www.maledatimes.com . ኩዌት ለኢትዮጵያውያን ምህረት አደረገች ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

. ኩዌት ለኢትዮጵያውያን ምህረት አደረገች !

By   /   June 20, 2017  /   Comments Off on . ኩዌት ለኢትዮጵያውያን ምህረት አደረገች !

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 24 Second

የማለዳ ወግ ..
=====================================
* ውጭ ጉዳይ ዶር ወርቅነህ ይመሰገናሉ
* የመረጃ ምንጮቸም ትመሰገናላችሁ

የኩዌቱ አሚር ሽህ አል አህመድ አል ጃብሪ በልዩ ልዩ ወንጄሎች በኩዌት እስር ቤት ለነበሩ ኢትዮጵያውያን የምህረት አዋጅ ማድረጋቸውን ኳታርን በመጎብኘት ላይ ያሉት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ወርቅነህ ገበየሁ አስታውቀዋል ። የዶር ወርቅነህ ስለተፈረገው ምህረት ሲያስረዱ አሚሩ ምህረቱን ያደረጉት በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጥያቄ መሰረት መሆኑን ጠቁመዋል። በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው ለነበሩ ኢትዮጵያውያን ምህረት ማድረጋቸው ያስታወቁት ዶር ወርቅነህ በነፍስ ማጥፋት የሞት ፍርድ የተላለፈባቸውን በምህረቱ መካተታቸው አልተብራራም ።

ኳታር የሚገኙት የመረጃ ምንጮቸ እንደጠቁሙኝ ከሆነ ምህረቱ በዋናነት በተለያዩ ጊዜያት ከሀገር ቤት ወደ ኩዌት ሲገቡ ከእቃቸው ጋር ባላወቁት መንገድ ጫት የተያዘባቸውንና በጥቃቅን ወንጀሎች የተያዙ ዜጎችን ብቻ እንደሚያካትት የመረጃ ፍንጭ ሰጥተውኛል ። ትናንት ባቀረብኩት የማለዳ ወግ የመረጃ ግብአት ዶር ወርቅነህ በእስረኞች ጉዳይ ከኩዌቱ አሚር ጋር እንደ ሚነጋገሩ መጠቆሜ የሚታወስ ነው ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ወርቅነህ ስልጣን ከጨበጡ ወዲህ ወደ ከአረብ ሀገራት ጋር ጥሩ ግንኙነት ከመመስረት አልፎ የአረብ ሀገር ስደተኞች ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው መስራታቸውን እየተመለከትን ነው ። በአጭር የስልጣን ጊዜያቸው በኩዌት ወህኒ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያስገኙት ምህረት በፋና ወጊ ስኬት መሆኑ ይጠቀሳል። ዶር ወርቅነህ ከቀጣይ በዘመድ አዝማድና በፖለቲካ ታማኝነት ብቻ የተሞላውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያ ቤትን በብቁ ሰራተኞች አንጸው፣ ሰስደተኛው ትክክለኛ ለመብታችን አስከባሪ ፣ ፣ ዲፕሎማሲያውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ፣ የድርጅት ሳይሆን የሀገርና የህዝብ ተወካይ ወደ አረብ ሀገራት በመመደብ የህዝብ ወገንተኝነታቸውን ያሳያሉ ብለን እንመኝ ።

ከአንድ ወር በፊት በጥድፊያ የተፈረመውንና ዝርዝር መረጃ ያልቀረበበትን የስራና ሰራተኛ ስምምነት መልሰው ይከልሱታል ብለን እንመኝ ። በክለሳው ደመወዝና ጠንካራ የመብት ማስከበሪያ መደራደሪያ በማቅረብ የሰራተኛ ውሉን በግልጽና በተጠያቂነት መንፈስ ያስተካክሉታል ብለን እንመኝ ! የወሬ አቀባዮችን ሳይሆን ትክክለኛውን የህዝብ ድምጽ ከሰሙ ይህንና የመከረኛው ስደተኛ ህይዎት ያሻሽሉታል የሚል እምነት አለኝ !

ዶር ወርቅነህ እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነታቸው ላሳዩን ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ያልታዬና ያልተለመደ ዜጋን የመታደግ ቀዳሚ ምግባር ምስጋና ይገባቸዋል ። ከዚሁ ጎን ለጎን ተጨባጭ መረጃዎችን በማቀበል ለምትተባበሩኝ ወገኖቸ ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ !

ከሰላምታ ጋር !

ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 13 ቀን 2009 ዓም

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on June 20, 2017
  • By:
  • Last Modified: June 20, 2017 @ 7:31 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar