www.maledatimes.com በሙስና ተጠርጥዋል የተባሉ ግለሰቦችንና ባለስልጣናት የማሰር ዘመቻው ቀጥሏል- ተጨማሪ ከፍተኛ ነጋዴዎችና ባለስልጣናት እስሩን ይቀላቀላሉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በሙስና ተጠርጥዋል የተባሉ ግለሰቦችንና ባለስልጣናት የማሰር ዘመቻው ቀጥሏል- ተጨማሪ ከፍተኛ ነጋዴዎችና ባለስልጣናት እስሩን ይቀላቀላሉ

By   /   July 30, 2017  /   Comments Off on በሙስና ተጠርጥዋል የተባሉ ግለሰቦችንና ባለስልጣናት የማሰር ዘመቻው ቀጥሏል- ተጨማሪ ከፍተኛ ነጋዴዎችና ባለስልጣናት እስሩን ይቀላቀላሉ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 21 Second

Maleda Times media group

July 29, 2017 

  • ትናንት ማምሻውን ቦሌየባለሥልጣናት መንደር ግርግር ተፈጥሯል
  • ደኅንነት መሥሪያ ቤት ባልደረቦች መሐል አለመግባባትእንዳለ እየተነገረ ነው፡፡
  • ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ትናንት ሊሰጠው የነበረውንመግለጫ ተሰርዟል
  • ዛሬ ረፋድ ላይ ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ጌታቸው አምባዬከጋዜጠኞች ጋር ይገናኛሉ::

ዋዜማ ራዲዮ- በከፍተኛ ሙስና ተጠርጥረው የሚታሰሩየመንግሥት ኃላፊዎች ቁጥር ወደ 40 ማሻቀቡን ተከትሎ ትናንትማምሻውን ቦሌ ኖቪስ ራማዳ ሆቴል ጀርባ በልዩ ኃይሎች ተከቦነበር፡፡

 

 ዋዜማ የሰፈሩን ነዋሪዎች የአይን እማኝነት በመንተራስ  ባገኘችው መረጃ ብርበራ ለማካሄድ በመጡ የልዩ አቃቤ ሕግባልደረቦችና በድኅነነት መሥሪያ ቤት ባልደረቦች መሐልመነሻው ያልታወቀ አለመግባባት ተፈጥሮ ቆይቷል፡፡ ፍጥጫውበግምት 45 ደቂቃቆች ከቆየ በኋላ መንገዱ ለተሸከርካሪዎችክፍት ተደርጓል፡፡ ኾኖም ዋዜማ የየትኛውም ባለሥልጣንመኖርያ ቤት ሲበረበር ይህ ችግር ሊፈጠር እንደቻለ መረጃማግኘት አልቻለችም፡፡

በአካባቢው እስከ አትላስ በሚዘልቀው መንገድ ወይዘሮ አዜብመስፍንን ጨምሮ 12 የማያንሱ ሚኒስትሮችና ከፍተኛየመንግሥት ሹመኞች መኖርያ ቤት ይገኛል፡፡

ለደኅንነት መሥሪያ ቤት ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደሚሉት‹‹ቅድሚያ ማን ይታሰር፣ ማን ይቆይ›› በሚለው ጉዳይ ደኅንነትመሥሪያ ቤቱ ዉስጥ ባሉ ኃላፊዎች ወጥ አቋም አይታይም፡፡በአቃቤ ሕግና በደህንነቱ ኃይሎች መካከልም የእዝ ሰንሰለቱ ላይመግባባቱ እምብዛምም ነው፡፡

ይህ በእንዲህ ሳለ ትናንት አርብ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በቀናት ልዩነትአዲስ መግለጫ ለመስጠት ጋዜጠኞችን ጠርተው የነበሩትየመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ ጋዜጠኞች ቦታው ከደረሱበኋላ ባልታወቀ ምክንያት መግለጫውን ሰርዘውታል፡፡ጋዜጠኞች ከተበተኑ በኋላም የልዩ አቃቤ ሕግ ሚኒስትሩ አቶጌታቸው አምባዬና ባልደረቦቻቸው በተጠርጣሪዎች ጉዳይ ሰፋያለ መግለጫ እንደሚሰጡ ተነግሮ ጋዜጠኞች ለዛሬ ቅዳሜአራት ሰዓት ተመልሰው እንዲመጡ ተነግሯቸዋል፡፡

 

ዋዜማ ባገኘቸው ሌላ ተጨማሪ መረጃ በሳምንታት ዉስጥ 50 የማያንሱ የነጋዴው ማኅበረሰብ አባላት የእስር ዘመቻውንይቀላቀላሉ ተብሎ ይገመታል፡፡ በፋይናንስ ደህንነት መሥሪያቤት፣ በገቢዎችና ጉምሩክ፣ በዋናው ኦዲተር እንዲሁምከጠቅላይ አቃቤ ሕግ ባልደረቦች የተውጣጣ ኮሚቴ 120 በላይ ነጋዴዎችን በተጠርጣሪነት በጥቁር መዝገቡ አስፍሯል፡፡ለወራት ያህልም የሂሳብ ባለሞያዎቻቸውን በመጥራት፣ስልካቸውን በመጥለፍ፣ ድንገተኛ ፍተሻ በማድረግ መረጃሲያሰባስብ እንደነበር ተነግሯል፡፡ ከነዚህ መሐል በመጀመርያዙር የእስር ማዘዣ ይወጣባቸዋል ተብለው የሚገመቱት 18 የሚሆኑ ከፍተኛ ነጋዴዎች ናቸው፡፡ የብዙዎቹ ክስ ከታክስ ስወራጋር የሚያያዝ ነው፡፡

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on July 30, 2017
  • By:
  • Last Modified: July 30, 2017 @ 6:56 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar