውብን በጋራ ትግል በድል ከተጠናቀቁት ጦርነቶች መካከል የአድዋውን መጥቀስ በቂ ነው።

አገራችን የውጭ ወራሪዎች በገጠማት ጊዜያት የነበሩት ነገስታት ነጋሪት በማስጎሰም ህዝቡን ለአገሩ እንዲዘምት እንዲህ ብለው የክተት ጥሪ ያስተላልፉ እንደነበር ይነገራል፦አገራችን በጠላት ተወራለችና ዕድሜህ ለጦር የደረስህ ሁሉ በየጎበዝ አለቃህ እየተደራጀህ ተከተለኝ፥ጉልበት የሌለህ ግን በፀሎትህ እርዳኝ።ይህን ጥሪ የሰማው ሕዝብም ዘር፡ቋንቋ፡አካባቢ ሳይል በየጎበዝ አለቃው እየተደራጀ ምላሽ ይሰጣል፣አቅመ ደካማውም እንደ የዕምነቱ ወደ አምላኩ በመፀለይ ያግዛል።እንግዲህ ይሄው ነው አገራችን በቅኝ ግዛት ሳትገዛ በነጻነት እንድትቆይ ያደረጋት የሁሉም ወገን ህብረትና እያንዳንዱ የራሱን ድርሻና የየአቅሙን መወጣት፦ወትሮስ ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ለሃምሳ ሰው ጌጡ አይደል?

አንባገነኑን የወያኔን መንግሥት ለመጣል በሚንቁሳቀሱ ተቃዋሚ ድርጅቶች መካከል ትብብር ምርጫ ሳይሆን አገርን የማዳን ታሪካዊ ግዴታችን ነው፥ምክንያቱም ትግሉ በድሮች ትብብር ሊታሰር እንደሚችለው አንበሳ ጠንካራ የኢኮኖሚ፣የወታደራዊ ፣የስለላና የደህንነት  ተቋም ከገነባ ቡድን ጋር ነውና፥ የ1997 ቱ የምርጫ ትብብር ለዚህ ትልቁ ማሳያ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ወይ ተባበሩ ያለዚያ ተሰባበሩ ሲል የነበረው በተናጠል የሚደረገው ትግል በተናጠል አንበሳውን ለማስር እንደምትሞክረው ፍጻሜዋም መበጣጠስ ብቻ እንደሚሆነው ድር አይነት ነው ።የኔ ሃሳብ ብቻ፣የኔ ድርጅት ብቻ፣የኔ የትግል ስልት ብቻ የሚለው ነገር የትም ሊያደርሰን አይችልም።

ትብብርን በተመለከተ ከዚህ በፊት ብዙ የተባለ ቢሆንም ሰሞኑን የሚታየው እርስ በእርስ መካሰስ እንደ አዲስ ያገረሽበት ስለሚመስል  ይህችን አጭር ምክር ለመወርወር ተነሳሳሁ።መተባበራችን ወያኔን ያዳክመዋል፣ጉልበት ያሳጣዋል፣ያሽመደምደዋል በሂደትም ያስወግደዋል፥ዳግመኛም አገርና ወገናችንን እንዳይጎዳ ያደርገዋል።

ጉልበታሙ ወያኔ በተቃዋሚ ድሮች ትብብር የትናትና ታሪክ ይሆናል። ፍላጎታችን ይህንን ማየት ከሆነ መተተባበር አማራጭ አይደለም ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን እርስ በእርስ የምንወራወረው ድንጋይ ሁላችንንም ያጠፉናልና እናስተውል።

«ነገር ግን እርስ በእርሳችሁ ብትነካከሱ፡ብትበላሉ እርስ በእርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ።» ገላትያ 5፥5

በሚቀጥለው እስክንገናኝ ቸር እንሰንብት!

 

እግዚአብሄርኢትዮጵያን ይባርክ!

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar