www.maledatimes.com አቤ ቶኪቻው ፀረ ኢትዮጵያ? - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አቤ ቶኪቻው ፀረ ኢትዮጵያ?

By   /   October 19, 2012  /   1 Comment

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 49 Second

ሰሞኑን “አይጋ” የተባለ የወያኔ ድረገፅ ግብረአበሮች ያላቸውን ሶስት ጋዜጠኞች በተከታታይ ፅሁፍ ሲደበድብ ሰንብቶአል። እነዚህ ሶስቱ ጣምራ ጠላቶች፣ አቤ ቶክቻው፣ ተመስገን ደሳለኝ እና እኔ ነበርን። ፀሃፊው እንቅልፍ በተጫጫናቸውና ውሃ በጠማቸው ቃላት ረጅም ሃተታ ፅፎአል። የአቤ፣ የተመስገን እና የኔ ስሞች ያለበትን እየመረጥኩ እየዘለልኩ ነው ያነበብኩት። ምክር ነክ ሃተታዎችን ዘለልኳቸው።

ከሶስቱ ተከታታይ ፅሁፍ ቀልቤን የሳበችው፣ አቤ ቶኪቻውን  ፀረ -ኢትዮጵያ ብለው መፈረጃቸው ነው። እኔን ቢሉኝ ያምርባቸዋል። “የቡርቃ ዝምታ”ን በማንሳት ወይም “ኤርትራዊ ነው” የሚለውን በማደማመቅ ለማሳመን አይከብድም ይሆናል። አቤን ፀረ – ኢትዮጵያ ለማለት እንዴት እንደደፈሩ ግን አልገባኝም። ነፍሱን ይማረውና መለስ በህይወት ቢኖር ኖሮ፣ እርግጠኛ ነኝ ይህን ፅሁፍ የፃፈውን ካድሬ እስርቤት ይልከው ነበር።
አልተረዱትም እንጂ አበበ ቶላ የሃገር ቅርስ ነበር። የህዝብ ስሜቶችን እና ብሶቶችን ጎልጉሎ እያወጣ በሚያስቅ መንገድ እውነትን ለተደራሲው ማቅረብ የቻለ የብእር ጀግና ነው – አቤ። ኢህአዴግ ብልህ ቢሆን ኖሮ፣ እንደ አቤ ያሉ ብእረኞች በነፃነት እንዲፅፉ ማመቻቸት ነበረበት።  መስታወት ይሆኑት ነበር። ስህተቶችን ለማረም ያግዙት ነበር። አቤን በፀረ – ኢትዮጵያነት የሚፈርጅ ምን አይነት ጭንቅላት ይሆን? ይህች ኢትዮጵያ የተባለች ሃገር እንደው ምን ይሻላታል? እውነተኛ ልጆችዋን ቀረጣጥፋ እየበላች የምትኖረው እስከመቼ ይሆን? የጠላቶችዋ መፈንጫ መሆኗ ከቶ መቼ ያበቃል?
ከመለስ መሞት ወዲህ አቤ በፃፋቸው መጣጥፎች፣ ብዙ ጊዜ ጧ! ብዬ ስቄያለሁ። ሁለቱ ግን አይረሱኝም። መለስ በመሞቱ ሃዘናቸውን ገለፁ ስለተባሉት የጎዳና ተዳዳሪዎች ምን ነበር የፃፈው? ቃል በቃል ትዝ አይለኝም፣ አሳቡ ግን እንዲህ ነበር፣
“እኛ ጎዳና ተዳዳሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ተማምነን ነበር ወደ ጎዳና የወጣነው። እሳቸው ከሞቱ ምን እንሆናለን?  እንግዲህ ምን እናደርጋለን። ያለን ምርጫ ያው ወደ ቤታችን መመለስ ነው…”
ሌላዋ ደግሞ እንዲህ ትነበባለች፣
“…እኔ የምለው ዘንድሮ ባለ ስልጣኖቻችንን እየታዘባችሁ ነው? ኩብለላን እኮ የስራቸው አካል አደረጉት። እኛ አቀርቅረን ኮብል ስቶናችንን ስንጠርብ፣ እነርሱ ደግሞ ኮብልል “ስቶን” እያሉ እየነኩት ነውኮ!”
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 12 years ago on October 19, 2012
  • By:
  • Last Modified: October 19, 2012 @ 8:37 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

One thought on “አቤ ቶኪቻው ፀረ ኢትዮጵያ?

  1. hi tesfay bemegemereya i want say thank you selemttefacewe hulu lelawe ahune erasu betafekw yasayekwe yemeqebabele sera betame yegeremale teleqe temeheret newe banetena abe tokcawe bezou temerenale beretu ayzoachhu besaqe eyafnedachu bezu qoume negere astemerachunale

Comments are closed.

<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar