www.maledatimes.com አራጣ በዳሪው በልዩ ስማቸው ወርልድ ባንክ የተሰኙት ግለሰብ በፕረዚዳንት ሙላቱ የምህረት ደብዳቤ መሰረት ከእስር መለቀቃቸውን የከፍተኛው ፍርድቤቱ አስታወቀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አራጣ በዳሪው በልዩ ስማቸው ወርልድ ባንክ የተሰኙት ግለሰብ በፕረዚዳንት ሙላቱ የምህረት ደብዳቤ መሰረት ከእስር መለቀቃቸውን የከፍተኛው ፍርድቤቱ አስታወቀ

By   /   July 13, 2017  /   Comments Off on አራጣ በዳሪው በልዩ ስማቸው ወርልድ ባንክ የተሰኙት ግለሰብ በፕረዚዳንት ሙላቱ የምህረት ደብዳቤ መሰረት ከእስር መለቀቃቸውን የከፍተኛው ፍርድቤቱ አስታወቀ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 12 Second

 

በአዲስ አበባ በአራጣ ብድር ህዝቡን ባዶ ሜዳ ያስቀሩት እና ብዙሃኑን በማስለቀስ ረገድ ወደር ያልተገኘላቸው አቶ ከበደ ተሰራ ከእድሜ ልክ እስራታቸው መለቀቃቸውን የከፍተኛ ፍርድቤት አንደኛ ምድብ ችሎት ከአቶ ሙላቱ ተሾመ በደረሰው የምህረት ደብዳቤ መሰረት ግለሰቡን ከእስር እንደለቀቀ አመልክⶆል ።

  በአርራጣ ብድርና በህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ተከሰው የ 25 አመት እስር ፍርደኛ የነበሩት አቶ ከበደ ተሰራ በኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ ምህረት መለቀቃቸው ተነግሯል።

አቶ ከበደ ተሰራ በአንድ ወቅት በአራጣ አበዳሪነታቸው የ አለም ባንክ (ወርልድ ባንክ) የሚል ቅጽል ስም በህብረተሰቡ ወቶላቸው  እንደነበር ይታውቃል።

በፐሬዝደን ሙላቱ ምህረት የተደረገላቸው ኣቶ ከበደ ተሰራ 8 ዓመታት ከታሰሩ በኋላ 17 ዓመታት የእስር ጊዜ ሲቀራቸው መሆኑን ፎርቹን ጋዜጣ ዘግቧል ።

አቶ ከበደ ተሰራ በአራጣ ብድርና በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ከተከሰሱ በኋላ የ25 ዓመታት እስር ሲፈረድባቸው 4 ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ የሰሩት ባለ ዘጠኝ ፎቅ ህንጻን መንግስት ወርሶባቸዋል።

የህንን ፎቅ የወረሰው መንግስትም በጨረታ ሂደት በ680 ሚሊዮን ብር ለንግድ ባንክ መሸጡ የታወሳል አቶ ከበደ ተሰራ ከእስር ሲወጡ የ 75 ዓመት አዛውንት መሆናቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል ። በተመሳሳይ የአራጣ ብድርና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር ተከሰው ዘብጥያ የወረዱት አቶ አየለ ዱባለ 22 ዕመታት ተፈርዶባቸው በእስር ላይ አንዳሉ መሞታቸው ይታወሳል ።አቶ አየለ ዱባለም አይ ኤም ኤፍ በሚል ቅጽል ስማቸው ያታወቁ ነበር።

አቶ ከበደ ተሰራም ሆነ አቶ አየለ ዱበለ ለበርካታ ዓመታት በአራጣ ብድርና በህገወጥ ሲታሙ ለረጅም ግዜ ሳይታሰሩ ከቆዩ በኋላ በአንድ ውቅት በድንገት መታሰራቸውን ብዙዎችን ሲያነጋግር የነበረ ጉዳይ ነው ።

ሁለቱም ፍርደኞች በታክስ ማጭበርበርም ተከሰው እንደነበር አይዘነጋም ። አቶ ከበደ ተሰራ በአሁኑ ጊዜ ለምን በፕሬዘዳንት ሙላቱ ተሾመ በምህረት ሊለቀቁ እንደቻሉ የተገለጸ ነገር የለም። የአቶ ከበደ ጠበቃ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on July 13, 2017
  • By:
  • Last Modified: July 13, 2017 @ 1:46 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar