www.maledatimes.com በጸረ-ሽብር አዋጁ አንቀፅ 3 “የሽብር ድርጊት ፈፅመዋል” የሚል ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት አቶ ጉርሜሳ አያኖ፤አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ አዲሱ ቡላላ ክሳቸው “በሽብርተኛ ድርጅቶች ውስጥመሳተፍ” ወደሚል ተቀይሮ ተከላከሉ ተብለዋል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በጸረ-ሽብር አዋጁ አንቀፅ 3 “የሽብር ድርጊት ፈፅመዋል” የሚል ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት አቶ ጉርሜሳ አያኖ፤አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ አዲሱ ቡላላ ክሳቸው “በሽብርተኛ ድርጅቶች ውስጥመሳተፍ” ወደሚል ተቀይሮ ተከላከሉ ተብለዋል

By   /   July 13, 2017  /   Comments Off on በጸረ-ሽብር አዋጁ አንቀፅ 3 “የሽብር ድርጊት ፈፅመዋል” የሚል ክስ ቀርቦባቸው የነበሩት አቶ ጉርሜሳ አያኖ፤አቶ ደጀኔ ጣፋና አቶ አዲሱ ቡላላ ክሳቸው “በሽብርተኛ ድርጅቶች ውስጥመሳተፍ” ወደሚል ተቀይሮ ተከላከሉ ተብለዋል

    Print       Email
0 0
Read Time:58 Second

የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ሃሙስ ሀምሌ 6/2009 ዓም በዋለው ችሎት በኦፌኮው ም/ል ሊ/መንበር በአቶ በቀለ ገርባ ላይ የቀረበውን የሽብር ወንጀል ክስ በመቀየር ፣ በወንጀለኛ ህጉ አንቀፅ 257 ሀ ስር የተደነገገውን ግዙፍ ያልሆነ ማሰናዳት ስር የተጠቀሰውን እንዲከላከሉ በይኗል።
በጉርሜሳ አያና መዝገብ ከተከሰሱት መካካል ከ ተራ ቁጥር አንድ እስከ 13 የተካተቱት ተከሳሾች የቀረበባቸው የሽብር ወንጀል ክስ ተቀይሮ መገፋፋትና ግዙፍ ያልሆነ ማሰናዳት በሚለው የጸረ ሽብር አዋጅ አንቀጽ 7/1 እንዲካለከሉ በይኗል።
ተከላከሉ ከተባሉት ውስጥ ጉርሜሳ አያና፣ ደጀኔ ጣፋ፣ አዲሱ ቡላላ፣ አብደታ ነጋሳ፣ ፣ ገላና ነገራ፣ ጌቱ ግርማ፣ በየነ ሩዳና ተስፋየ ሊበን የሚገኙ ሲሆን፣ ጭምሳ አብደሳ፣ ፍራኦል ቶላ፣ ጌታቸው ደረጀ እና አሸብር ደሳለኝ ደግሞ ከክሱ ነጻ ተብለዋል።
ከ14 እስከ 22 ባለው ተራ ቁጥር የተቀመጡት ደረጀ መርጋ፣ የሱፍ አለማየሁ፣ ኢካ ተክሉ፣ ገመቹ ሻንቆ፣ መገርሳ አስፋው፣ ለሚ ኢዴቶ፣ አብዲ ታምራት እና አብዲ ኩምሳ ቀደም ብለው ተከሰውበት በነበረው አንቀጽ 7(1) ስር የተጠቀሰውን እንዲከላከሉ ተበይኖባቸዋል።
አቶ በቀለ ገርባ እንዲከላከሉ የተጠቀሰባቸው አንቀጽ እስከ 10 ዓመት በሚደርስ እስር የሚያስቀጣ ቢሆንም የዋስትና መብትን ግን አይከለክልም። አቶ በቀለ ዋስትና እንዲፈቀድለት በጠበቆቹ በኩል ጥያቄ አቅርቦ የነበር ቢሆንም፣ ፍርድ ቤቱ ‹‹በፅሁፍ አስገቡ›› የሚል ትእዛዝ በመስጠት በእለቱ ውሳኔ ሳይሰጥ አልፎታል፡፡
ፍርድ ቤቱ ከሃምሌ 8-12 ጊዜ ውስጥ የመከላከያ ምስክሮችን ይሰማል ተብሎ ይጠበቃል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on July 13, 2017
  • By:
  • Last Modified: July 13, 2017 @ 1:37 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar